Get Mystery Box with random crypto!

ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ samuelbelete — ሳሙኤል በለጠ(ባማ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ samuelbelete — ሳሙኤል በለጠ(ባማ)
የሰርጥ አድራሻ: @samuelbelete
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

የሐሳብ ነገር
| @wosdomati |

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 01:03:10
ግብዥ
#
ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከጎተ ኢኒስቲቲዩት እና ከኢጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ጋር በጣምራ የሚያሰናዱት ወርሀዊ የመጻሕፍት ላይ ሂሳዊ የውይይት መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 28 2014 ዓ.ም በአገልግሎቱ ቅጽር ግቢ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ይከናወናል፡፡ በአካል እንዲሁም በኦን ላይ ዙም መተግበሪያ ላይ ከ8፡00 ጀምሮ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡ በዙም ለመገኘት ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያ ወይም የአድራሻ ቁልፍ ይጠቀሙ፡፡
https://zoom.us/j/98380493730?pwd=em1hTDJvVis3LzdDaVR3M3YveS9TZz09
Meeting ID: 983 8049 3730
Passcode: 311999
ርዕስ:- "ታንጀሪና ሆቴል እና ሌሎችም"
ዘውግ:- አጫጭር ልቦለዶች
ደራሲ :- ደረጀ በቀለ
የመነሻ ጽሑፍ አቅራቢ:- ሳሙኤል በለጠ
62 viewsSamuel Belete(bama), 22:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:12:27 From a life of suffering, she explored the new love of the Somali people with her poetic pen. She is a respected painter and art teacher. She is the only African and Ethiopian artist who has participated in major art exhibitions.
I always wonder how much we have studied her work and honored her.
109 viewsSamuel Belete(bama), 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:12:27 The side of poetry and pain
Samuel Bele (Bama)

Kebedech Tekleab (assistant professor) is a highly accomplished artist as a poetess, artist and teacher.
She has created a political movement by participating as a member of the youth movement in ኢህአፖ.

Fyodor Dostoevsky was sentenced to death for joining a fictitious socialist group. He was sent to Siberia and spent four years doing hard labor in prison. After his release, he published a book focusing on his life in prison called "The house of the dead" in the form of a novel. When Kebedech was a student in the art department of Addis Ababa University, they planned to leave the country with others and were captured and sent to their miserable homes.

It was a hard time of punishment. "Every moment was a long slowness of punishment, we were subjected to hard labor, we were tormented by thirst and hunger. The layout of the prison was fenced on one side and the other fence was the ocean of reality. What we eat for breakfast is known only because it is a word. But there is lunch that is not fenced." Maize Porridge. Rat There is Sorghum Porridge for Ten Years [Where is Page-8]

It was during this period that Kebedech started writing poetry. After her release, she continued at Howard University in America, where she left off three years later. She published an award-winning collection of poems entitled ''የት ነው ?' I heard that she is now an assistant professor.

ጣት ወዳጁን ሲያጣ?

እንዲህ እንዳሁኑ ጣት ወዳጅ ሲያጣ
ብዕር እንደ ዋዛ ተዘንግቶ ሳይቀር፤
ጣት ወዳጁን አጥቶ መሬት ሳይቆረቁር
የብሶት ተካፋይ ንጹሕ ብራና አጥቶ
ለምድር ሳይናገር
ተቀባይ ሳያጣ መልዕክት ሳያሰፍር
ሁሉም በየመልኩ ይሰፍር ነበረ
ለመጻፍ ተነስቶ ብዕር ካመረረ
ካንጀት ካመረረ ደም ይተፋል ብዕር
ቢያጥቡት የማይነጻ ቢቀቡት የማይሽር
እሳት ቢጨምሩት ነዲድ ሆኖ 'ሚገር
ደረቁ ብራና እንዲህ ሳይወራዛ
ተዘግቶ ሳይቀር ብዕር እንደ ዋዛ..."
[የት ነው ገጽ-13-14 1972 ሶማልያ(ዋህይ)]

The pain is deep, the pain of her soul has reached her body and her finger that has not touched the ground. It was written in prison. Dostoevsky described the same pain in "The House of the Dead" when he wrote, "The place where we were imprisoned was at the extreme beyond the wall. When we looked at the eaves between the palisades, hoping to see something, not a peep from the sky could be seen. Day and night, guards walked always here and there Time is a kind of messengers of sickness, just sickness." This reminds me of William J. Ray's poem about prison. The poem is called "The Window".  even if we don't climb up, the sky won't be seen/ If I bend down, the slope won't hurt/ I can see 'nothing', I can see an 'empty' picture/ an exhausted soul on the other side of the window; American journalist and author Chuck Palahniuk says so in his memoir.
"It's so hard to forget pain, but it's even harder to remember sweetness. We have no scar to show for happiness. We learn so little from peace." The way the poet went to describe the distance of the horizon of loneliness and pain is surprising.
Deprivation of a person is a disease."ሰው እንጂ መዳኒ" As an example "...ግን ከንፍገት ሁሉ/
ሰው መንፈግ ይከፋል/ ለሰው ሕመም ደዌ/
ሰውን ምን ይተካል?/[የት ነው ገጽ-96]

Indian aerospace scientist and author Abdul Kalam, "Poetry creates poetry from happiness and from deep sadness." He says. The poetess is not silly, she equates "evening and old age". She is right, old age is the night of life. Just as the night is older than the day, so the night is more glorious than the day in the days of youth.

ምሽትና ዕርጅና

...ያይን ብሌን ዓቅሙ
ከተዳከመበት
አፍ ተሞልቶ ነገ ከማይጠራበት
እንደ ምሽት ብርሃን ተስፋ ካነሰበት
አካል አጎንብዞ አዕምሮ ተዳክሞ
ከነ ሕይወት ልምዱ
መሬትን ካዩበት
ከጨቅላው ዘመን ጋር
ሲገናኝ ሸምጦ
ዕለት ለካ አጭር ነው
ነጋሲ ጨለማ ብርሃን ተለውጦ
[የት ነው? ገጽ-98]

It's a corrective thought, "In the evening, I will go out to the plateau. As much as it is, it will make my age melt.... ሌት በጥምቀቷ የነጣው፤ ነጋ፤ ደፈረሰ ደሜ።/ ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘልኝ፤ አዬ የስለት አታምጣ!/ በውጣ ውረድ በጠበል፤ ባሣር ወዜ ቢገረጣ/ ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ፤ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ! [ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድሀን፣ እሳት ወይ አበባ]

Loret Tsagaye Gebre Medhin gave a background comment about her poems (blurb) and said, "Kebedech faced 11 years of persecution, exile and imprisonment as a child with her inner light of poetry. This is the secret of the pen of poetry.
116 viewsSamuel Belete(bama), 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:23:07 የጥንቃቄ - መረጃ
#Share
#Share
አሸባሪው ህውሓት የነፍስ ውጪ ነፍስ ጊቢ ትግሉንና ሸብሩን ቢቀጥልም አጸፋውን መቋቋም ተስኖት እየተፍረከረከ እንዳለ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬም ከትናንቱ ባልተለወጠ ስልት ከንቱ ትግሉን እያካሄደ ያለው ሕውሓት በርካታ ሴራዎችን እንደጠነሰሰ ከታማኝ ምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል። እንደ ከዚህ በፊቱ የሐሰት ፕሮፖጋንደ በመንዛት አሁንም በርካታ ምግብ እና ውኃ በጠማው ትግራይ ህዝብ ላይ ድርብ ቁማር እየተጫወተ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነቱን ያጣው አለም ደም አፍሳሽ እንደሆነ ሲረዳ አሁንም የአሸንፍያለሁ ቀረርት ለማቅራራት ይመቸው ዘንድ ከሰሞኑ አንድ ያቀደው ሴራ እንዳለ ለማወቅ ተችላል።

በዚህም የህወሓት ታጣቂዎች የአማራ ልዩ ሃይል እና የፋኖ ሬንጀር በማስለበስ ማርከናል ብሎ ፕሮፖጋንዳ ለአለም ህዝብ በቀጠራቸው ሚዲያዎች ለማሰራጨት እንዳለመ ከታማኝ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል።

በዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከተሳሳተ መረጃ እንዲሁም ለሕውሓት ዓላማ ከሚዘጋጁ መረጃዎች እራሱን እንዲጠብቅ የኢትዮጵያዊ ዜጎች ፍላጎት መሆኑ ታውቋል።

Vian EBN

#DisarmTPLF
#TPLFBelligerenceMustBeCondemned #TPLFisthecause
#EthiopiaPrevails
78 viewsSamuel Belete(bama), 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:25:30
274 viewsSamuel Belete(bama), 18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:51:48 የጡዘት መጋረጃ ሲቀደድ
ክፍል አንድ
ሳሙኤል በለጠ

ማስተዋወቂያ

የስብስቡ ርዕስ:-ጡዘት
የሕትመት ዘመን:-2008 ዓ.ም
የግጥም ብዛት:-102 ግጥሞች

ፊዶር ደስቶቮስኪ በየትም አገር የገነነ ራሺያዊ ደራሲ ነው፡፡ ደስቶቮስኪ ከሚታወቅባቸው ስራዎች መካከል “white Nights” አንዱ ነው፡፡ በዚህ መጽሃፉ በፒተርስበንግ ከተማ ባይተዋር ስለሆነ ከስጋው ወደ ነፍሱ ስለሚያይ በምሽቱ የሚደንቅ አንድ ገጸ፟ ባህሪ አለ ዶስቶቭስኪ እንዲህ ጽፏል።

“My history!” I cried in alarm. “My history! But who has told you I have a history? I have no history....”
“Then how have you lived, if you have no history?” she interrupted, laughing.
“Absolutely without any history! I have lived, as they say, keeping myself to myself, that is, utterly alone—alone, entirely alone.[White Night ገጽ-16]

ሰውን 'ሚያህል ብርሃን ታሪኩ ሲያጨልመው ታሪክን 'ሚያህል ታላቅ ነገር ሰው ሳይሰራው ሲቀር ከዚህ የበለጠ 'ሚለበልብ ምን ጸጸት አለ? ገጣሚና ጋዜጠኛ ፋሲል ተካልኝ ይህንን ጉዳይ አብሰልሶሎታል።
“…ሰፊ ሆኖ ተገኝቶ እንደ ጨርቅ ታሪኬ
ተንዘልዝሎ ቀረ አልሆን አለ ልኬ።
ከልደት እስከ ሞት ሲተረክ ሰማሁት
የሕይወት ታሪኬ ላይ ታሪኬን አጣሁት።”
ፋሲል ተካልኝ
[ጡዘት ገጽ-30]

በሕይወት ታሪካችን ታሪካችን ከሌላ እኛ ምንድነን? ማነን? የፍልስፍናው አባት ሶቅራጠስ እንዳለው ነው። "unexamined life is not worth living" (ያልተመረመረ ሕይወት ሊኖር አይገባም!) ዶ/ር በድሎ ዋቅጅራ "ለራስ ወቀሳ" 'ሚል ግጥም አላቸው ከራስ ፀበሉ የተጣላን አንድ 'ራስ የሚወቅሱበት ከእድሜ እድሜ ምንም ቀለም፣ ታሪክ ቢያጡበት እንዲህ ወቀሱት
ለራስ ነፍስ ወቀሳ፣
ላጠራቅም ዕድሜ፣
በራፌን ከርችሜ፣
መስኮቴ ላይ ቆሜ፣
አልድን ወይ አላድን፣
በድን!
[የራስ ምስል ገጽ-44]

ግጥም ሲሰምር እንደዚህ ያለ ውስብስቦችን ይገልጻል ዕውቁ ገጣሚ ቻርለስ ብኮቮስኪ “Poetry is what happens when nothing else can.” ይላል። "ግጥም ምንም መሆን ሳይችል ሲቀር 'ሚሆን('ሚገለጥ) ነው" እንደማለት ነው።

ገጣሚው ጉደኛ ነው ሐሳብ ምልከታ አይነጥፍበትም በቼም ይች ዓለም እንቅብ ሙሉ ሐዘን ነው የደፋችብን ይህም ሐዘን ለማረጋገጫ -nihilism- Absurdism- ሚባሉ 'ርዕዮቶች ፈጥሯል። ፈረንሳዊው ደራሲ አልቤር ከሙ በካሊጉላ መንፈስ "ሰዎች ያለቅሳሉ ምክንያቱን ይህች ዓለም ፍትሃዊ ዐይደለችም" ይላል ፋሲል ደግሞ "ሰበብ" ሲል ተመስጦበታል።
የመጀመሪያ መጨረሻ
እየታወቀው ለሰው እየታየው ለሰው
ሞቱ እየታወሰው
ገና ሲወለድ ነው ቀድሞ 'ሚያለቅሰው።
ፋሲል ተካልኝ
[ጡዘት ገጽ-68]

ለምን? የክፍለ ዘመናችን ታዋቂው ደራሲ Anthony T. Hincks እንዳለው ነው። “Sometimes, I cry other people's tears”.(“አንዳንዴ የሌሎችን ዕንባ አለቅሳለሁ።”) የዓለሙ ፍጽምና ማነስ ሲያስቃስተው እንከተለዋለን።
ገለልተኛ ተመልካች ሳይሆን፥ ተቆርቋሪ ነው፤
በንጽረተ-ዓለሙ አፈጣጠር ምልዓተ ፍጽምና መጉደልና በሰው ኅላዌ የሚንፀባረቀው ሰቆቃ ያብሰለስለዋል? ዕንባን ተማምኖ ወደ ዓለም መጥቶ ማቃሰት ግጥሙ የተሸከመውን ህመም አከረረው።

ገጣሚው ስለ እግዜርና ሰይጣን በጻፈው ግጥም ለመመራመር ይጥራል።[ገጽ-45-46]
ለመኖር አምላክ ወይ ሰይጣን 'ሚል ምርጫ ያስቀምጣል። ያለነዚህ ዓለም ሁሌም ባዶ ነው።
ለገጣሚው ከምናቡና ከንጽጽሩ በዘለል ሐሳቦቹ የግጥሞቹ አጧዥ ናቸው።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እንዲህ በጀርባ አስተያየት ይላሉ "ግጥምን የተዋጣ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል 'ሐሳብ' የቃላት አመራረጥና አደራደር በመጨረሻም 'ምናባዊነት' እና 'ንጽጽር' ናቸው። የፋሲል የግጥም ስብስቦች፣ ስለባህል፣ ታሪክ፣ ስለፖለቲካ በጠቅላላው የሰው ልጅ የሚገኝበት ሁኔታ በተዋቡ ስንኞች ቀርበዋል።" እውነትም!
376 viewsSamuel Belete(bama), 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 13:18:08
375 viewsSamuel Belete(bama), 10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 13:56:36 የአልቤር ከሙ ወርቃማ አባባሎች
(በእኔ የተመረጡና የተተረጎሙ)
ሳሙኤል በለጠ

አልቤር ከሙ(ከ1913-1960) በሥነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት የተበረከተለት ትውልደ አልጀሪያዊ ፈረንሳዊ ደራሲና ፀሐፌ ተውኔት ነው።

እንደ የልቦለድ ደራሲ፥ ወግ ፀሐፊ፥ ጋዜጠኛና ፀሐፌ-ተዉኔት ስሙ የገነነ ነዉ። አልቤር ከሙ በሥራዎቹ የሕይወትን ወለፈንድ(the absurdity of life) በስፋት ዳሷል።

ምድር ላይ ብዙም ያልሰነበተው ከሙ ከሆነ ስፍራ በባቡር ለመሳፈር ሲጣደፍ ጓደኛዉ በሚኩና ካላደረስኩህ ብሎት እያሽከረከር ሲጓዝ በሌላ መኪና ይገጫሉ። ጓደኛዉ ሲተርፍ፥ ካሙ ግን በአደጋው ይሞታል። ልክ እንደ ፅሁፎቹ አሟሟቱም ፍልስፍናዉን -የሕይወት ወለፈንድን- ያደምቃል ይላሉ ብዙዎች ከአባባሎቹ ለዛሬ እንቀንጪብ:-

1.በዚህ ሁሉ መኃል መረዳት የቻልኩት በተሸፈነ ድቅድቅ ክረምት ውስጥም የተሸሸገ በጋ በውስጤ ተዳፍኖ መኖሩንና ማግኘቴን ነው::

2.እስከ ዕንባህ የመጨረሻ ጠብታ ጥረስ ኑር

3. ደስተኛ ለመሆን ስለሌሎች ከልክ በላይ መጨነቅ የለብንም።

4.በሁሉም ውብ ልብ ውስጥ አንዳንዴ ኢ-ሰብአዊ የመሆን ነገር አለ።

5.ሰዎች ያለቅሳሉ ምክንያቱም ይች ዓለም ፍትሐዊ አይደለችምና

6.እኔ ያለሁት ስላመጽኩ ነው።

7.ነጻነት የተሻለ የመሆን ዕድል እንጂ ሌላ አይደለም።

8. ልቦ-ለድ በምስል የተገለጸ ፍልስፍና እንጂ ሌላ ዐይደለም

9. በዓለም ላይ ያለው ክፋት ሁል ጊዜ ከድንቁርና የሚመጣ ነው፣ መልካም ህሳቤም ከሌለው የመጥፎ ስሜት ያህል ይጎዳል።

10. የሕይወት ትርጉም ምን መሰለህ(ለሽ) 'ራስህን ከማጥፋት የሚከለክልህ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እሱ የሕይወት ትርጉም ነው።

11. በየቀኑ የምትወስነው በጣም አስፈላጊው ውሳኔ 'ራስህን ላለመግደል መወሰን ነው።

12. ሕይወት የሁሉም ምርጫዎችዎ ድምር ውጤት ነው፣ ታዲያ ዛሬ ምን እያደረክ ነው?

13. ደስታና ወለፈን ሁለት የተለያዩ የአንድ ምድር ልጆች ናቸው፣ አይነጣጠሉም።

14. ራሴን ላጠፋ ወይንስ ቡና ልጠጣ? በመጨረሻ አንድ ሰው 'ራሱን ከማጥፋት ከሚያስፈልገው ድፍረት ይልቅ ለመኖር የበለጠ ድፍረት ያስፈልገዋል።

15. ተስፋ 'ኮ የለም እንፈጥረዋለን 'ጂ

16. የወለፈንድ(absurd) ጽንሰ-ሐሳብ አስፈላጊና የመጀመሪያው እውነት ነው።

17. እኔ የምወደው ሥዕሎችህን ሳይሆን ሥዕልህን ነው።
388 viewsSamuel Belete(bama), 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 23:27:13
መውደድ መወደድን ማክበር ያስተማረኝ
360 viewsSamuel Belete(bama), 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ