ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ tafachtarikoch1 — ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇
የቴሌግራም ቻናል አርማ tafachtarikoch1 — ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇
የሰርጥ አድራሻ: @tafachtarikoch1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 74
ተመሳሳይ ቻናሎች ያልተመደበ
የሰርጥ መግለጫ

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
➤ ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ᴀɴᴅ ᴀᴅᴠᴇʀᴛɪsɪɴɢ 📩
@nati_promotion & @Natiiiye

የቻናል ስታትስቲክስ
10000% የተሳትፎ መጠን
7,400 እይታዎች / ልጥፍ
0 ልጥፎች / ቀን

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

17 juuli 2024


የ18 አመቷ ታዳጊ አሳዛኝ ወግ

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በ ጣፋጭ ታሪኮች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ

#ክፍል8



<< ማታ ማታ ከመ/ር ይግረም ጋር ብቻችንን ፊት ለፊት በባዶ ቤት መፋጠጥ ጀመርን፡፡
መ/ር ይግረም ብዙ ይቆዝማል፡፡ እኔንም ምንም ክፉ ቃል ሳይናገረኝ ባላምነውም እንኳን እንደፈራሁት ሳይሆን ባልጠበኩት መንገድ ጥሩ ሰው ሆነልኝ፡፡ መስከሩን እርግፍ አርጎ ተወ፡፡ ከሕይወት በኃላም ህይወት ቀጠለች፡፡ መስከረም ሲመጣ ያቆምኩትን 6ተኛ ክፍል ቀጠልኩ፡፡ ነገር ግን ትምህርት ያስጠላኝና ፈተናም መስራት ያቅተኝ ጀመር። ባይመታኝም ባይቆጣኝም ምንም ባይለኝም ከመ/ር ይግረም ጋር በአንድ ቤት መኖሬ ውስጤን ፋታ ነሳኝ፡፡ ሁሌም ሳየው እናቴን ሲመታት ሲያንጓጥጣት ይታየኛል፡፡ እሱ ግን አንድም ክፉ ቃል ተናግሮኝ አያቅም። በአብዛኛውን ጊዜ ከትምህርት ቤት መልስ እነ ለምለም ቤት በመሄድ አሳልፍ ነበር፡፡ ወንድሟ መ/ር አይተነው በትርፍ ጊዜው ሁሌም የከበደንን ትምህርት ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን እኔ መማር እጅግ እያስጠላኝ መጣ።ሲያስረዳን ከለምለም በፊት እኔን ይገባኛል፡፡ ፈተና ላይ ግን ሀሳቤን መሠብሰብ እያቃተኝ ዝቅተኛ ውጤት አመጣለው፡፡ በዚ ሁኔታ ተንጠልጥየ ወደ 7ተኛ ክፍል ለትንሽ አለፍኩ፡፡ ለምለም ደረጃ ውስጥ ባትገባም ጥሩ ውጤት ነበር ያመጣችው፡፡ መ/ር አይተነው ቁጣም ምክርም እየቀላቀለ ገሰፀኝ፡፡ እናም አንዳንድ ጊዜ ለምለም ወጥ ስትሰራ ወይም ልብስ ስታጥብም ሳይቀር እኔን ለብቻየ ያስጠናኝ ነበረ፡፡ የማይለመድ ነገር ስለሌለ ይሁን ወይም ሀዘኔን ለምጄው ባይገባኝም ወደ በፊቱ ጥሩ አቋሜ መመለስ ጀመርኩ። ውጤቴም እየተስተካከለ መጣ።
የህፃንነት ጊዜየን በቅጡ ሳላጣጥመው የልጅነቴ ጊዜ እያለፈ የኮረዳነት መልካችን እየጎመራ እንደፅጌረዳ መፍካት ሲጀምር ብዙ የወንድ ማጭዶች ሊቀጥፉን ተስገበገቡ፡፡ ለምለም ከትምህርት ቤት ስንመለስ የሚለክፉንን ወንዶች መልስ ትሰጣቸዋለች፤ አንዳንዴም ለማስቆም የሚሞክሩትን ሳይቀር እየቆመች ታዋራቸዋለች። ለምለም በጣም ደስ የሚል ደም ግባት ያላት ከጎራዳ አፍንጫዋ በስተቀር ከሚያምረው ቀይ ክብ ፊቷ ምንም እንከን የማይገኝላት ልቅም ያለች ቆንጆ ነች። ደብረ ኤልያስ ከሚባል አነስተኛ የገጠር ከተማ ወንድሟ ሊያስተምራት ያመጣት ሲሆን ትምህርት ቤት ስትገባ ትንሽ በመዘግየቷ ከኔ በ3 አመት ትበልጣለች፡፡ 17 አመቷ ነው፡፡ በተክለ ቁመና ግን ከኔ ምንም ያህል አትበልጥም። በዚ በሀሪዋ ግን ከኔጋ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡ እንደ ታላቅ እህቴ ብቆጥራትም ስለ ወንዶች መጥፎነት ሳልሰስት እነግራታለሁ እሷ ግን አልሰማኝ አለች። እንዳውም አንድ ቀን ሁሌም የሚከታተለንን ልጅ ወዳው ኖሮ ቆማ ስታናግረው ቆይታ መጣችና እሳት ጎርሳ እሳት ለብሳ << አንቺ ግን ወንዶቹን ምን እያስነካሻቸው ነው ሁሉም ካዋሩኝ በዉሀላ እኔን ሳይሆን አንቺን ፈልገው እንደሆነ ይነግሩኛል። ኤጭ አሁንስ አስጠላሽኝ የሆንሽ አስመሳይ ነሽ!>> አለችኝ ምርር ብላ እየተሳደበች። ደነገጥኩ! ወንዶችን ምን ያህል እንደምጠላቸው እያወቀች እንዴት እንዲ ትለኛለች በዛ ላይ በጣም ልጅ ነኝ እያልኩኝ ብስልስል ብየ ተከፋሁና ተቀየምኳት፡፡በተለይ በሷ እንዲ መባሌ አመመኝ። ከለምለም ጋር ትምህርት ቤትም ሆነ መኖሪያ ቤታቸው መሔድ አቆምኩኝ። ብቸኝነቴን ታገልኩት፤ ለካ የሚያዋሩትም ሰው ማጣት ከባድ ቅጣት ነው!? እናቴ እንደ አዲስ ትናፍቀኝ ጀመር። ከ2 ሳምንት በኃላ የለምለም ወንድም መ/ር አይተነው ትምህርት ቤት ስገባ በር ላይ ጠብቆኝ ......


Like አይቆጥርም ኧረ ተጫኑት

✎.ክፍል ዘጠኝ(9)ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ. Like & Share  ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ ጥል ሼር ያድርጉ
                ------
------
     @TAFACHTARIKOCH1
     @TAFACHTARIKOCH1
7.4K views𝔹𝕝𝕒𝕔𝕜 𝔹𝕝𝕠𝕠𝕕 , 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 74 ተመዝጋቢዎች ያሉት የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ ግምገማዎች፣ ደረጃ እና ዝርዝር ስታቲስቲክስ ይገኛሉ።
በዚህ ገጽ ላይ "ወደ ቻናል ይሂዱ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ወይም @tafachtarikoch1 ን በቴሌግራም መተግበሪያ ውስጥ ይፈልጉ። እንዲሁም የቻናሉን የተጠቃሚ ስም ገልብጠው በቴሌግራም መፈለጊያ ውስጥ መለጠፍ ይችላሉ።
አዎ፣ ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 ነፃ የቴሌግራም ቻናል ነው። ሁሉንም ልጥፎች ያለምንም ክፍያ መከታተል እና ማንበብ ይችላሉ።
ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 ይዘቱን በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ያትማል። መልእክቶቹን ለማንበብ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ቻናሉን በቴሌግራም ይክፈቱ።
አዎ፣ ተመሳሳይ የያልተመደበ ቻናሎችን ከታች "ተመሳሳይ ቻናሎች" በሚለው ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ተዛማጅ የቴሌግራም ቡድኖችን፣ ቦቶችን እና ተለጣፊዎችንም እናሳያለን።
መልእክቶቹ በቴሌግራም ውስጥ ይነበባሉ፦ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 ን ይክፈቱ። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ የተመዝጋቢዎች ብዛት፣ ግምገማዎች እና ስታቲስቲክስ ያገኛሉ።
ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 avatar
ጣፋጭ ታሪኮች አገናኝ❤️👇 @tafachtarikoch1
በቴሌግራም ይክፈቱ