Get Mystery Box with random crypto!

ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርና ዐብዱልመሊክ ኢብኑ መርዋን እርስ በርስ መዋጋት ጀምረዋል። የወንድማማችነታ | SEBIL TUBE

ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርና ዐብዱልመሊክ ኢብኑ መርዋን እርስ በርስ መዋጋት ጀምረዋል። የወንድማማችነታቸው ነገር ንፋስ ገብቶት አሻክሯቸዋል። በዚህ ጊዜ ታዲያ የሮማዊያን መኳንንቶችና የጦር አበጋዞች ተሰባስበው ንጉሳቸው ዘንድ አመሩ።
"ንጉስ ሆይ! አሁን ሙስሊሞች እርስ በርስ መጣላት ጀምረዋል። ይህ ዕድል ሳያመልጠን እንፋለማቸው" አሉት።
ንጉሱ ግን "በፍፁም እንዳታደርጉት!" በማለት ግርምትን የሚያጭር መልስ ሰጣቸው።
መኳንንቶቹ በመልሱ በመደነቅ ምክኒያቱን ጠየቁ። ንጉሱም ሁለት ውሻዎችን አስመጣና እንዲያናክሷቸው አስደረገ። ውሻዎቹ እርስ በርስ እየተናከሱ ጠባቸው ሲፋፋም ንጉሱ ቀበሮ አስመጣና ወደ ውሾቹ ላከ። በዚህ ጊዜ ውሻዎቹ ጠባቸውን ትተው በመተባበር ቀበሮውን አሳደው ገደሉት። በዚህ ጊዜ ንጉሱ
"የኛና የሙስሊሞች ምሳሌ ይህ ነው! ካጠቃናቸው አንድ ሆነው ይጨርሱናል! ከተውናቸው ግን እርስ በርስ ይጨራረሳሉ" አላቸው።
ይኸው ነው ምሳሌያችን
ወንድሜ! ታሪኩ እርስ በርስ መናከሳችን ትርፉ ለጠላት መሆኑን ነው የሚነግረን!

ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ቁተይባ ዑዩኑል አኽባር በተባለ ኪታባቸው ላይ ታሪኩን ዘግበዋል።

@sebil_tube
@sebil_tube