Get Mystery Box with random crypto!

ሁለታችን ታመን የሌቱን ማህሌት ፣ የንጋቱን ደወል ጆሮሽ ሰምቶ ነቅቶ ሩቅ ሊያይ ቢማልል ትዝ አለ | ❤ የፍቅር ግጥም🌹

ሁለታችን ታመን

የሌቱን ማህሌት ፣ የንጋቱን ደወል
ጆሮሽ ሰምቶ ነቅቶ ሩቅ ሊያይ ቢማልል
ትዝ አለኝ ዘፋኙ ትዝ አለኝ ዜመኛው
ሁለታችን ታመን ብሎ የተቀኘው
እውነት በጥልቅ ዕድሜ ...
በአንድ ጎጆ ታዛ ፍቅር አስጠልሎን
የዘነበው ካፊያ በጣሪያው ቀዳዳ ዘልቆ ገብቶ ነክቶን
በገላየ ጥምቀት ገላሽ እየራሰ
ፍቅር ለዘመናት ደምቆ እየታደሰ
በእፀ ፈውስ ቅጠል ህመማችን ስንሽር
በአብሮነት ውብ ቀለም አብረን ስንሰደር
በጀምበር ንግስና ጠዋት እየፈካን
ነቃን ከጥል ደዌ ሁለታችን ታመን

@Addisu32

𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 በ ፍቅር

━━━━━━✦✗✦━━━━━━


https://t.me/+kHkzbnAK3CA3MDY0