Get Mystery Box with random crypto!

አማራጩ መጠንከር ብቻ ሲሆን! ያላችሁ ምርጫ ብርቱና ጠንካራ መሆን ብቻ ሲሆን፣ ያን ጊዜ በእርግጥ | የ ሼን ግጥሞች እና እይታዎች ♥

አማራጩ መጠንከር ብቻ ሲሆን!

ያላችሁ ምርጫ ብርቱና ጠንካራ መሆን ብቻ ሲሆን፣ ያን ጊዜ በእርግጥም ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ ሰዎች እንደሆናችሁ ታውቁታላችሁ፡፡

ሁሉም ነገር ተስፋ አጥቶ፣ አንዱን ችግር ተወጣሁት ስትሉ ሌላው ችግር ሲተካና ግራ ሲያጋባችሁ፡፡ ከሰዎች የምትጠብቁትን መልካም ነገር ሳታገኙ ስትቀሩና የማትጠብቁትን ጥሩ ያልሆነ ነገር ስታገኙ፣ ያላችሁ አማራጭ መጠንከር ብቻ ነው፡፡

ያን ጊዜ ነው ምን ያህል ብርቱና ጠንካራ እንደሆናችሁ የምታውቁት፡፡ ሁሉም ነገር የከዳችሁና መስመር የሳተ ሲመስላችሁ ምን ያህል ጠንካራና ጎበዝ እንደሆናችሁ የምታውቁበት ጊዜ ነውና ተስፋ አትቁረጡ፡፡
#መልካም_እንቅልፍ