Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን           ክፍል ሰባት         በዲ/ን አቤል ደጀኔ (ፍቅረ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
          ክፍል ሰባት
        በዲ/ን አቤል ደጀኔ (ፍቅረ አብ)

ልዩ የሆነችው የእኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሉኝ ብላ ከምትኮራባቸው እና ከምትጠቀምባቸው ንዋየ ቅድሳቶቿ መካከል #ቅዱስ_መስቀል አንዱ ነው!

እናም ሰሞኑን ስለ መስቀል እየተማማርን ነበረ ካስታወሳችሁ ስለ እንጨት መስቀል ስለ መጾር መስቀል ስለ ብረት መስቀል ስለ ብር መስቀል  ስለ መዳብ መስቀል ምሳሌነት ተማምረን ነበረ!
ዛሬ ደግሞ ማጠቃለያ እንማማራለን !!!
ከነገ ጀምሮ ንዋያተ ቅዱሳት ስማቸውና ምሣሌያቸው ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን አንጻረሰ እንመለከታለን!!!

መስቀል

መስቀል የእርግማን ምልክት የሆነ የወንጀለኞች መቀጫ ነበር፡፡ ሰውን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረው በጥንቱ ፋርስ በዛሬዋ ኢራን ነው፡፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት 339-33 ዓመትነው ይህም የሆነው ‹‹ከመሬት አምላክ›› ወይም አርሙዝድ የተባለው አምላክ በነበረበት
ወቅት ነው፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ከኃጢአትና ከሞት ለመዳን በቀራኒዮ የተሰቀለበት ነው፡፡የእንጨት መሆኑ
በቀደመው ጊዜ ኃጢአት በዕፅ ገብቷልና፡፡ ስለዚህ ለመካስ በዚህ ምክንያት አድርጓል፡፡
ክርስቶስ በደሙ ስለቀደሰው ግን ቅዱስ መስቀል ተብሏል፡፡ በመስቀል ድኅነትን አግኝተናል፡፡ንዋያተ ቅዱሳት ይባርኩበታል! መስቀል የነጻነታችን ግርማ፣ የድህነታችን
መገኛ፣ ጠላትን ድል የምንነሣበት መሳሪያችን ነው!

ለመስቀል ክብር ለምንድን ነው የሚያስፈልገው?

ክርስቶስ መስዋዕት ሆኖ ራሱን የሠዋበት እውነተኛ መንበር በመሆኑ የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት፣ እኛ የዳንበት የነጻነት አርማችን የክርስቲያኖት አንድት የተመሠረተበት የድኅነት አርማችን ስለሆነመስቀል መለኮታዊ ፍቅር የተገለጠበት መሳሪያ በመሆኑ እንሰግድለታለን የፀጋ ስድገት !!!

መስቀል ኃልነ መስቀል ጽንነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንኅነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
            ይቆየን!
ይቀጥላል ....
መልካም ቀን
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   

ለጥያቄለአስተያየት
@fekrAbe
#ሼርርርር