Get Mystery Box with random crypto!

سامحني يا الله

የቴሌግራም ቻናል አርማ samihni — سامحني يا الله س
የቴሌግራም ቻናል አርማ samihni — سامحني يا الله
የሰርጥ አድራሻ: @samihni
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196
የሰርጥ መግለጫ

💚 እንባችን ለዚያ ከፍራቸው የተነሳ
ካለቀስንለት እሳት እንደማይነካን ቃል ለገባልን
አላህ በስተቀር እንጂ ለማንም አትገባም ።
🌹 https://t.me/joinchat/AAAAAFk46EsH0CcLz0dXlQ
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 07:18:41 ድንቅ ታሪክ
ነብዩላሂ ሙሳ አላህን ያናገሩ ነብይ ናቸው፡፡
አንድ ጊዜ አላህን የጀነት ጎደኛዬን አሳየኝ ብለው ጠየቁ ፡፡
አላህም ወደ አንድ ደካማ ቤት እንዲሄድ የመንገዱን አቅጣጫ
ነግራቸው ሄዱ፡፡
የተባሉት ቤት ደርሰው አንኳክተው ገቡና ቁጭ አሉ፡፡
በእድሜ የገፉ እናትና አባቱን የሚካድም አንድ ወጣት ልጅ
ተመለከቱ፡፡
ልጁ ሽማግሌዎቹን በመካደም ተጠምዶዋል ያጎርሳቸዋል
ያጠጣቸዋል፡፡
በዚህ የተነሳ ቤቱ ማን እንደገባ እንኳን አላወቀም፡፡
ከጨረሰ በኃላም ዞር ብሎ ሲመለከት አንተ እንግዳ ቤት በኩል
ገባህ አላቸው?
ነብዩላሂ ሙሳ (ዐ.ሰ) አፉ በለኝ ይሉትና
ልጁም እንዲህ አላቸው
እነሱን እየካደምኩ ስለነበረ በዛ ምክንያት ነው ። ስትገባም
ያለየሁክ አላቸው።
ነብይ መሆናቸውን አላወቃቸውም፡፡ ልጁም እንግዳዬ ነህ እሺ ምን
ላድርግልህ ከነሱ የተረፈ አለ ትበላለህ አላቸው፡፡
( ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንም አልፈልግም ሸኘኝ በቃ አሉት፡፡
ወጪ ከወጡ በኃላም ነብዩላሂ ሙሳም(ዐ.ሰ) ልጁን ጠየቁት እነዛ
ሽማግሌዎች ምንህ ናቸው አሉት?
ልጁም ወላጆቼ ናቸው አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንም ሌላ ልጆች የላቸውም ቤተሰብም
የላቸውም አሉት፡፡ ልጁም አዎ እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንድን ነው የምትሰራው አሉት?
ልጁም ተሸካሚ ነኝ ተሸክሜ ባገኝሁት ብር እነሱን
ቁርስ፣ምሳ፣እራት ሳላሳልፍባቸው እየገዛሁ እካድማቸዋለሁ
አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ወላጆችህ ስታስደስታቸው ምን እያሉ
ነው ሚመርቁህ አሉት፡፡
ልጁም አይ እሱስ ከባድ ነው የማለገኝውን ነው የሚመርቁኝ
በተለይ እናቴ አንድ ነብይ አለ ደረጃህን በጀነት ከነብዩ ሙሳ ጋር
ያድርግልህ ትለኛለች፡፡ ስለምትወደው ነው እንጂ እኔ እንኳን ከነሱ
እኩል መሆን አልችልም አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ)
ታውቀዋለህ ግን ነብዩላሂ ሙሳን አሉት?
አላውቀውም!
እንዳለ እሰማለሁ እንጂ አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም (ዐ.ሰ) በል እንግዲህ እኔ ነብዩላሂ ሙሳ ነኝ
እኔም የጀነት ጎደኛህ ነኝ አላህን
የጀነት ጎደኛዬን ማን እንደሆነ አሳየኝ ብዬው ነው!
ዛሬ አንተ መሆንህን ያሳየኝ አሉት።

t.me/samihni
11 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:18:14
12 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:30:48
t.me/muselimnegn
23 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:55:58 ተአምረኛው የዘምዘም ውሃ
★የውሃው ሌቨል 10•6 ጫማ ከወለል በታች ሲሆን
★በሰከንድ 8000 ሊትር እየመነጨ
★ሳያቋርጥ ለ24 ሰአት ወደ ላይ ቢገፋ
28800×24=691•2 ሚሊየን ሊትር በቀን ይለቀቃል ማለት
ነው። # ሱብሃነላህ
★ የሚገርመው እራሱን መልሶ ለመተካት የሚፈጅበት 11 ደቂቃ
ብቻ ነው። አጂብ አትሉም
★ምንም አይነት ከለርና ሽታ ባይኖረውም የራሱ የሆነ ጠአም
አለው ።
★ማንኛውም ውሃ ጥምን ሊቆርጥ ይችላል ይሄ ግን ረሀብንም
ያስታግሳል።
★በውስጡ ካልሺየም ማግኒዥየም ፍሎራይድ እና ሌሎችነም
ንጥረነገር በመያዙ አንድ ሰው ይሄን ብቻ እየጠጣ መቆየት
ይችላል።
★የዚህ ውሃ አንድ ጠብታ የሌላ ውሃ አንድ ሺ ጠብታን የተለመደ
የውሃ ባህሪነት ይቀይረዋል።
★ጠአሙና ጥራቱ በፍፁም ለምን ለዚህ ሁሉ ከፍለ ዘመናት
አንዴም አለመቀየሩ ሳይንስ ሊደርስበት ባይችልም በዚህ ዙሪያ
ያለው ጥናትና ምርምር ግን እንደቀጠለ ነው።
★ከሁሉም በላይ የሚገርመው ይሄ ውሃ ሲሞላ እራሱ የሚቆም
ሲሆን ከተመደበው በላይ አይመነጭም።
በቀን 691 ሚሊየን ሊትር እየመነጨ በአላህ ተአምር እና ፍቃድ
የሀጀራን ምኞት አስታኮ ባለበት ባይቆም ኖሮ አለም በዚህ ውሃ
አትጥለቀለቅም ነበርን?
ግን እናት ሀጀራ እንዳያልቅባት ፈርታ እንዳያጥለቀልቀን
ገደበችው። ቁም ፣ ዝም በል፣ አትፍሰስ አለችው። ዘም ፣ዘም፣ ።
ተአምረኛው ፀበል ከውሃም በላይ ነው።

t.me/samihni
52 views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:55:36
39 views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 20:05:51 ልብ የሚነካ ታሪክ
---------//---------
በፀፀቷ በጣም የምትታወቅ ሰሀባ ነበረች ስሟ ( ጋሚዲያ )
ይባላል የዚህችን ሰሀብይ ታሪክ ብዙ ሙስሊሞች ያውቁት ይሆናል
።እቺ ሴት ሰሀቢይ ናት፣የነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) ባልደረባ ናት። ሰሀባ
አግብታ ነው የምትኖረው።
እስልምናን የተቀበለችው ከነቢዩ እጅ ነው ፣እቺ ሰሀቢይ ዚና ላይ
ትወድቃለች ፣ሰሀቢይ ናት ግን ዚና ላይ ወደቀች ዚና ላይ ወደቀችና
ወደ ነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) መጣች ለነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) እንዲህ አለች
ጠሂርኒ ያረሱለላህ ፣አንተ የአላህ መልእክተኛ አፅዳኝ አለች
እቺ ሴት አፅዳኝ የምትለው በድንጋይ ቀጥቅጠህ አስገድለኝ ነው
የምትለው።
አግብቶ ዚና የሰራ ሰው ቅጣቱ ፣ተቀጥቅጦ በድንጋይ መገደል ነው
አፈር ይቆፈርለታል እስከ ወገቡ ከዛም በድንጋይ ተወግሮ ይሞታል
አላህ ወንጀሉን ይምርለታል።
እቺ ሴት ግን አፅዳኝ ያረሱለላህ አለች። ነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ )
አዘኑላትና ተመለሺ ወደ አላህ ቶብቺ ( ተውበት ) አድርጊ አሏት ፣
በዚህ መሰረት እቤቷ ገብታ አስተግፊሩላህ ብትል ይበቃት ነበር
።ባሏ ሳያቅ፣ነቢዩ ሳያቅ፣ህዝቧ ሳያቅ አላህ ይምርታል ።
እሷ ግን የመፀፀቷ ብዛት ይህ አይበቃኝም አለች ።አንተ የአላህ
መልእክተኛ ሆይ ( ማኢዝ ኢብኑ ማሊክን ) እንደመልስከው
ልትመማሰኝ ትፈልጋለህ ወይ፣ አልቀጣሽም ብለህ ልትመማሰኝ
ነው ወይ ? ወላሂ እኔ ከዚና አርግዣለሁ ፈጠሂርኒ ( አፅዳኝ ) ነው
የምልህ ያረሱለላህ አለች።
ከዛም ነቢ ( ሰ.ዓ.ወ ) ተገረሙና እኮ አንቺ ከዚና አርግዘሻል ?
አዎ አርግዣለሁ አፅዳኝ አለች።
ነቢ ( ሰ.ዓ.ወ ) ምን አሏት ተመለሺ ልጁን ያረገዝሽውን
ስትወልጂው ነይ አሏት ።
እራሷን ለነቢዩ አጋለጠች ዚና እንደሰራች ባሏ አወቀ ፣ሀገር
አወቀባት ፣ሙስሊሙ ማህበረሰብ አወቀባት
እሷ ግን የፈለገችው ሀገር የፈለገ ይበል እኔ መፅዳት ነው
የምፈልገው አለች።
ከዛ በኋላ ዘጠኝ ወር ሙሉ እያለቀሰች እየነደመች ቆየችና በዘጠኝ
ወሯ ልጇን ወልዳ ይዛ መጣች።
ከነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) ፊት ቆመችና ኢኸው ወልጄዋለው አንተ
የአላህ መልእክተኛ አፅዳኝ አለች
ከዛም ከነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) ምን አሏት በይ ሂጂ ተመለሺ ልጅሽ
ጡት ሲጥል፣ ምግብ መብላት ሲጀምር ይዘሽው ነይ አሏት።
አንድ ህፃን ምግብ ለመጀመር ሁለት አመት ይፈልጋል ጡት ትቶ
ምግብ ለመጀመር፣ እናም እቺ ሴት ተጨማሪ ሁለት አመት
አሳለፈች ቤት ቁጭ ብላ እያለቀሰች ፣እየተፀፀተች ።
ሁለት አመት ከቆየች በኋላ ይሄን ህፃን ይዛው መጣች መብላት
መጀመሩን ለማሳየት እጁ ላይ ቁራሽ ዳቦ አስይዛው
ያነቢየላህ ይኸው ጡት አቁሟል ፣መብላት ጀምሯል አፅዳኝ አለች
ነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) እንዲህ ስትላቸው ሶስት አመት መመላለሷን
ሲያዩ ህፃኑን ልጅ ተቀበሏትና ለአንድ አንሳር ሰጡት፣ ከዛም ለሷ
ጉድጓድ ቆፈሩላት ጉድጓድ ውስጥ ገባች፣
ሙስሊሙ በድንጋይ እየቀጠቀጠ ይገድላት ጀመር፣ ከመቷት
ውስጥ አንዱ ካሊድ ኢብኑ ወሊድ ነበር ።
በድንጋይ ሲመታት ደሟ ተፈናጥሮ እሱ ላይ ተረጨ በዚህ ጊዜ
ይሰድባት፣ይዘልፋት ጀመር ።
ነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) በካሊድ እጅግ በ አዘኑበት እና ወደሱ ዘወር
ብለው ተው ባክህ አንተ ካሊድ እሷኮ አሁን የተወበተችው
ተውበት ለአንድ ህዝብ ብናከፋፍለው በበቃቸው ነበር ። አሉት
ከዛም ነቢዩ ( ሰ.ዓ.ወ ) ሰገዱባትና ተቀበረች

t.me/samihni
59 views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 20:05:47
43 views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 14:23:40 አሳዛኝ እና ድንቅ ታሪክ
▰▰▰✿▰▰▰
አንድ አባት ከሀምሳ ዓመት በፊት ከአባቱ ጋር ሃጅ ያደረገበትን
አጋጣሚ
አስታውሶ ለልጁ እንዲህ በማለት ታሪኩን ያወጋዋል ....
:
ከአንድ ቅፍለት (ጀመዓ) ጋር በመሆን ወደ ሃጅ ጉዞ በማድረግ ላይ
ሳለን አባቴ መጰዳዳት ፈለገና ከግመል አወረድኩት ።
:
«አባቴም» ልጄ ሆይ ከቅፍለቱ ጋር በመሆን ተጓዝ እኔ
እንደጨረስኩ
እደርስብሃለሁ አለኝ እና...ወደ መጰዳጃ ቦታ ሄደ፣ እኛም
ጉዞዋችንን
ቀጠልን ።ጥቂት እንደተጓዝን ወደ ኋላ ዞር ብዬ ስመለከት
«አባቴን» በጣምእርቀነው ሄደናል ።
:
እኔም ቶሎ ብዬ በፍጥነት ወደ አባቴ ሄድኩኝ ፣ድረስኩኝና አባቴን
በጀርባዬ አዝየው ወደ ቅፍለቱ መመለስ ጀመርኩ ፣አባቴን አዝየው
እየተመልስኩ ሳለሁ የአባቴ እንባ እርጥበት በጀርባዬ ሲወርድ
ተሰማኝ።
:
ከዛም ለአባቴ ። በአላህ ስም እምላለሁ «አባዬ» አንተ ከጀርባዬ
ከሚወርደው እርጥበት የቀለልክ ነህ ።አልከበድከኝም ለምን
ታለቅሳለህ ?? አልኩት
:
አባቴም አይ ልጄ ለዛ አይደለም ያለቀስኩት እኔም እዚህ ቦታ ላይ
አባቴን አዝዬ ወደ ሃጅ ጉዞ አድርጌ ነበር እሱን አስታውሼ ነው
ያለቀስኩት ሲሉ መለሱለት ።
:
ለወላጆቹ መልካም ዋሉ ።ልጆቻቹ መልካም
ይወሉላቹሃል። ታሪኩን ከወደዱት እርሶጋ ብቻ እንዲቀር አያድርጉ
ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶዎ ያድርሱ

t.me/samihni
45 views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 14:23:28
38 views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 08:44:59 በከተማዋ አንድ በጣም ምስኪን ሰውዬ ነበር።
ብር ተበድሮ ተበድሮ...መክፈል ያቅተውና ሀሳብ ጭንቀት እረፍት
ያሳጣዋል።
ብድሩ 500 ዲናር ደርሶበታል..እናም አንድ ቀን አበዳሪዎቹ
መጥተው በአንዴው ያፋጥጡት ጀመር ...
እሱም ወደ አንድ ነጋዴም ይሄድና በተወሰነ ግዜ እንደሚመልስለት
ቃል ገብቶ ከሱ 500 ዲናር ይበደርና ላስጨነቁት አበዳሪዎቹ
መለሰላቸው።
ቀናት እና ሌሊቶች ይነጉዱ ጀመር ባላሰበው መልኩ የቀጠሮው
ቀን እየተቃረበ መጣ..
ግን ይህ ምስኪን ምንም ያዘጋጀው ነገር የለም።ይልቁንም
ገና ለገና ለቤተስቡ ድጎማ ለሌላ ብድር ተዳርጓል።
ቀኑ ደረሰ ያአበዳሪ መጣና ብሩን ሲጠይቀው ብድሩን መመለስ
አልቻለም።
ነጋዴውም ለከተማዋ ቃዲ/ፍርድ ቤት ዳኛ ጉዳዩን ያቀርብና
ሰውየውን ችሎት አስቆመው...
የፍርድ ቤቱም ዳኛ ጉዳዩን ከተመለከተ በኋላ ተበዳሪው ብድሩን
እስኪመልስ ድረስ እስር ቤት እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
ይህ ምስኪንም ዳኛውን፦
"እባክህ አንድ ቀን ስጠኝ መታሰሬን ለባለቤት እና ለቤተስቤ
ልንገራቸው በፍለጋ እንዳይደክሙ" ይለዋል።
ዳኛውም "ዋስ አምጣ" አለው።
ያን ግን ግዜ ይህ ምስኪን ዋስ ሚሆነው ሰው በአጥገቡ
አላገኘም...
"የኔ ዋስ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ ናቸው። እነሱን ዋስ አድርጌ ነገ
ባልመጣ ከሳቸው ኡመት እንዳልሆንኩ በዱንያም በአኼራም
መስክርብኝ" አለው
ዳኛውም የዋስትናውን ትልቅነት ተረድቶ ዋስትናውን ተቀበለ።
ሰውየውም ወደ ቤቱ ተመለሰ
የሆነውን ሁሉ ለባለቤቱ ነገራት።
ሚስቱም እንዲህ አለችው፦
"በል ከፍርድ ቤት በረሱል ሰ.ዐ.ወ ዋስትና እንደወጣህ ሁላ አሁን
በሳቸው ላይ አብረን ስለዋት እናውርድ አላህ በሳቸው በረካ ከዚህ
ጭንቀት ሊያወጣን ይችላል። አለችው
(ገራሚ ሚስት ናት ወላሂ)
ከዛም በዚህ ተስማሙ አብረው ሰለዋት ማለትም ጀመሩ....
የሰው ልጅ ደካማ ነውና እዛው እንቅልፍ አሸንፎ ወስዳቸው።
ከዚያም በዚህ ሰውየ በህልሙ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ይመጡና፦
"ሲነጋ የከተማዋ አስተዳዳሪ ጋ ሂድና ሰላምታዬን
አድርስልኝ።እንዲህም በለው፦ {ረሱል ሰ.ዐ.ወ ብድሬን
እንድትከፍልልኝ አዘውሀል። ምናልባት ምልክትህ ምንድነው ካለህ
አስተዳዳሪው ሁሉ ቀን በኔ ላይ 1000 ሰለዋት ያወርዳል ዛሬ
ቁጥር ላይ ተሳስቶም ነበር አላህ እንደሞላለትም ነገረው} " አሉት።
ሰውየው ገና ከመንጋቱ አስተዳዳሪው ቤት ሲሮጥ ደረሰ።
አስተዳዳሪው ዘንድ እንደደረሰ
"የአላህ መልዕክተኛ ሰላም ብለውኻል። የእኔንም ብድር
እንድትከፍልልኝ አዘውኻልም።"
አለው
አስተዳዳሪው፦ስንት ነው ብድርህ?
ሰውየው፦500 ዲናር
አስተዳዳረው፦እውነት ስለመናገርህ ምንድነው ምልክቱ?
ሰውየው፦ሁለት ምልክቶች አሉኝ አንደኛው አንተ በቀን 1000
ሰለዋት ታወርዳለህ...
አስተዳዳሪው፦ልክ ነህ (አንገቱን ደፍቶ እያለቀስ)
ሰውየው፦ሁለተኛዋ ደሞ ትናንት ስለዋት ስታወርድ በቁጥር
ተሳስተህ ነበር እሷንም አላህ ሞልቶልሀል።
አስተዳዳሪው እያለቀሰ ልክ ብለሀል አለው።
ኪዚያም ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት 500 ዲናር እንዲሰጠው አዘዘ
ከግል ንብረቱ ደሞ 2500 ዲናር ሰጥቶ ይህ የኔ ስጦታ ነው ብሎ
አሰናበተው።
ሰውየው ከአስተዳዳሪው ቤት ፊቱ በደስታ ተሞልቶ ይወጣና
ትናንት የገባውን ቃል ሊሞላ ሩጫ ወደ ፍርድ ቤት ይጀምራል...
ፍርድ ቤት ደረሰ...ዳኛው ጋ ሲገባ ዳኛው በከረጢት ብር ይዟል።
ብድርህን እኔ እከፍልልሀለሁ ይህን 500 ዲናር ያዘው ስጦታ
ነው። ባንተ በረካ ረሱልን ዐ.ሰ አይቻለሁ "የዚህን ሰው ሀጃ
ከተወጣህለት የውመል ቂያማ ሀጃህን እንወጣልሀለን" ብለውኛል
አለው።
ያን ግዜ አበዳሪውም ድንገት ብቅ አልና እንዲህ አለ፦" ብድሩን
አውፍ ብየዋለሁ ይህ 500 ዲናር ከኔ ስጦታ ነው ረሱል ዐ.ሰ
በህልሜ "ይህን ሰው አውፍ ካልከው የቂያማ እለት አውፍ
ትባላለህ" ብለውኛል አለ።
ሰውየው ደስታውን መቆጣጠር አቅቶት ወደ ባለቤቱ ሩጫ ቀጠለ
የሆነውን ሁሉ አጫወታት..
በአላህ እርዳታ ትናንት በ500 ዲናር ሊፈረድበት የነበረ ሰውዬ ዛሬ
4000 ዲናር ይዞ ቤቱ ገባ...
__
ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶዎ ያድርሱ

t.me/samihni
75 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ