እናቴ አንቺ እየከሣሽ እኔ መፋፋቴ አንቺ አጎንብሠሽ እኔ መቃናቴ። ተርቦ አንጀትሽ ጠግቤ መብላቴ ባዶ እግርሽን ሁነሽ እኔ መጫማቴ። አንቺ አፍሽ ደርቆ እኔ መጠጣቴ አንቺ ሣትማሪ ተምሬ ማወቄ ልፋትሽ ተረሥቶ እኔ መደነቄ። እውቀትና ክብሬ ሥጦታ ውበቴ ሽልማት ማሬጌ መልኬ ደም ግባቴ። የእኔኮ አይደለም የአንቺ ነው እናቴ። እማ ፈጣሪ አብዝቶ ጤናሽን ይሥጥሽ @Addisu32 https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0 1.1K viewsAddisu, edited 16:16