Get Mystery Box with random crypto!

ልቧ እስኪጠፋ እንደምትወደኝ አውቃለው ስሜ እስኪጠፋኝ እወዳታለው....አንድ ቀን ፍቅሯ ንሽጥ አረገ | SEBIL TUBE

ልቧ እስኪጠፋ እንደምትወደኝ አውቃለው ስሜ እስኪጠፋኝ እወዳታለው....አንድ ቀን ፍቅሯ ንሽጥ አረገኝና "ታገቢኛለሽ " አልኳት
"ምን አለህ? " አለችኝ በማፌዝ አኳሆን::

"ማለት?" ግራ በመጋባት
"ለኔ የሚሆን ምን አለህ?" አለችኝ።
"ንፅሁ ልብ ፍቅርና ጤና....."
"ጤነኝነትህ መች ጠፋኝ በቀን ሶስት ድንች በአዋዜ ብቻ እየሰለቀጥክ እንዲህ ደልበ እያየሁ......" አለችኝ።

ደሜ እንደበረንዳ ቡና ይንተከተክ ጀመር?
"ቆይ ያ ሁሉ ውሸት ነበር ....አታፈቅርኝም ማለት ነው?"
"አፈቅርሀለው ነገር ግን ፍቅር ብቻ ትዳር አይሆንም?" አለችኝ።
"ፍቅር ትዳር ካልሆነ ታድያ የትዳር ዋስትናው ምንድነው?" ብሽቅ እያልኩ....
"ፍቅር የትዳር ዋስትና አይሆንሞ አላልኩም ትዳር በፍቅር ብቻ አይቆምም: ትዳር ልብ ለልብ መግባባት፣ፀባይ ከፀባይ መጣጣም....."

"ጀመርሽ እንግዲ....አትፈላስፊቢኝ" ስል ጮሄ አቋረጥኳት።
"አትጩህብኝ ግልፍተኛ! እንዲሁም አግብቼ እያከክኩ መኖር አልፈልግም ! አላገባህም" ስትል አንቧረቀች።
ሳላስብበት በደመነፍስ በቃሪያ ጥፊ አላስኳት።

አፍንጫዋን ይዛ ስትለቀው እየነሰረች ነበር። ምንድን ነው ያደረግኩት? የምይዝ የምለቀውን አጣሁ...
"አልጎዳሀኝም አትጨነቅ" አለችኝ አፍንጮዋን መልስ እየያዘች፣ፈገግ ብላ እያየችኝ።

ነስሩ ጋብ ሲልላት "አየህ ፈተናህን ወደቅክ .....እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ ዳሩ ግን እንደሮሚዮ እስከመቃብር ሊከተለኝ የሚችል ፍቅር ቢኖርህም፣ ሲጥ አድርጎ ሊገድለኝ የሚችል ግልፍተኝነትህ ያሳስበኛል!" አለች ትኩር አድርጋ እያየችኝ #منقول

@sebil_tube
@sebil_tube