Get Mystery Box with random crypto!

በቀል የእግዚአብሔር ነው! እግዚአብሔር ለበዳዮች ብቻ ያለ ይመስላቸዋል ለተበዳዮች እግዚአብሔር | ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

በቀል የእግዚአብሔር ነው!

እግዚአብሔር ለበዳዮች ብቻ ያለ ይመስላቸዋል ለተበዳዮች እግዚአብሔር ያሌለ ይመስላቸዋል ለዛም ነው በዳዮች ያለ ፍርሐተ እግዚአብሔር ሰውን የሚበድሉት ግን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ እኩል ነው የሚበድለውንም ይወደዋል የሚበደለውንም ይወደዋል ሲጀመር እግዚአብሔር ማንኛውንም የሰው ልጅ ጥቁር ነጭ ሳይል አጭር እረጅም ሳይል ቆንጆ አስቀያሚ ሳይል ወፍራም ቀጭን ሳይል ንጹህ ቆሻሻ ሳይል ሴት ወንድ ሳይል በፍጹም ፍቅር ይወደናል! እግዚአብሔር የሚጠላው ኃጢያትን ነው! ስለዚህ የምትበድሉ ሰውች ለተበዳዮችም እግዚአብሔር እንዳለ እወቁ ለተበዳዮች የሚበቀልላቸው እርሱ እግዚአብሔር ነው! ለተቸገሩት የሚሠጣቸው እግዚአብሔር ነው! አንተ በድለህ ላስለቀስካቸው የሚያጽናናቸው እግዚአብሔር ነው! እና አንተ ስትበድል የበደልህን መልስ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደምታገኝ ማወቅ አለብህ! በቀልን የሚበቀል ለተበዳዮች የሚበቀልላቸው እግዚአብሔር ነው! አንተ ደግሞ በዳይም ብትሆን የእግዚአብሔርን በቀል ስለማትችለው አትበድል ይቅርብህ ሰውን አታስለቅስ አታሳዝን!

ተበዳዮችም ደግሞ ወደ እግዚአብሔር አልቅሱ ለምኑ እንጂ ወደ ሰው አትሂዱ ሰው ምንም ሊያደርግላቹ አይችልም! እግዚአብሔር ግን እንደ ዋጋው የዘራውን ያሳጭድላቹሃል እግዚአብሔር ይበቀልላቹሃል!ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር አመልክቱ!!!

በቀል የእግዚአብሔር ነው!
ዲ/ን አቤል (ፍቅረ አብ)
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን Tube
https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw


@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   
@seratebtkrstian   

     join
#ሼርርርርርርርርርርር