Get Mystery Box with random crypto!

ፈገግታ ሱና ነዉ፡፡ #ዛሬ የምነግራችሁ ስለ አንድ የዋህና ብልጥ ሸህ ታሪክ ነዉ፡፡ ሁለቱም የሚ | || Sᴇʟʟᴜ ᴀʟʟᴇ ɴᴇʙɪʏ ﷺ ||

ፈገግታ ሱና ነዉ፡፡

#ዛሬ የምነግራችሁ ስለ አንድ የዋህና ብልጥ ሸህ ታሪክ ነዉ፡፡ ሁለቱም የሚኖሩት በገጠሩ ክልል ሲሆን #ሸህየዉ አላገቡም ነበር፡፡ የዋሁ ሰዉየ ምንም ቁርአንም ኪታብም አልቀራም ጃሂል ነዉ፡፡

ሰዉየዉም በሰላም ሚስቱ ጋር እየኖረ ህልም ያያል ህልሙም ሚስቱን ሶስቴ ሲፈታት በህልሙ ያያል ....ሶስቴ መፍታት ከትዳር እንደተፋቱ ነዉ ሲሉ ሰምቶ እስኪ ለማንኛውም ልጠይቅ ይልና የሰፈሩን ሸህ ይጠይቃቸዋል፡፡

#ሰዉየዉ :- ሸሀችን በህልሜ ሚስቴን ሶስቴ ፈትቻት ነበር ፡፡ ምንድን ትሉኛለሁ ሲለቸዉ

#ሸህየዉም:- ያማ በህልምህ ስለፈታህ ግድ መፍታት አለብህ ይሉታል፡፡ከዛ ሰዉየዉም እያዘነ እነሸህ ካሉማ ምን ይደረጋል ይልና ይፈታታል፡፡

ከ ሁለት ወር ቡሀላ ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ..የተፈታችዉን ልጅ ሸህየዉ ለራሳቸዉ የትዳር አጋር እንድትሆናቸዉ አገቧት፡፡

ጃሂሉም ሰዉየ ሰምቶ ተሸወድኩ ብሎ ነገሩን ተወዉ፡፡

አንድ በጣም የሚቀርበዉ ጓደኛዉ አልሰማም ነበር ,..ምንድን ነዉ የአንተን ሚስት #እነሸህ ጋር አየሇት እሳ ሲለዉ ...እሱም እኔማ በህልሜ ሶስቴ ስፈታት አይቼ እነሸህን ፈትዋ ጠይቂያቸዉ ፍቹ ግድ ነዉ ሲሉኝ ፈትቼ ኢሄዉ እሳቸዉ አገቧት ይለዋል፡፡

ጓደኛዉ  በሰማዉ ነገር ተናደደ ጓደኛዉ በጣም በሳልና ብልጥ ነበር..ና እኔን ጥልቆ ይዘህ ተከተለኝ ይለዋል ሁለቱም ጥልቆ ይዘዉ ሸህየዉ ቤት ይሄዳሉ ፡፡

ከዛ የሰዉየዉን ቤት ግርግዳ በጥልቆዉ መምታት ጀምሩ ..ከዛ ሸህየዉ ምንድን ነዉ ተዉ እንጂ ሲሏቸዉ ..ጓደኛዉ እነ ሸህ ዝም በሉማ...የሆነ ነገር ታይቶናል ይላቸዋል..,ከዛም ቤቱን ዝም ብለዉ በጥልቆ መምታቸዉን ቀጠሉ ..ከዛ

#ሸህየዉም አረ እባካችሁ ተዉ ቤቴን በጥልቆ መምታታችሁን ሲሉ .. የሰዉየዉ ጓደኛ ሸሀችን ወድጄ አይደለም ቤትሁን በጥልቆ የምመታዉ በህልሜ የአንቱን ቤት በጥልቆ ስመታዉ አይቼ ነዉ ይላቸዋል፡፡

ሸህየዉም በፍጥነት ህልም እኮ ዉሸት ነዉ ይሏቸዋል፡፡ የሰዉየዉ ጓደኛም ምን ቢል ጥሩ ነዉ
ህልም ዉሸት ከሆነ የጓደኛየን ሚስት መልሱ ፡፡ ብሏቸዉ እርፍ

መመለሷን አለመመለሷን አጣርተን እንነግራችሇለን፡፡

ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ ፈትዋ የምንጠይቀዉ የምናማክረዉ የምናወያየዉ እና ሀሳብ የምናጋራዉን ሰዉ ለይተን ማወቅ አለብን።

ጨረስኩ

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN:       
JOIN: @SELLU_RESUL    ╚════════════╝