Get Mystery Box with random crypto!

SEMAY MULTIMEDIA/ ሰማይ መልቲሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ semaymultimedia21 — SEMAY MULTIMEDIA/ ሰማይ መልቲሚዲያ S
የቴሌግራም ቻናል አርማ semaymultimedia21 — SEMAY MULTIMEDIA/ ሰማይ መልቲሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @semaymultimedia21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 500
የሰርጥ መግለጫ

በማህበረሰብ ንቃተህሊና ማዳበር ላይ በማተኮር የሰዎችን አመለካከትና የአስተሳሰብ አድማስ ማስፋትና ሰዎችን ወደንባብ በማምጣት ያገኙትን እውቀት በሚዛናዊነት ለራስም ሆነ ለማህበረሰብ ብልጽግና እንዲያውሉት ማስቻል ነው።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-03 23:38:23
አሌክሳንደር ዱማስ ፔሬ : The Father of Plot
-----
ብዕር የትልም ጥግ የነካ እለት ዱማስን ያክላል ይባልለታል ። ፈረንሳዊው ደራሲ አሌክሳንደር ዱማስ ለሳምንታዊ ጋዜጣ የትረካ አምድ ስር ይውሉ ዘንድ ይፅፋቸው የነበሩ ተከታታይ ታሪኮች በአለም ደግመው ደጋግመው ከተሸጡና ከተነበቡ ስራዎች መካከል ዳጎስ ብሎ የሚታይ መፅሃፍ እንዲወጣቸው ሆነ።
መፅሃፉ The Count of Monte Cristo ይሰኛል። ”ፈረንሳይ ውስጥ በነበረው የፓለቲካ ሽግግር ሳቢያ ሁነቱ ሰለባ ስላደረገው ወጣት መርከበኛ ይተርካል። ወቅቱ ናፖሊዮ እና ሊዊ 16 ኛ ያልረገበ ውጊያ የሚያካሂዱበትና መንበር ለመለዋወጥ የተፋለሙበት ጊዜ ነበር። ይህን ደራሲው ለመፅሃፉ እንደ መቼት የተጠቀመው ሲሆን እልፍ ገፀባህሪያትን በመመስረት ታሪኩን አሰናስሎ ይጓዛል።

ዱማስ እጅግ በርካታ የመድረክ ትያትሮችንም ፅፏል። የዚህ ጥቁር ደራሲ መጽሀፍት ስነጽሁፋዊ ውበት ያስደመማቸውና እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያስጫናቸው ፈረንሳውያን ዘረኞቹ ነጮች "ጥቁርነቱን አስረሳን" እያሉ በምፀት በማሞካሸት ጥበቡን ከዘራቸው የምትቀዳ ለማስመሰል ጥረዋል።
“እፎይታ” በሚል ስያሜ ተሾመ ዳምጤ ወደ አማርኛ ግሩም አድርጎ መልሶታል።
በሆሊውድ መንደር ፊልምም ተሰርቶለታል።

ከ20+ በላይ መፅሃፍትን ያበረከተው አሌክሳንደር ዱማስ ፔሬ በ1802 ፈረንሳይ ውስጥ የተወለደ ሲሆን በ68 ዓመቱ በ1870 እዚያው ፈረንሳይ ውስጥ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል |
88 views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:49:54
share!
112 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 21:48:00
199 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 09:20:44
ተወደደም ፣ ተጠላም እውቀት የአንድ ሀገር ህልውና ማስቀጠያ ሀዲድ ነው ። ያለ እውቀት መኖር ፣ ያለ ጥበብ መኖር ኋላ ቀር ትውልድ እንዲፈጠር ያደርጋል።
''እውቀት ቦንብ ይፈጥራል ፣ ጥበብ ደግሞ መቼ መጠቀም እንዳለብን ይነግረናል '' እንደሚባለው
እውቀትን ከጥበብ ጋር አዳብለን መርሃችንን ፣ መመርያችንን ፣ ማነፀርያችንን ማስተካከል አለብን። የአለማችንን ታሪክ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ብዙ ትምህርት ማግኘት እንችላለን። ዛሬ ዛሬ አጥብቀን ምንከጅላቸው ሀገሮች የታሪክ ዳራቸውን ብንመለከት እውቀትን ገንዘብ ያደረጉ ሀገሮች ናቸው። ብዙ የሥልጣኔ ማማ ላይ የወጡ ሀገራት በትሩን ያስጨበጣቸው እውቀት መር የሆነ አቅዋም አሊያም ፖሊሲ ስላላቸው ነው። አለም የተራቀቀችው ፣ የመሰጠረችው ፣ የተዋበችው በእውቀት ነው። እውቀት ደሞ የሚገኘው አንድም ከንባብ ነው፡፡ በማንበብ ያልዳበረ ሰው አዲስ ሀሳብ አይኖረውም፡፡
ባላነበብን ቁጥር የማሰብ አቅማችንን ያሽመድምዳል። አእምሮ ደግሞ ያለ እውቀት ሲመራ ስንፍናና ቸልተኝነት ይነግሳል። እንደ ህዝብ የሰከነ ፣ የለዘበ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የአስተሳሰብ አድማሱ የተቃኘ ፣ ሥራ ወዳድ ፣ ሀገር ወዳድ ፣ ጠያቂ ፣ መርማሪ ፣ አሰላሳይ ፣ ለሚያምነው እምነት ታማኝ የሆነ ፣ ጨዋ ማህበረሰብ ባህሉን የሚያውቅ ፣ ታሪኩን በጥንቃቄ ሚመረምር ድንቅ ትውልድ መፍጠር የውዴታ ግዴታችን ነው።
ተፅዕኖ ፈጣሪ ማንነትን ለመላበስና የተዋበ ስብዕና ባለቤት ለመሆን የንባብ ባህላችንን እናዳብር፡
ሁሉን አይነት መፅሀፍት በልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል፡፡
https://t.me/EYOBBOOKZONE
196 viewsedited  06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 03:32:11 ሴት ክዋክብት
ሜሪል ስትሪፕ በወጣትነቷ ለአንድ ፊልም ኦዲሽን ስታደርግ ካስቲንግ ዳይሬክተሩ በጣልያንኛ ለረዳቱ "ይቺን አስቀያሚ ደግሞ ከየት ነው ያመጣህብኝ?" ብሎ ይገስፀዋል። ሁለቱም የማያውቁት ሜሪል ጣልያንኛ አቀላጥፋ እንደምትናገር ነው። ሜሪል ያንን ሰምታ ተነስታ ወጣች። ታላቅ ተዋናይት ከመሆን የሚያግዳት ግን አልነበረም። ሜሪል በጣም የተራራቁ ገፀባህሪያትን፣ እጅግ የተለያዩ ስብእናዎችን ሁሉንም በብቃት ተጫውታለች። የሶስት ኦስካር ባለቤት ናት።
• ስካርሌት ጆሃንሰን በሆሊውድ ውስጥ የቁንጅና መለኪያ ተደርጋ የምትወሰድ ተዋናይ ናት። ምክንያቱም ፊቷ perfect symmetry አለው። የቀኝ ፊቷ እና የግራ ፊቷ እርስ በእርስ ፍፁም የመስታወት ምስል ናቸው።
• ኬት ዊንስሌት ታይታኒክ ላይ የሮዝን ገፀባህሪ ከተጫወተች በኋላ ዝነኛ ሆናለች። የፊልም ሃያስያን ወፍራም በመሆኗ የፊልም ተዋናይት መሆን አትችልም ቢሉም በስራዋ ሃሳባቸውን ውድቅ አድርጋለች።
• ጄኒፈር ኮኔሊ በውበትም በትወናም የተዋጣለት ተዋናይት ናት።
• ናታሊ ፖርትማን ገና ከለጋነቷ ወደ ሆሊውድ ገብታ ዝነኛ ተዋናይ ብትሆንም ከዝነኝነት ብልህነት ይበልጥብኛል ብላ ትምህርቷን ዩኒቨርስቲ ድረስ ተከታትላ በስነልቡና በማእረግ ተመርቃለች።
• ጁዲ ዴንች ለትወና ጥበቧ "ዴም" የተሰኘው ታላቅ ማእረግ ተሰጥቷታል።
• ሂላሪ ስዋንክ በግሩም የትወና ብቃቷ ሁለት ኦስካር አሸንፋለች።
• ማሪየን ኮቲላርድ የፈረንሳይ ኩራት የአለም ሃብት ናት።
• ጄኒፈር ሎረንስ ገና በ16 አመቷ በረዳት ተዋናይነት በ23 አመቷ በዋና ተዋናይነት ኦስካር አሸንፋለች።
• ዉፒ ጎልድበርግ ከባባድ ገፀባህሪዎችን በብቃት በመወጣት የተሳካላት ናት።
• ኡማ ተርማን በኩዊንቲን ታራንቲኖ አንደበት እንዲህ ትገለፃለች ፦ "ኡማ የጥበብ አማልክቴ ናት"
• ጆዲ ፎስተር ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገን ላይ የግድያ ሙከራ እንዲደረግ ምክንያት የሆነች ተዋናይት ነች። አንዱ loser የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ስላልተቀበለችው ታዋቂ ስላልሆንኩ ነው ብሎ ደምድሞ ሬገንን ለመግደል በመሞከር ታዋቂ ለመሆን ጥሯል። ጋዜጠኞችም በዚህ ምክንያት ጆዲ ፎስተርን መቆሚያ መቀመጫ ቢያሳጧት "ያለጥፋቴ ለምን?! ብላለች።
174 views00:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 08:58:15 የሚያነቡ ሰዎች . . .
1. ካለማቋረጥ ራሳቸውን ያሻሽላሉ
2. ጊዜያቸውን በተራ ነገር ከማሳለፍ ይጠበቃሉ
3. ጸሃፊዎቹ ብዙ ጊዜ ወስደው በልምምድና በጥናት ያገኙትን እውቀት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይቀስማሉ
4. አእምሯቸው በንባብ ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ስለሚል ለተራ ወሬና ለወረዱ ነገሮች ጊዜውም ሆነ ፍላጎቱ አይኖራቸውም
5. የውስጥ እርካታና መረጋጋትን ያዳብራሉ
አንብቡ ! እደጉ ! ተለወጡ !
ከተራውና ከማይጠቅማችሁ ወሬ ውጡ ! በሃገራችንም ሆነ በውጪ ሃገር ሰዎች የተጻፉ መልካም ነገር የያዙ መጽሐፎችን እየመረጣቹ አንብቡ ።
Dr . Eyob Mamo
332 views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 02:51:02 ይህ ታላቅ ጸሐፊ እና ሐያሲ'አልበርት ቺንዋሉሞጉ አቼቤ' የሚል ስም ተሰጥቶት፤ እ.ኤ.አ 1930 ዓ.ም ላይ በምሥራቂቷ ናይጄሪያ ኢግቦ አውራጃ ተወልደ፡፡ በልጅነቱ በትምህርቱ ፈጣን እና ብርቱ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ በመምህራኑ ዘንድ የተወደደ እና የተመሰገነ ለመሆን በቃ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀም፤ ብዙዎች ለፈጣን እና ብርቱ ተማሪዎች የሚመኙትን ሕክምና እንዲያጠና ነጻ የትምህርት እድል ደርሶት ወደ ዩኒቨርሲቲ ቢሄድም፤ እርሱ ግን በሥነጽሑፍ ተማርኮ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ ለማጥናት ወሰነ፡፡ በዚህ ውሳኔው ነጻ የትምህርት እዱሉን ቢያጣም፥ በራሱ ጥረት እና በወንድሙ እገዛ ወጪውን እየሸፈነ በአሁኑ ኢባዳን ዩኒቨርሲቲም ገብቶ የእንግሊዝኛ ቋንቋን እና ሥነ-ጽሑፍን ተማረ፡፡ ከዚያም በኋላ የተወሰነ ጊዜ በማስተማር ካሳለፈ በኋላ በናይጄሪያ የብሮድካስት ተቋም ውስጥ ገብቶ በኃላፊነት አገልግሏል፡፡
ቺኑዋ አቼቤ የልብወለድ ሥራዎችን መድረስ የጀመረው ገና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለ ነበር፡፡ በተለይም አፍሪቃዊ የሆኑ ባህሎችን እና እምነቶችን በከፍተኛ ትኩረት ያጠና ስለነበር፤ የልብወለዶቹም ትኩረት ከእዚህ ብዙም የራቀ አልነበረም፡፡ እስከዛሬ ድረስ የሚጠቀስለት ስራው “Things Fall Apart” ሲሆን፤ በዓለም ደረጃ በብዙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለማስተማሪያነት ይውላል፡፡ መጽሐፉ ቅኝ ገዢዎች የራሳቸውን ባህልና ቋንቋ ይዘው ሲመጡ ከአፍሪቃዊ ባህል ጋር የሚፈጥረውን ግጭት እና መዘዞቹን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ቺንዋ አቼቤ ከዚህ መጽሐፉ በኃላ ብዙ መጽሐፍት፣ ግጥሞች እንዲያውም አጫጭር ሞጋች ጽሑፎችን ደርሷል፡፡ የአፍሪቃን ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ከቀየሩ ሰዎች መካከልም በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ይህ ታላቅ ጸሐፊ በ1990ዎቹ ውስጥ በገጠመው የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች ፓራላይዝድ ሆነ፡፡ ቀሪውን ሕይወቱንም በዊልቼር እየተንቀሳቀሰ ለመኖር ተገደደ፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ የሚበገር አልነበረም፡፡ ይህ ከተከሰተ በኋላ እንኳን በባርድ እና በእውቁ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የአፍሪቃ ጥናት ፕሮፌሰር በመሆን ለሃያ ዓመታት ያህል አስተምሯል፡፡ ይህ ጸሐፊ በሥራዎቹ ምክንያት ከሠላሳ በላይ የሆኑ ዓለምአቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ያገኘ ሲሆን፤ እውቅ የሆኑና ለሥነ-ጽሑፍ ባለሞያዎች የሚሸለሙ ሽልማቶችን ለማግኘት ችሏል፡፡ የአራት ልጆች አባት የሆነው የአፍሪቃ ኩራት ቺንዋ አቼቤ 2013 ላይ በሰማኒያ ሁለት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
245 views23:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 02:50:35
ቺንዋ አቼቤ: ተዓምረኛው ብዕረኛ
በአፍሪቃ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ እንደ እንቁ ካበሩ ሰዎች መካከል ይጠቀሳል - ቺንዋ አቼቤ፡፡ በቋንቋ አጠቃቀሙ የሚራቀቅ፣ አፍሪቃዊ ባህልና ትውፊትንም አብዝቶ በሥራዎቹ ውስጥ የሚጠቀም ከመሆኑ ባሻገር፤ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ድርሰቶችን እና ግጥሞችን በመጻፍ የአፍሪቃን ባህል ለዓለም ለማስተዋወቅ ችሏል፡፡ በዛሬው የታዋቂ ሰው ገፃችን- ታዋቂውን ናይጄሪያዊ ጸሐፊ፣ ገጣሚ እና ሐያሲ ቺንዋ አቼቤ በጥቂቱ እንዳስሳለን፡፡
192 views23:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 15:46:11 ከሀብታም ቤተሰብ የተገኘና በወጣትነት ጊዜ ለትምህርት ወደ ሮም ሄዶ የነበር, ግሪክን የጎበኘ፤ በዳኝነት ውስጥ ጥቂት ስራዎችን የሰራ, ወደ ህዝባዊ ህይወት ውስጥ ላለመግባት የወሰነ እና ከዚያ ይልቅ ገጣሚ ለመሆን የወሰነና በጣም የተዋጣለት ገጣሚ የሆነ ሰው ነው::
ኦቪድ በአውግስጦስ ዘመን የኖረ ሮማዊ ገጣሚ ነበር። እሱ ብዙውን ጊዜ ከሦስቱ ቀኖናዊ ባለቅኔዎች የላቲን ሥነ-ጽሑፍ ገጣሚዎች አንዱ ሆኖ ከሚመረጠው የአሮጌው ቨርጂል እና ሆራስ ዘመን ነበር።
ሜታሞርፎሲስንና (Metamorphosis) የፍቅር ጥበብ (The Art of Love)ን የመሳሰሉ ፅሁፎችን በቅኔ የፃፈው ይህ ባለቅኔ ፣ ገጣሚና ፈላስፋ የጥንት ሮማውያን ለመቶዎች አመታት በዓለም ላይ በሀያልነት ሲቆዩ ካፈሯቸው በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ታላላቅ ሰዎች ሆኖ በታሪክ ሲሰፍር ፅሁፎቹ አሁንም ድረስ እንደ አዲስ ይነበባሉ ፡፡ ይህ ገጣሚ፣ በአብዛኛው ስማቸው በደግ ከማይነሳው እንደ ኔሮና ካሊጉላን ከመሳሰሉት ሮማውያን ነገስታት ይልቅ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል ፡፡
የኢምፔሪያል ምሁር የነበረው ኩዊቲሊያን ኦቪድን የላቲን የፍቅር ልሂቃን የመጨረሻው እንደሆነ ገልጿል። በህይወት በነበረበት ጊዜ ከፍተኛ ተወዳጅነት ነበረው:: (ንጉሠ ነገሥት) አውግስጦስ ራሱ ማስታወቂያን አውጥቶ ኦቪድን በግዞት ወደ ቶሚስ - በዘመናዊቷ ሩማንያ በጥቁር ባህር ውስጥ ወደሚገኝ ቦታ -አባሮት ነበር።
በጣም አስከፊ ነበር። ኦቪድ በግዞት ተወስዷል ፤ መጽሃፎቹም ታገዱ። ይህ ለምን እንደተከሰተ ግን ማንም አያውቅም: ያለው ብቸኛ ማስረጃ ኦቪድ ራሱ ግዞቱን በካርመን እና ስህተት ("ግጥም እና ስህተት") በሚለው ስራው ገልጿል። ዝርዝር ጉዳዮችን ለመግለፅ ፈቃደኛ አለመሆኑ በምሁራን ዘንድ ብዙ ግምቶችን አስከትሏል። ኦቪድ በግዞት ከሄደበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሮም ተመልሶ አያውቅም። ቀሪ ህይወቱን ወደ ቤቱ ለመመለስ እንዲፈቀድለት የሚለምን ደብዳቤ በመጻፍ አሳልፏል። ሰሚና ምላሽ ግን አላገኘም፡፡ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በቶሚስ ውስጥ ሞተ፡፡
224 viewsedited  12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 15:45:59
በዓለም ታሪክ ውስጥ ግለሰብ ሰዎች ለዓለም ያደረጉት አበርክቶ ለክፍለ ዘመናት ህልውና ከነበራቸው ታላላቅ ኢምፓየሮችና ነገስታት ካደረጉት በብዙ እጥፍ ይበልጣል ፡፡ ለምሳሌ ከግሪክ ስልጣኔ እና ኢምፓየር ይልቅ ታላላቆቹ የግሪክ ፈላስፎች በዘመናቸው ለሰው ልጅ ያበረከቱት ይልቃል ፡፡ ግሪክን ከሚያክል ስልጣኔ ይልቅ በተደጋጋሚ ስማቸው የሚነሳው ፕሌቶ፣አሪስቶትል እና ሶቅራጥስ እና መሰል የግሪክ ፈላፋዎች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡
በዚህም በአንድ ዘመን ወይም በጥቂት ክፍለ ዘመናት ውስጥ ተነስተው ገነው ከዚያም ከሚደበዝዙት ኢምፓየሮችና ማንም የሚያስታውሳቸው ከማይኖረው ነገስታት እና ስልጣኔዎች ይልቅ ዘመንና ጊዜን ፣ ትውልድን ቋንቋን መሻገር የሚችለው እውቀትና ሃሳብ እንዲሁም የዚሁ እውቀት ጥበብና ሃሳብ ባለቤቶች ፈላፎችና ገጣሚዎች፣ደራሲዎች፣ሰአሊዎች ይበልጣሉ ፡፡
ዛሬ የማስተዋውቀው ኦቪድ የተባለውንና ጁሊየስ ቄሳር በተገደለ በ43 ዓ.ዓ. የተወለደውን ሮማዊ ገጣሚ ነው።
189 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ