Get Mystery Box with random crypto!

      #ልወዳት_ነው_መሰል       ━━━━✦ ✦━━━━ ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ ቀል | ❤ የፍቅር ግጥም🌹

      #ልወዳት_ነው_መሰል
      ━━━━✦ ✦━━━━

ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
ቀልቤ እኔን ጥሎ እሷ ጋር በረረ
አያት እንዳልነበር እንደ ንፁህ እህቴ
ታዲያ ምነው ዛሬ እንቅልፍ ማጣቴ
አይኗን ካላየው ድብርት ውስጥ መግባቴ
.
ልወዳት ነው መሰል ትናፍቀኛለች
በደቂቂቃ ሲኮንድ ትዝ ትለኛለች
ከሌላ ጋር ሳያት በቅናት ማበዴ
አፈቀርኳት መሰል ወቸው! በል ዘመዴ
.
ልነግራት ስፈልግ የልቤን አውጥቼ
ፍቅሬ እንድትሆን በፅኑ ጓጉቼ
ግን ደግሞ እንደገና እጠራጠራለሁ
እህትነትሽን እንዳላጣ ሰጋሁ…
.
ልወዳት ነው መሰል ልቤ ጠረጠረ
በቃ! እነግራታለሁ በኔ አልተጀመረ


       ,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
                  •═••• •••═•
  
     @selafeker
   ,,,,,, @Addisu32
━━━━━━━✦ ✿✦━━━━━━━

https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0