2022-10-10 16:32:10
➧ኢብኑ ተይሚያህ~የሱንናዉ አንበሳ ➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬
◉ክፍል 24
ዙህዳቸዉ ➺➺➺➺
➲ገና በልጂነታቸዉ ጀምሮ አላህ በልባቸዉ ዉስጥ ኢኽላስን አስርፆላቸዋል። እኩዮቻቸዉ በብልጭልጭ መጫወቻ በሚሸወዱበት ግዜ እንኳን ጌታቸዉን አስበዉ ዱንያን ይፀየፉ ነበር።
➲ቁርአን ያስተማሯቸዉ ሸይኽ እንድህ ይላሉ፦"የኢብኑ ተይሚያ አባት ልጃቸዉ ቁርአን ሲያቋርጥ የሚቀራ ከሆነ,በየ ወሩ አርባ ድርሀም እንደሚሸለም ንገርልኝ። ይሄ የዚህ ወር ነዉ ብለዉ አርባ ድርሀም ሰጡኝተ,በወሩ ስጠዉ። ልጂ ስለሆነ ተደስቶ ለቁርአን ያለዉ ጉጉት ይጨምራል፣ ትምህርቱንም ይቀጥላል። በየ ወሩም ተመሳሳይ ነገር አለህ በለዉ አሉኝ።➲ግዜዉ ሲደርስ ልሰጠዉ ብል ሊቀበል ፍቃደኛ አልሆነም። አለቃዪ! እኔ በቁርአን ደመወዝ ላልቀበልበት ለአላህ ቃል ገብቻለሁ" ብሎ አምቢ አለ። ይሄ የአላህ እንክብካቤ እንጂ ከህፃን የሚከሰት እንዳልሆነ አሰብኩ።
➲ዑመር አልበዛር ረሒመሁላህ ከዚህ ታሪክ ስር እንድህ ይላሉ፦ ሸይኹ እዉነት ብሏል ለደረሰበት ኸይር ሁሉ ያደረሰዉ ኋላ የመጣ ሳይሆን ገና ከህፃንነቱ ያገኘዉ የአላህ ጥበቃ ነዉ።(አል አዕላም 45)
➲በዘመናችን እንደሳቸዉ ያለ ዛሂድ አልታየም። በቅርብ የሚያዉቃቸዉ ቀርቶ ተራዉ ህዝብ ሳይቀር የሚያምነዉና የሚቀባበለዉ ይህን ነበር። ሲበዛ ትሁት ነበሩ። ደካሞችን ድሀዎችን ያቀረቡ፣ያከብሩና ይንከባከቡ ነበር።ሴት ሆነ ወንድ፣ትልቅ ሆነ ትንሺ፣ ባሪያ ሆነ ነፃ ፣ዓሊም ሆነ መሃይም፣ ከተሜ ሆነ ገጠሬ የጠየቃቸዉን አይሰለቹም፣አያርቁም፣የሚያስከፍቸዉን አይናገሩም።እነሱ እስከሚለዩ ጥለዉ አይሄዱም።
➲አለባበሳቸዉ አቀማመጣቸዉ፣ አካሄዳቸዉ ከተራዉ ህዝብ በምንም መልኩ የሚለይ አልነበረም።ስለ ዱኒያ ብልጭልጭ፣ገፀታ ስለ ጣፍጭ ጣዕም፣ስለ ኑሮ አያወሩም፣አይጠይቁም።➲ይልቁንም ሙሉ ትኩረታቸዉ አኼራን ፍለጋ ነበረ። ቤተሰቦቻቸዉን ራሳቸዉ አስበዉ ካላመጡ በስተቀር ምግብ አይጠይቁም። የሁል ግዜ ሁኔታቸዉ እንድሁ ነበር ይላሉ ወንድማቸዉ።እኚህ ወንድማቸዉ ልክ ንጉስን እንደሚያከብሩት ነበር ወንድማቸዉን የሚያከብሩት።ልክ እራሳቸዉ ላይ ወፍ ያረፈባቸዉ ይመስል ነበር ከሳቸዉ ጋር ሲሆኑ የሚያሳዩት መረጋጋት።
➲ሁኔታዉ ይደንቀን ነበር። በልምድ አንድን ሰዉ የዉጭ ሰዉ የሚያከብረዉን ያክል ቤተሰቦቹ አያከብሩትም። ይልቁንም ከፊቱ ዘና ይላሉ።ምነዉ አንተን ልክ በሸይኹ ላይ ድንበር እንደሚያልፍ ተማሪ አይነት የምናይህ?እያልን እንጠይቀዉ ነበር ይላሉ አልበዛር።መልሱ ግን እኔ እንድህ እንደምታዩኝ እንድሆን ያስገደደኝ ሌላ ሰዉ የማያየዉ ብዙ ነገር ከሱ ሰለማይ ነዉ ይሉ ነበር።ምን እንደሆነ ሲጠይቁ ግን ለመናገር ፍቃደኛ አይሆኑም። ምክንያቱም ሸይኽ ሸይኽ እንድህ አይነት ገዳይ እንድወጣ ፍላጎት እንደሌላቸዉ ስለሚያዉቁ።(አል አዕላም፡55)➲ለስልጣን የሚያንጋጥጡም አልነበሩም። ገና ሰላሳ አመት እንኳን ሳይሞላቸዉ የዳኞች የበላይ ዳኛ፣ልክ እንድሁ የመሻይኾች ሀላፊ እንድሆኑ ተጠይቀዉ ነበረ።ሀላፊነቱ ሌሎች ሊሸከሙ ይችላሉ ብለዉ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።(ዘይል፣4/98)
➲በ700ሂ ወደ ግብፀ መንግስት ለጂሃድ ቅስቀሳ በሄዱበት ወቅት እንኳን ከተማሪያቸዉ አጓት ቤት ነዉ ያረፉት። ከመንግስት ደመወዝ እና ስጦታዎች ቢበረከቱም ለመቀበል ፍቃደኛ አልሆኑም። ከአመታት ቡሀላ በግብፀ እስር ቤት በነበሩ ግዜም መንግስት የሚቀርበዉን ልብስም ጉርስም ሊቀበሉ ፍቃደኛ አልነበሩም።ከመንግስት ዳርጎት ጋር ጭራሺ መነካካት አይፈልጉም ነበር።➲እድሜ ልካቸዉን በግብይት ጉዳይ፣በንግድ፣በግብርና፣በግንባታ፣ ጉዳይ ከሰዉ ጋር ተቀላቅለዉ አያዉቁም።ከአሚርም፣ከሱልጧንም፣ ከነጋዴም ጋር በዚህ ጋር የተያያዘ ግንኙነት የላቸዉም።ገንዘብ፣ንብረትም፣ ምግብም አያስቀምጡም።እንድህ ነበር ህይወታቸዉ።
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ......................
ከመጀመሪያዉ ለማግኘት ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
t.me/abuUseyminabdurehman/6601
t.me/abuUseyminabdurehman/6601
ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ሸር ያድርጉ!➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/abuUseyminabdurehman
91 viewsاحْرِصْ عَلَى مَا يَنفَعُكَ واسْتَعِنْ بِاللهِ, 13:32