Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ በጣጣጣጣምምም ደስስስ ብሎኝ ነው የዋልኩት! ለምን አትሉኝም? ዛሬ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ ለ | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

ዛሬ በጣጣጣጣምምም ደስስስ ብሎኝ ነው የዋልኩት! ለምን አትሉኝም?

ዛሬ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ ለመጠቅ ሄድኩ 7 ሰዓት ነው የሚከፈተው የእኛ ደብር ጸበል ቤት እና ሄጄ ተጠመኩኝ እና ማንም የለም ነበረ ወላ አጥማቂዎቹ እንቅልፍ እያዳፋቸው ነበረ እና አንዳንድ ካህናት እየመጡ በዛ ሌሊት ይጠመቃሉ!ለምን በሌሊት ሄድክ የምትሉ አትጠፉም ለምን መሠላችሁ አንድ ካህን ወይም ዲያቆን አካሉ በግልጽ መታየት የለበትም ለምሳሌ ደረቱ ወዘተመታየት የለበትም ምክንያቱም እንዳይመኙት ከተመኙት ደግሞ የተመኘ አመነዘረ እንዳለ እና ለዛም ነበረ በሌሊት የምንጠመቀው እና ደስ ይል ነበረ ጸበሉ ልክ ስወጣ ግን የብርዱ ነገር አጠይቁኝ እና በዛ ሰዓት ማንም ሰው ስላሌለ ወይሄ በቃ የሚጠመቅ ጠፋ ሕዝበ ክርስቲያኑ መጠመቅ አይፈልግም ወይስ አያውቅም ብዪ አዝኜ ወደ ቤቴ ሄድኩ ! ከዛ 11 ሰዓት እስኪ ኪዳን ላድርስ እዚህ ተጋድሜ ምን አረጋለሁ ብዪ ተነስቼ እሄዳለሁ በየት ልለፍ ሕዝቡ ጥቅጥቅ ብሏል በዛ ሰዓት የተሰማኝ ደስታ በስመ አብ ምን ብዪ ልግለጽላችሁ በጣም የሚገርም ነው ሰልፉ ከስኳርና ከዘይት ከታክሲ ሰልፍ በለጠ በጣምምምም ደስ ብሎኝ እግዚአብሔር እያመሠገንኩ ለካ ሕዝቡ አለ አልኩኝ በልቤ እና ኪዳኔን አድርሼ ወደ ቅዳሴ ሲገቡ እኔ ወደ ቤቴ ወጥቼ ስመጣ ሲጀመር ጸበል ቤቱጋ ታቦታ የወጣ በቃ ንግሥ አታውቁም ንግሥ ነው እንጂ ጸበል ነው አትሉም ሕዝቡ በስመ አብ በጣጣጣምምምም የሚገርም ነበር በጣም ደስ ይላል በዛች ሰዓት አንድ ነገር ተመኘሁ ይሄን ሁሉ ህዝብ እዚሁ የዘወትር ተጠማቂ ቢሆንጰብዪ ተመኘሁ ! ምን አለ ለዚህ አመት ጠብቆ ለሚጠመቅ ህዝብ ጷጉሜ ረዘም ብትይ ምን አለ ብዪ እየተመኘሁ ወደ ቤቴ ሄድኩ እናም ሕዝቡ ለካ አለ የሥራ ጉዳይ የቤተሰብ ጉዳይ ወዘተ ይዞት እንጂ ህዝቡማ አለ በሉ ተጠመቁ በርቱ
መልካም ጥምቀት