2022-08-11 18:33:43
መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት
ሠላም፣ ቲቪ፣ ነሀሴ 5/2014 አ አ
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።
የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔውን ምክረ ሀሳብን ውድቅ ያደረገው።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17/2011 ባደረገው ጉባኤ ዞኑ ራሱን ችሎ ክልል ለመሆን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
የደቡብ ክልልን ለሁለት የሚከፍለውን የክልልነት አደረጃጀት በም/ቤቱ ባለማጽደቅ የጉራጌ ዞን ብቸኛው ሆኗል።
ቀሪዎች የደቡብ ክልል 10 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ ሁለት ክልል የመመስረት ውሳኔን በምክር ቤቶቻቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል።
የተከበራችሁ የሰላም ቲቪ ታዳሚያን፤ ዝግጅቶቻችንን በሚከተሉት ሊንኮች ይከታተሉ፣ ለሌሎችም በማጋራት መረጃዎቹን ያስተላልፉ
You tube https://m.youtube.com/channel/UC0iqOAbFBmmPgffGPou85RANGE 8um
Facebook https://www.facebook.com/358052114402788/postgs/1540031149538206/
Telegram
https://t.me/joinchat/AAAAAEvmfSnMMMBhyE2XxgL
266 viewsMustefa Aman amba, 15:33