Get Mystery Box with random crypto!

'ሁኔታችን እያማረኝ አይደለም ' .......... ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት እርግፍ አድርጌ መ | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

"ሁኔታችን እያማረኝ አይደለም "
.......... ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት እርግፍ አድርጌ መቁረጡ ከብዶኝ አልያም ከተለየሁህ በዃላ ያለው የብቸኝነት ሂወቴ አስጨንቆኝ አይደለም : ወይ ደግሞ አንተ ከኔ ውጭ የሌላ ሴት ብትሆን ቅናቱ አያስቀምጠኝም የሚል ፍራቻ ውስጤን ሞልቶትም አይደለም ........ ግን እንዴት አድርጌ ፍቅሩን ከልቤ ላይ መፋቅ እችላለሁ ? " በየትኛውስ አቅሜ " እንዴትስ አድርጌ እኒያን ሁሉ ትዝታዎች በቀላሉ መርሳትና እንዳልነበሩ አስቤ መኖር እችላለሁ ? የሚሉት ነገሮች ናቸው ሁሌም የሚያስፈሩኝ ... አየህ ያም ነው ዛሬ ጓንህ የመሆኔ ምክኒያት የሆነው ......... ነገስ ???? እንጃ
#ሼን