Get Mystery Box with random crypto!

የደም ግፊት ክፍል አንድ የደም ግፊት ማለት ደም በሰዉነትዎ ዉስጥ ባሉ የደም ቅዳ የደም ቧንቧዎ | ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

የደም ግፊት

ክፍል አንድ
የደም ግፊት ማለት ደም በሰዉነትዎ ዉስጥ ባሉ የደም ቅዳ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ በሚያሳድረዉ ግፊት አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን የደም ግፊትዎ ከልኬቱ በላይ ሲጨምር አንድ ሰዉ የደም ግፊት አለዉ እንላለን።

ከደም ግፊት እዉነታዎች ዉስጥ
አንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ 46 በመቶ የሚሆኑት የደም ግፊት ያለባቸው ጎልማሶች በሽታው እንዳለባቸው አያውቁም

የደም ግፊት የልብ፣ የአንጎል፣ የኩላሊትና የሌሎች በሽታዎችን ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምር ከባድ የጤና እክል ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ የደም ግፊት ሰዎች ያለጊዜያቸዉ ( የለዕድሜያቸዉ) ለሞት የሚዳርግ ዋነኛ የሞት መንስኤ ነው።

የደም ግፊት በሁለት ቁጥሮች የሚገለፅ ሲሆን የላይኛዉ ቁጥር( ልኬት) ሲስቶሊክ ሲሆን ይህም የሚወክለዉ ልብ በሚመታበት ጊዜ( ደም በምትረጭበት ወቅት በደም ሥሮች ውስጥ ያለውን ግፊት ይወክላል። የታችኛዉ ደግሞ ዲያስቶሊክ የሚባል ሲሆን የሚያመለክተዉ ደግሞ ልብ በምት መካከል እረፍት በምታደርግበት ወቅት በደም ቧንቧዎች ዉስጥ ያለዉን የግፊት መጠን ነዉ።

አንድ ሰዉ የደም ግፊት የለበትም የሚባለዉ የላይኛዉ ከ120 ሚሜ ሜርኩሪና ከዚያ በታች እንዲሁም የታችኛዉ ደግሞ ከ80ሚሜ ሜርኩሪና ከዚያ በታች ሲሆን ነዉ።

አንድ ሰዉ የደም ግፊት አለበት የሚባለዉ መቼ ነዉ?

በሁለት የተለያዩ ቀናት ሲለካ በሁለቱም ቀናት የላይኛዉ (ሲስቶሊክ) የደም ግፊት ልኬት ወይም መጠን 140 ሚሜ ሜርኩሪና ከዚያ በላይ ሲሆን እና ወይም በሁለቱም ቀናት የዲያስክቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ90 ሚሜ ሜሪኩሪና ከዚያ በላይ ሲሆን ያ ሰዉ የደም ግፊት መጠን መጨመር አለዉ እንላለን።

የ Facebook ገጻችን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/