Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን አመሻችሁ? ለሚለው ጥያቄ እግዚአብሔር ይመስገን ያለ የለም እንጂ ጥያቄውን በሚገባ መልሳ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

እንደምን አመሻችሁ? ለሚለው ጥያቄ እግዚአብሔር ይመስገን ያለ የለም እንጂ ጥያቄውን በሚገባ መልሳችሁታል!!! ቃለ ሕይወት ያሠማልን! ቃለ በፍቅር ያሠማልን! ቃ እግዚአብሔር ያሠማልን! ቃለ እግዚአብሔር እራሱ የናፈቃቸው ስንት አሉና!

ወደ መልሱ ስንሄድ በሚገባ መልሳቹታል ማብራራትም አይገባም ግን ለማረጋገጥ ያህል!

አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ድንግልናውን ካጣ ወዶም ይሁን ሳይወድ ማኅተመ ድንግልናውን ካጣ ተክሊል አይደረግለትም!

ካስታወሳችው ቅዳሴ ላይ እግዚአብሔር የድንግልናቸውን ዋጋ አክሊል ይሰጣቸው ዘንድ እንማልዳለን! ይላል ታዲያ ይሄ ምንን ያስረዳል ? የድንግልና ዋጋው ምንድነው ? አክሊል ነው ብሎ አስቀምጦልናል እና ድንግል ላልሆኑ ሰዎች ተክሊል ሊፈጸም አይችልም ማለት ነው! በፍቅርም ግዜ ይሁን በልጅነትም ጊዜ ይሁን ሊጋቡ ቀናትም ይቅራቸው ብቻ ሩካቤ ከፈጸሙ ድንግልና የለም! አንዳንድ ሰዎች ንስሓ ድንግል ያረጋል ይላሉ! ግን ይሄ ትርጓሜው ሌላ ነው! አትቀላቅሉ እሺ!

በድጋሜ እናገራለሁ ሩካቤ የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም አይችልም!!!

ታዲያ ድንግልና ላሌላቸው ሰዎች ቤተ ክርስቲያን እንዴት አድርጋ ትድራለች? ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ከተዳርን እግዚአብሔር አይባርክልንም ስለዚህ ምን ይሻላል? ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም መጠነቅም ማወቅም ያስፈልጋል!

የውላችሁ አስተውላችሁ ስሙኝ ሳይሆን አዳምጡኝ! አዳምጡኝ! የኛ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያልሰራችልን ሕግ ያልሰጠችን ነገር የለም! አንድም ነገር ያለ ምሳሌ አታደርግም! አንድም ነገር ጎዶሎ የለም ሁሉ ሙሉ ነው!  እናም ድንግልና ላሌላቸው ሰዎች ወይም ላፈረሱ ልበለው እና ለእነሱ ምን አዘጋጀች ቅዱስ ቁርባን አዘጋጀች! በቅዱስ ቁርባን መጋባት ይችላሉ!!! ካባ ይለብሳሉ ቀለበት ያደርጋሉ አበቃ!!!

ግን ተክሊሉ ፍጹም ይለያል ! ስለ ተክሊል በሰፊው ሌላ ጊዜ እጽፍላችኋለው ነካ ነካ ከርጌ ከማልፍ እና እንደዛ ነው እላችኋለው

ቀጣይ ጥያቄ ደግሞ ጠብቁኝ
ዲ/ን አቤል (ፍቅረ አብ)
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw

#subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ

@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   

     join
ለጥያቄ ለአስተያየት
@fekrAbe
#ሼርርርርርርርርርርር