Get Mystery Box with random crypto!

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን           ክፍል ስድስት         በዲ/ን አቤል ደጀኔ (ፍቅረ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
          ክፍል ስድስት
        በዲ/ን አቤል ደጀኔ (ፍቅረ አብ)

ልዩ የሆነችው የእኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሉኝ ብላ ከምትኮራባቸው እና ከምትጠቀምባቸው ንዋየ ቅድሳቶቿ መካከል #ቅዱስ_መስቀል አንዱ ነው!

እናም ሰሞኑን ስለ መስቀል እየተማማርን ነበረ ካስታወሳችሁ ስለ እንጨት መስቀል ስለ መጾር መስቀል ስለ ብረት መስቀል ስለ ብር መስቀል  ስለ መዳብ መስቀል ምሳሌነት ተማምረን ነበረ!

ዛሬ ደግሞ ስለ #ዓውደ_ዓለም መስቀል እንማማራለን!

መስቀሎች አብዛኞቹ ተመሣሣይ ቢሆኑም ይሄ ዓውደ ዓለም መስቀል የተባለበት የእራሱ ምክንያት አለው! ይህም ምክንያት እንደምታዩት በሥዕሉ ላይ እንደምታዩት ክብ ሆኖ የመስቀል አምሳል ይዟል!

ዓውደ ዓለም  መስቀል ምሳሌነቱ ምንድነው ?
የዓውደ ዓለም መስቀል ምሳሌነቱ  በክብ ቅርጽ የተዘጋጀ የተሰራ ስለሆነ የዓለም ሕዝብ በመስቀሉ የመዳኑ ምሳሌ ነው!

ማስታወሻ
የዓውደ ዓለም መስቀል ባያችሁ ቁጥር  ! ስለ ዓለም መዳን ብለህ በመስቀል የተሰቀልከው ክርስቶስ ሆይ ኃጢያቴን ይቅር በለኝ!አቤቱ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይሁን!!! እያላችሁ ጸልዩ! እሺ?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
            ይቆየን!
ይቀጥላል ....
መልካም ቀን
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw
#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   

ለጥያቄለአስተያየት
@fekrAbe
#ሼርርርር