2022-04-07 10:00:15
መጋቢት 29
እመቤታችን ድንግል ማርያም አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግልና የፀነሰችበት ዕለት ነው!!!
ስንክሳር ዘኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን
ይህች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት። በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች።
በዚህች ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር
፩.ሰማይና ምድርን ፈጠረ።
(ዘፍ. ፩፥፩)
፪.በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ (ተጸነሰ)። በዓሉም "በዓለ ትስብእት" ይባላል። "አምላክ ሰው፣ ሰው አምላክ የሆነበት" ማለት ነው።
(ሉቃ. ፩፥፳፮)
፫.የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ።
(ማቴ. ፳፰፥፩ ፣ ማር. ፲፮፥፩ ፣ ሉቃ. ፳፬፥፩ ፣ ዮሐ. ፳፥፩)
፬.ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚህች ቀን ይመጣል።
(ማቴ. ፳፬፥፩)
በእነዚህ ታላላቅና ድርብርብ በዓላት ምክንያት ቀኑ "ርዕሰ በዓላት" (የበዓላት ራስ)፣ "በኩረ በዓላት" እየተባለም ይጠራል።
ቸሩ እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ፣ ከጽንሰቱ፣ ልደቱና ትንሣኤው በረከትን ይክፈለን። በጌትነቱም ሲመጣ በርኅራኄው ያስበን።
2.3K views07:00