Get Mystery Box with random crypto!

ከእናንተ የመጣ ጥያቄ 231 ጥያቄው? Ene awalaj nurse negn ena salawald al | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ከእናንተ የመጣ ጥያቄ 231

ጥያቄው?
Ene awalaj nurse negn ena salawald aliwulm silezih betechirstian ayidelem awalje yewoledech set bet kegebah tetemkeh new mitgebaw yilegnal tadya ene bezih miknyat hije alakim  metsihafu MN yilal

መልስ

ይሄንን ካንቺ ጋር እኮ አያገናኘውም! ለምሳሌ አንድ ዶክተር የሆነ ሰው  ተፈንክቶ ቢመጣና ደሙን ቢጠራርግለት እና ቢሰፋው ከዛ በኋላ ተጣጥቦ ልብሱን ቀያይሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን ደም ስለነካ ብቻ ይከለከላልን? አይደለም! ስለዚህ አንቺም ተመሣሣይ ነው ማዋለድሽ ከቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ መቅደሱ አይነጥልሽም! ማድረግ ያለብሽ ነገር ልንገርሽ መጀመሪያ ያዋለድሽበትን ልብስ ቀይሪ በደንብ 1 ነጥብ እንኳን የደም ፍንጣሬ አካልሽ ላይ እንዳይቀር ከዛ ንጹሕ ልብስ ለብሰሽ ሰውነትሽን ንጹሕ አድርገሽ ሠዠመግባት ትችያለሽ ! ከተከለከልሽማ እድሜ ልክሽን ከእግዚአብሔር ሳትገናኚ ሳትቆርቢ ሳትጠመቂ መኖርሽ ነው ይሄ ደግሞ ተገቢ አይደለም! ትችያለሽ እሺ!

መጠየቂያ
@Men_Lerdawobot


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube Subscribe በማድረግ አዳዲስ መረጃ ይከታተሉ!

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

@seratebtkrstian


አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
@Men_Lerdawobot