Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

የቴሌግራም ቻናል አርማ seltena — ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉
የቴሌግራም ቻናል አርማ seltena — ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉
የሰርጥ አድራሻ: @seltena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.68K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ ስለ ጤና ጉዳዮች የምናስተምርበት ቻናል ነው። አብረን እንቆይ !
በዚህ ቻናል- ስለ
👉አካላዊ ና ሰነ-ልቦናዊ የጤና እክሎች እና መፍትሄዎቻቸው በዝርዝር በጤና ባለሞያዎች ይዳሰሳል። ️
👉አዳዲስ የጤና ሳይንስ መረጃዎች ይቀርባሉ::
👉እንዲሁም በቀረቡ መረጃዎች ላይ ተጨማሪ ጥያቄ ካለ በጤና ጥያቄ ና መልስ ግሩፕ ላይ እወያያለን! ይምጡ ይቀላቀሉን ይወዱታል!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-25 00:03:58 ጥያቄ:- የማህፀን በር 'ቅደመ ካንሰር' ምልክቶችን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
መልስ :-
ሰላም!!
የማህፀን በር ካንሰር(cervical cancer) ሁሉት አይነት የደረጃ መገለጫዎች አሉት : ቅደመ ካንሰር ደረጃ እና ከፍተኛ ደረጃ::
ቅደመ ካንሰር ብዙ ጊዜ ምልክት የለውም :: የሚታወቀው ፓፕ ስሜር በሚባል የማሃፀን ምርመራ አይነት ነው:: ብዙ ጊዜ በ20 ዎቹ መጨረሻ እና በ30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ በምርመራ የሚታይ ሲሆን ÷ ከፍተኛ የካንሰርነት ደረጃ ደግሞ በአብዛኛው ከ45- 50ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ ከምልክቶች ጋር ይታያል!

#አጋላጭ #ሁኔታዎች
የማህፀን በር ቅደመ ካንሰር ና ካንሰር ደረጃ አጋላጭ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:-
1. በ'ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ'(HPV 16 &18) መጠቃት:- ይህ ቫይረስ 70% ለምጠጋ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መንስኤ ሲሆን የምተላለፈውም በልቅ ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው::
2. ከአንድ በላይ ሰዎች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ(በተለያየ ወቅትም ሊሆን ይቻላል)
3. ከሀያ ዓመት እድሜ በታች የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት
4. በለጋ እድሜ ልጅ መውለድ(ከ20 በታች)
5..በአባላዘር በሽታዎች መያዝ
6. በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተጠቁ ከሆነ ተጋላጭነት ይጨምራል
7. ሲጋራ(ወይም ትምባሆ) ማጨስ
አንዳንዴ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን መጠቀም (OCP) ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ ዕድል እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ::

#ከ ምልክቶች በጥቂቱ?
1. ለየት ያለ በማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ
2. ያለወትሮ ከፍተኛ የሆነ በማህፀን የደም መፍሰስ መታየት
3. ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ
4.ዳሌ አካባቢ እና የጀርባ ህመም ዋነኞቹ ናቸው::
#ማስታወሻ.1:- የዳሌ ህመም ÷ሽታ የለው የማህፀን ፈሳሽ ÷ ከእምብርት በታች የሆድ ህመም : የማህፀን ኢንፌክሽን (PID) ወይም የአባላዘር በሽታ ምልክት ሊሆን ይቻላል :: ስለዚህ ይህን ምልክቶች ለመለየት በቅርብ ያሉ ሕኪሞች ጋር ሄዶ መታየት ይገባል::
#ማስታወሻ.2.
የማህፀን በር ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ #ምንም ምልክት ሳያሳይ በቅደም ካንሰርነት ደረጃ እስከ 10ዓመት ሊቆይ ይቻላል :: አንዳንዴ የሰውነት "በሽታ የመከላከል" አቅም ከተዳከመ ከዚህ ባጠረ ጊዜ ምልክት ያሳያል::

ቅደመ ካንስርን #የማወቂያ #ብቸኛ መንገድ "#ፓፕ ስሜር" የተባለውን ምርመራ ማደረግ ነው::
እድሜቸው ከ21 ዓመት እስከ 65 ዓመት የሆኑ ሴቶች በየ 3 ዓመቱ ይህንን ምርመር ማደረጋቸው "የቅደመ ካንሰር" ምልክት መኖሩን ለማወቅ እንዲሁም ነገሩ ስይወሳሳብ እና አደገኛ ደረጃ ስይደርስ ለማከም ይረዳል::
ምርመራው በብዙ ሆስፒታሎች እንዲህም በአንዳድ የማህፅን ና ፅንስ ሰፔሻሊት ክሊኒኮች ይገኛል::
የዚህ ምርመራ ዋጋ ውድ አይደለም ስለዚህ እድሜያቸው ከ 21 እስከ 65 ዓመት የሆናቸው ሴቶች አገልግሎቱ በሚሰጥበት የጤና ተቋም በመሄድ እንዲመርመሩ ና የጤና ሁኔታቸው እንዲያውቁ #አበረታታለሁ::

መልካም ጊዜ::
ዳንኤል አበበ(MD)(ሲንየር ጠቅላላ ሀኪም)
748 viewsedited  21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 06:15:19 የተሻh ሰው መሆን የምትፈልግ ከሆነ፤

ጥቂት አውራ፤ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ፡፡
አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፤ ስራህ ላይ አተኩር።
ምርጥ የሰውነት አቋም ይኑርህ።
ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን፡፡
ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፤ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት፡፡
ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን ከመፍጠር ተቆጠብ።
ፀዳ በል፡፡ በደንብ ልበስ ፣ ፏ በል!
ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን።
አደርገለሁ ያልከውን ነገር አድርገዉ።
በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን።
ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ ብቻ መዝናቸዉ።
የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ስዉ ሁሉ አትኖገር።
ሰዉ ስለ አንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘ።
ኃላፊነት መዉስድን አትፍራ።
ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ።
የጎዱህነና ' ምንም የለዉም!' ብለ የራቁUነ ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ።
ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ 'ላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸል።

የተሻለ ሰው እንዲሆኑ ለሚፈልጓቸው ጓደኛዎ #ሼር ያድርጉላቸው።
1.1K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 12:56:24
ደም ግፊት
የህመም ምልክቶች

ክፍል ሁለት
ስለ የደም ግፊት ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት በጣም አደገኛ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የደም ግፊት እንዳለብዎ ላያውቁ ስለሚችሉ ነዉ። እንዲያውም የደም ግፊት ካለባቸው ሰዎች መካከል ወደ አንድ ሦስተኛ የሚጠጉት የደም ግፊት ህመም እንዳለባቸዉ አያውቁም። የደም ግፊትዎ መጨመሩንና አለመጨመሩን ለማወቅ ተመራጩ መንገድ መደበኛ የጤና ምርመራዎችን በተወሰነ ጊዜ ልዩነት በማድረግ ነው፤ በተለይ ከፍተኛ የደም ግፊት ያለው የቅርብ ዘመድ ካለዎት እርስዎም መደበኛ ክትትል ማድረግ ይገባዎታል።

የደም ግፊት "ዝምተኛ ገዳ" ይባላል። አብዛኛዎቹ የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች ምንም አይነት የህመም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ላይኖራቸው ስለሚችል ችግሩን እንዳለባቸዉ አያውቁም። እነርሱም
ጠዋት ጠዋት የራስ ምታት መከሰት
የልብ ምት መዛባት
የአይን ወይም እይታው ላይ ብዥ ማለት
መጨናነቅ
የደረት ላይ ህመም፣ የጡንቻዎች መንቀጥቀጥ( muscle tremors) ናቸዉ።
የደም ግፊት መጨመርን መቆጣጠር ካልቻሉ ሊያመጣዉ የሚለዉ የጎንዮሽ ጉዳቶች
ሌሎች ሊያመጣቸዉ ከሚችላቸዉ ችግሮች በተጨማሪ የደም ግፊት መጠን መጨመር በልብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
የደረት ላይ ህመም-- ይህም አንጃይና ይባላል
ድንገተኛ የልብ መጎዳት( Heart attack)፦ ይህ የሚከሰተዉ ወደ ልብ የሚጓዘዉ የደም ቧንቧ ሲዘጋና በኦክሲጂን እጥረት ምክንያት የልብ ጡንቻ ሴሎች ሲሞቱ ነዉ።
የልብ ድካም፦ የሚከሰተዉ ልብ በቂ ደምና ኦክሲጅን ወደ ሌሎች አስፈላጊ የሰውነት አካላት መርጨት ሲያቅታት ነዉ።
መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት መከሰት

የ Facebook ገጻችን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
981 views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 12:56:24
የደም ግፊት

ክፍል አንድ
የደም ግፊት ማለት ደም በሰዉነትዎ ዉስጥ ባሉ የደም ቅዳ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ በሚያሳድረዉ ግፊት አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን የደም ግፊትዎ ከልኬቱ በላይ ሲጨምር አንድ ሰዉ የደም ግፊት አለዉ እንላለን።

ከደም ግፊት እዉነታዎች ዉስጥ
አንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ 46 በመቶ የሚሆኑት የደም ግፊት ያለባቸው ጎልማሶች በሽታው እንዳለባቸው አያውቁም

የደም ግፊት የልብ፣ የአንጎል፣ የኩላሊትና የሌሎች በሽታዎችን ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምር ከባድ የጤና እክል ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ የደም ግፊት ሰዎች ያለጊዜያቸዉ ( የለዕድሜያቸዉ) ለሞት የሚዳርግ ዋነኛ የሞት መንስኤ ነው።

የደም ግፊት በሁለት ቁጥሮች የሚገለፅ ሲሆን የላይኛዉ ቁጥር( ልኬት) ሲስቶሊክ ሲሆን ይህም የሚወክለዉ ልብ በሚመታበት ጊዜ( ደም በምትረጭበት ወቅት በደም ሥሮች ውስጥ ያለውን ግፊት ይወክላል። የታችኛዉ ደግሞ ዲያስቶሊክ የሚባል ሲሆን የሚያመለክተዉ ደግሞ ልብ በምት መካከል እረፍት በምታደርግበት ወቅት በደም ቧንቧዎች ዉስጥ ያለዉን የግፊት መጠን ነዉ።

አንድ ሰዉ የደም ግፊት የለበትም የሚባለዉ የላይኛዉ ከ120 ሚሜ ሜርኩሪና ከዚያ በታች እንዲሁም የታችኛዉ ደግሞ ከ80ሚሜ ሜርኩሪና ከዚያ በታች ሲሆን ነዉ።

አንድ ሰዉ የደም ግፊት አለበት የሚባለዉ መቼ ነዉ?

በሁለት የተለያዩ ቀናት ሲለካ በሁለቱም ቀናት የላይኛዉ (ሲስቶሊክ) የደም ግፊት ልኬት ወይም መጠን 140 ሚሜ ሜርኩሪና ከዚያ በላይ ሲሆን እና ወይም በሁለቱም ቀናት የዲያስክቶሊክ የደም ግፊት መጠን ከ90 ሚሜ ሜሪኩሪና ከዚያ በላይ ሲሆን ያ ሰዉ የደም ግፊት መጠን መጨመር አለዉ እንላለን።

የ Facebook ገጻችን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
735 views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 19:39:03 የማጋነን/የመዋሸት ሱስ Mythomania
==========================
ውሸት በተለያየ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡ የሰዎችን ስሜት ላለመጉዳት ወይም ጨዋ ለመሆን በትናንሽ ጉዳይ ላይ የሚዋሽ ውሸት አለ፡፡ በእንግሊዘኛ white lie የሚባለው፡፡ አንዳንድ 'በስራው ፀባይ' ምክኒያት የሚመጣ ማጋነን/ውሸት አለ-እንደ ድለላ፣ ፓለቲካ አክቲቪስትነት በመሳሰሉት ስራዎች፡፡ የማጋነን/የመዋሸት ሱስ ከእነዚህ የሚለየው ከግለሰቡ እውቅና እና ቁጥጥር ውጭ የሆነ በመሆኑ በማናቸውም ሁኔታ ላይ የሚደረግ መሆኑ ነው፡፡
መንስኤ፦
ማይቶማኒያ ያለባቸው ሰዎች መረጃ የሚመዝነው የአእምሯቸው ክፍል ከሌሎች ሰዎች ደከም ያለ ሲሆን መረጃ የሚያመነጨው ክፍላቸው በተቃራኒው ከፍ ያለ ነው፡፡ ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶቹን በሚመለከት አንዳንዶቹ በልጅነት የነበሩበትን ጥሩ ያልሆነ ሁኔታን ለማምለጥ በምናብ የመሄድ አዝማሚያ ከፍ ብለውና ጥሩ ሁኔታ ውስጥም ሆነው ቀጥለውበት ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላኛው ተቀባይነትን ለማግኘትና የብቸኝነትን ስሜት ለመሸሽ ከግለሰቡ እውቅና ውጭ በውስጠኛው የአእምሮ ክፍል የሚወሰድ እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡
ምልክቶቹ፦
ማይቶማኒያ ያለባቸው ሰዎች ሳያጋንኑ ወይም ሳይዋሹ መናገር አይችሉም፡፡ በእነሱ አእምሮ ውስጥ ምናባዊውና እውነታው ስለተምታታ እየዋሹ እንደሆነ አይታወቃቸውም፡፡ ማይቶማኒያ በልጅነት የሚጀምር በመሆኑ የሚያጋንኑት/የሚዋሹት አሁን እየተካሄዱ ስላሉት ነገሮች ብቻ ሳይሆን ስለ የድሮ ትዝታዎች ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ማይቶማኒያ ካለበት አብሯደጋችሁ ጋር ስለ ትምህርት ቤት ብታወሩ እነሱ የሚተርኩት የተጋነነ/የተለየ በመሆኑ "እኔ ሌላ ትምህርት ቤት ነው እንዴ የተማርኩት?" ሊያስብሉ ይችላሉ፡፡
ማይቶማኒያ በራሱ የአእምሮ ህመም አይደለም ነገር ግን የሌሎች ህመሞች በተለይ የስብዕና ህመሞች (Personality disorders) ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ፈቃደኛ ሆነው የሚመጡ ከሆነ በአእምሮ ሀኪም ቢታዩ በተወሰነ መልኩ ሊረዳ የሚችል የንግግር ህክምና ሊሰጣቸው ይችላል፡፡
ሶስት ጓደኛሞች ሲያወሩ የመጀመሪያው "የኛ ቤት ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ቤታችን ውስጥ ትንሽ ሲኒማ ቤት አለን፡፡" አለ፡፡ ሁለተኛው "እኛም ቤታችን ውስጥ ሲኒማ ቤት አለ፡፡ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ የእግር ኳስ ሜዳ ያክላል፡፡" ሲል ሶስተኛው "የኛ ቤት ሲኒማ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ አሁን የተጣለ እንቁላል ከኃላ ብትወረውር መድረኩ ጋር እስኪደርስ ይፈለፈላል፡፡
የ1998 የኖብል የስነ ጽሁፍ ተሸላሚ ሆዜ ሳራማጎ "የሰው ልጅ በተለያዩ ዘመናት ውስጥ አልፏል- የድንጋይ ዘመን፣ የነሀስ ዘመን አሁን ደግሞ በቅርብ የውሸት ዘመን!"
መልካም ጊዜ!
#Via_ዶ/ር ዮናስ
1.3K viewsedited  16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 19:21:40 ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል pinned a photo
16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 19:04:12
#Patient_info

የማህፀን በር ካንሰር ምንድነው?
የማህፀን በር ካንሰር ሂውማን ፓፒሎማ በሚባል ቫይረስ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ይህ የካንሰር አይነት በዝግታ ስለሚስፋፋ የብዙ ሴቶችን ህይወት በቀላሉ ይቀጥፋል፡፡ ህመሙ ቀድሞ ከታወቀ ታክሞ መዳን የሚችል በሽታ ነው፡፡
የማህፀን በር ካንሰር መንስኤዎች
• ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ
• በለጋነት እድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት መጀመር
• በአባላዘር በሽታዎች መያዝ
የማህፀን በር ካንሰር ምልክቶች
የማህፀን በር ካንሰር ምልክት ሳያሳይ ብዙ ሊቆይ ይችላል ህምሙ ከተባባሰ በኃላ የሚታዩ ምልክቶች
• የግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ ከማህፀን የደም መፍሰስ
• ያልተለደመ የማህፀን ፈሳሽ
• የማህፀን አካባቢ ህመም
• የግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት መኖር
የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ መንገዶች
• በለጋነት እድሜ የግብረ ስጋ ግንኙነት አለመፈፀም
• አንድ ለአንድ መወሰን
• ኮንዶም በአግባቡ መጠቀም
• የአባላዘር በሽታዎችን መከላከል
• በየአምስት አመቱ አንድ ጊዜ ምርመራ ማድረግና የቅድመ ካንሰርን መለየትና ማከም
• እድሜያቸው 9-12 ያሉ ሕፃናት ቅድመ መከላከል ክትባት መከተብ
#ወደ ጤና ተቋም #በመሄድ #የቅድመ ካንሰር ምርመራ ያድርጉ!!!


@seltena
1.3K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 17:49:30 #ስትሮክ
የደም ቧንቧ መፈንዳት ምክንያት የሚከሰት ስትሮክ (ሄሞራጂክ ስትሮክ)

ክፍል ሁለት
ሄሞራጂክ ስትሮክ የሚከሰተው በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ሥር ሲፈዳና አኡአንጎል ዉስጥ ደም ሲፈስ ነዉ። የአንጎል ደም መፍሰስና በደም ሥሮች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ብዙ ሁኔታዎች አሉ።

ከሄሞራጂክ ስትሮክ ጋር የተያያዙ ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
ቁጥጥር ያልተደረገበት ከፍተኛ የደም ግፊት( Uncontrolled high blood pressure)
የደም ማቅጠኛ መድሃኒት ወስደሁ ደም ከመጠን በላይ እንዲቀጥን ማድረግ
የደም ቧንቧ ችግሮች( በተፈጥሮ የደም ስር ግድግዳ መላላት ሲኖር --አንዩሪዝም)
አደጋ( ለምሳሌ የመኪና አደጋ)
የፕሮቲን በደም ቧንቧ ዉስጥ መጠራቀምና የደም ቧንቧ ግድግዳዎች አንዲላሉ ማድረግ( አሚሎይዶሲስ)
በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ፍሰት በጊዜያዊነት ብቻ መስተጓጎል ሲኖር
አንዳንዴ ሚኒስትሮክ ይባላል። ይህም የስትሮክ ምልክቶች ለተወሰነ ሰዓታት ታይቶ መጥፋት ሲሆን ችግሮቹም ዘላቂ ጉዳት አያመጡም። ይህ ችግር የሚከሰተዉ ወደ በተወሰነ የአንጎል ክፍል የደም ዝዉዉር ወይም ፍሰት በግዜያዊነት ሲቀንስ ነዉ።

አጋላጭ ምክንያቶች
የአኗኗር ዘይቤ አጋላጭ ምክንያቶች
የሰዉነት ክብደት መጠን ከፍተኛ መሆን
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
ከመጠን በላይ መጠጥ የሚጠጡ( binge drinking)
አንደ ኮኬይን ያሉ ህገወጥ አደንዛዥ መድሃኒቶችን የሚወስዱ
ከህመም ጋር የተያያዙ አጋላጭ ምክንያቶች
ከፍተኛ የደም ግፊት
ሲጋራ ማጨስ(ከሚያጨሱ ሰዎች ጋር ያሉትን ይጨምራል-- secondhand smoke exposure)
ከፍተኛ የደም ኮሌስትሮል( ስብ ) መጠን
የስኳር ህመም
የእንቅልፍ ችግር( ኦብስትራክቲቭ ስሊፕ አፕኒያ)
የልብና ደም ቧንቧ በሽታዎች፦ የልብ ድካም፣ የልብ ኢንፌክሽን፣ የልብ ምት መዛባት ችግሮች( ፊብሪሌሽን)
ከዚህ በፊት በራስዎ ወይም በቤተሰብዎ ዉስጥ ስትሮክ መከሰት፣ድንገታዊ የልብ ችግር አሊያም በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ፍሰት በጊዜያዊነት ብቻ መስተጓጎል ችግር ከዚህ በፊት መኖር
የኮቪድ 19 ኢንፌክሽን ናቸዉ።
ከፍ ያለ የስትሮክ አደጋ ጋር የተያያዙ ሌሎች ነገሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
እድሜ፦ ዕድሜያቸው ከ55 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ለስትሮክ የመጋለጥ እድላቸው ከወጣቶች የበለጠ ነው።
ፆታ፦ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ለስትሮክ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
ሆርሞን፦ ኢስትሮጅን ያላቸዉ የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ወይም የሆርሞን ህክምናዎች መጠቀም ታጋላጭነትን ይጨምራል።
ዘር ወይም ጎሳ፦ አፍሪካ አሜሪካውያን ና ስፓኒሾች ከሌሎች ዘሮች ወይም ጎሳዎች ይልቅ የበለጠ ለስትሮክ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ

https://www.sturaelclinic.com/
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
https://sturaelclinic@gmail.com
999 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 22:23:59 ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል pinned «ስትሮክ ክፍል አንድ ስትሮክ በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በሚስተጓጎልበት ወቅት የአንጎል ሴሎች(ሕዋሶች) እንዲሞቱ የሚያደርግ የጤና እክል ነው። ሁለት ዋና ዋና የስትሮክ አይነቶች አሉ። እነርሱም በአንጎል ዉስጥ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰትና በደም ቧንቧ መዘጋት ወይም መጥበብ ምክንያት ወደ አንጎል የሚሄድዉን ደም መጠን በመቀነስ የሚከሰቱ ናቸዉ። ሁለቱም…»
19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 22:23:34 ስትሮክ

ክፍል አንድ
ስትሮክ በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በሚስተጓጎልበት ወቅት የአንጎል ሴሎች(ሕዋሶች) እንዲሞቱ የሚያደርግ የጤና እክል ነው። ሁለት ዋና ዋና የስትሮክ አይነቶች አሉ። እነርሱም በአንጎል ዉስጥ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰትና በደም ቧንቧ መዘጋት ወይም መጥበብ ምክንያት ወደ አንጎል የሚሄድዉን ደም መጠን በመቀነስ የሚከሰቱ ናቸዉ። ሁለቱም የአንጎል ክፍሎች ሥራቸውን በትክክል እንዳያከናዉኑ ወይም እንዲያቆሙ ያደርጉታል። ስትሮክ የሚከሰተው የአንጎላቸን የደም አቅርቦት በሚቀነሱ ወይም በመዘጋቱ ምክንያት ነው። ስትሮክ የድንገተኛ ህክምና ስለሚፈልግ ፈጣን ህክምና መስጠት ወሳኝ ነው። አስቀደም እርምጃ መውሰድ የአንጎል ጉዳትንና ሌሎች ችግሮችን ሊቀንስ ይችላል።

የህመም ምልክቶች
ለመናገር መቸገር እንዲሁም ሌሎች የሚሉትን ለመረዳት መቸገር፦ ግራ መጋባት፣ ቃላት/ድምፅ ማዉጣት መቸገር ወይም ንግግር መረዳትን መቸገር
የፊት፣ ክንድ ወይም እግር ሽባ መሆን ወይም መደንዘዝ፦ በድንገት የመደንዘዝ ስሜት፤ ፊት ፣ ክንድ ወይም እግር ላይ ድክመት ወይም ማንቀሳቀስ መቸገር። ይህ ብዙውን ጊዜ አንድን የሰውነት ክፍል በቀኝ ወይም ግራ ብቻ ምልክቱ ይታያል።
በአንድ ወይም በሁለቱም አይኖች ላይ የማየት ችግር መከሰት
በአንድ ወይም በሁለቱም አይኖች ላይ በድንገት ብዥ የማለት ወይም ጭልም ማለት ሊኖርዎት ይችላል ወይም አንድ ነገር ሁለት ሆኖ የመታየት ችግር ሊኖር ይችላል።
የራስ ምታት፦ ከድንገተኛና ከባድ ራስ ምታት ጋር ተያይዞ ማስታወክ፣ መፍዘዝ ወይም የንቃተ ህሊና መቀነስ ወይም እራስን መሳት የስትሮክን ሊያመለክት ይችላል።
ለመራመድ መቸገር፦ የባላንስ ማጣት፣ እንዲሁም ድንገተኛ ማዞር ወይም ቅንጅት ማጣት (loss oc coordination) ሊኖርብዎ ይችላል።

መንስኤዎች
ለስትሮክ ሁለት ዋና ዋና መንሰኤዎች አሉ እነርሱም የደም ቧንቧ መዘጋት ወይም በደም መርጋት የሚከሰት( ኢስኬሚክ ስትሮክ)ና የደም ቧንቧ መፈንዳት ችግር ምክንያት የሚከሰቱ( ሄሞረጂክ ስትሮክ) ናቸዉ። አንዳንዶች ደግሞ በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ፍሰት በጊዜያዊነት ብቻ መስተጓጎል ሊገጥማቸዉ ይችላል። በዚህም ምክንያት የህመም ምልክቶቹ ለአጭር ጊዜ ብቻ ሊታይ የሚችል ሲሆን ይህም ትራንዚየንት ኢስኬሚክ አታክ(TIA) ይባላል።

በደም መርጋት ምክንያት የሚከሰት (Ischemic stroke)
ይህ አይነቱ በጣም የተለመደና በብዛት የሚከሰት የስትሮክ አይነት ነዉ። ይህ የአንጎል የደም ስሮች ሲጠበቡ ወይም ሲዘጉ የሚከሰት ሲሆን ወደ አንጎል የሚሄድን የደም ዝውውርን በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጋል (ischemia) ።
የተዘጉ ወይም የጠበቡ የደም ስሮች የሚከሰቱት በደም ስሮች ውስጥ በሚጠራቀሙ የስብ ክምችቶች፣ በደም መርጋት ወይም በደም ዝውውር ውስጥ በሚጓዙና ከልብ ተነስተዉ በደም ስሮች ዉስጥ ተሰክተዉ በሚቀሩ ሌሎች ነገሮች ምክንያት ነው።


አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ

https://www.facebook.com/sturaelclinic/
https://www.sturaelclinic.com/
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
https://sturaelclinic@gmail.com
847 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ