Get Mystery Box with random crypto!

ስለቆቦ ከተማ! “እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የቆቦ ከተማና አካባቢው እስከ አሁኗ ስአት ድረስ በጠ | ሴራ ታሪክ እና ምርምር

ስለቆቦ ከተማ!

“እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የቆቦ ከተማና አካባቢው እስከ አሁኗ ስአት ድረስ በጠላት ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው። አንዳንድ ወገኖችና የማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች የወገን ጦር ቆቦ ገብቷል በማለት የሚሰጡት መረጃ ትክክል አይደለም። ይህም ሆኖ የወገን ጦር በቆቦና አካባቢው እየወሰደው ባለው የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ አማካኝነት ቆቦ ከተማ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነጻ ሊወጣ እንደሚችል ይታመናል።”

- ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ እንደገለፀው!

“በቆቦ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁኃን በሕወሓት ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ!

በቆቦ ከተማ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁኃን በሕወሓት ታጣቂዎች መገደላቸውን በስፍራው የሚገኙ ምንጮች ገልፀዋል። እስካሁን የሟቾቹን አስከሬን ማንሳት እንዳልተቻለም የአይን እማኞቻችን አረጋግጠዋል።ቆቦ ከተማ እስካሁን በሕወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ስትሆን ነዋሪዎቿ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ለአማራ ድምፅ አረጋግጠዋል። ታጣቂዎች ቤት ለቤት እየዞሩ በርካታ ንጹኃንን ፋኖ እና ሚሊሻ ናችሁ በሚል ጎዳና ላይ አውጥተው እንደረሸኗቸው የአይን እማኞቹ አረጋግጠዋል።”

- ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ እንደገለፀው