Get Mystery Box with random crypto!

Sami Habib

የቴሌግራም ቻናል አርማ sami_habib — Sami Habib S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sami_habib — Sami Habib
የሰርጥ አድራሻ: @sami_habib
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 513
የሰርጥ መግለጫ

ያገደኝ በሙሉ፤
ያስቆመኝ በሙሉ፤
የህይወት ወደቡ፤ ጥጉ እየመሰለኝ፤
ዘንድሮም አራህማን፤
ያገደኝን ወጀብ፤
ርብራብ አድርጎ፤ ወንዙን አሻገረኝ።
🔰ሀሳብ መቀበያ @Sami_Habib_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 10:31:10 እንኳን ለተወደደውና ለተከበረው ለ1,443ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢዱል-አድሓ በዓል አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል
ዒዱኩም ሙባረክ
http://t.me/Sami_Habib
194 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:30:20 በሙሴ ሕግ አስቀድሞ የተወለደው የበኲር ልጅ ለያህዌህ ይሆናል፥ የበኵር ልጅ በእርሱ ፋንታ እንስሳ ይታረዳል። ይህንን ሕግ አብርሃም ፈጽሞታል፦
ዘጸአት 13፥2 በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፈት በኵር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው።
ዘፍጥረት 26፥5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን "ሕጌንም ጠብቆአልና"።

አብርሃም ሕጉ ከጠበቀ የበኵር ልጁ ሊሰዋ ነበር ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሁሉንም ነገር ዐዋቂ ነው፥ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው ይህ አንዱ አምላክ ቁርኣንን ወደ ነቢያችን"ﷺ" አውርዷል፦
33፥54 አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው። فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
25፥6 «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

"ነበእ" نَبَأ የሚለው ቃል "ነበአ" نَبَّأَ ማለትም "አወራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ነቢብ" "የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ ከአሏህ ዘንድ የሩቅ ወሬ የሚወርድለት ሰው "ነቢይ" نَبِيّ ሲባል "ነባቢ" "የሩቅ ወሬ አውሪ" ማለት ነው። ከአሏህ ዘንድ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከወረደው የሩቅ ወሬ አንዱ ስለ ኢብራሂም እና ስለ ቤተሰቡ ነው፦
26፥69 በእነርሱም ላይ የኢብራሂምን "ወሬ" አንብብላቸው፡፡ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ إِبْرَاهِيمَ
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

ኢብራሂም ሊሰዋው የነበረው ልጅ ኢስማኤል እንደሆነ ከቁርኣን ብቻ ሳይሆን ከባይብልም መለኮታዊ ቅሪት ከላይ እንዳብራራነው እናገኛለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
http://t.me/Sami_Habib
95 views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:29:56 የዕርዱ ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

"ኢሽማኤል" יִשְׁמָעֵאל‎ የሚለው ቃል የሁለት ዕብራይስጥ ቃላት ውቅር ነው፥ "ኢሽማ" שָׁמַע ማለት "ይሰማል" ማለት ሲሆን "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ኢሽማኤል" יִשְׁמָעֵאל‎ ማለት "አምላክ ጸሎቴን ሰማኝ" ማለት ነው፥ ይህ ስም የወጣበት ምክንያት አብርሃም፦ "አቤቱ ያህዌህ ሆይ! ምንን ትሰጠኛለህ? ያለ ልጅ እሄዳለሁ” ብሎ ለለመነው ልመና መልስ ፈጣሪም፦ "ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል" በማለት ይመልስለታል፦
ዘፍጥረት 15፥2 አብራምም፦ አቤቱ አቤቱ ያህዌህ ሆይ! ምንን ትሰጠኛለህ? ያለ ልጅ እሄዳለሁ።
ዘፍጥረት 15፥4 እነሆም የያህዌህ ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

ፈጣሪም ከአብርሃም ጉልበት ስለወጣው የአብራኩ ክፋይ ሲናገር፦ "ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ" በማለት ጸሎቱን ሰምቶታል፥ አብርሃምም አምላክ ጸሎቱን ስለሰማው የልጁን ስም "እስማኤል" ብሎ ጠራው፦
ዘፍጥረት 17፥20 ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ "ባርኬዋለሁ"።
ዘፍጥረት16፥15 አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።

"ልጁን" የሚለው ይሰመርበት! አንዳንድ ዐላዋቂ የክርስትና መምህራን እስማኤል የአብርሃም ልጅ እንዳልሆነ እና እንዳልተባረከ ሲናገሩ ስንስማ ምን ያክል ባይብልን እንዳማያነቡ ያሳብቅብባቸዋል። አጋር የሳራ ባሪያ ብትሆንም ለአብርሃም ሚስቱ ነእንደነበረች እሙን እና ቅቡል ነው፥ ስለዚህ ልጇ ለኢብራሂም ሕጋዊ ልጅ ነው፦
ዘፍጥረት 16፥3 የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።

አጋር የሳራ ባሪያ የነበረች መሆኗ በእስማኤል ልጅነት ላይ የሚፈይደው አሉላዊ ቁብ የለውም። ለምሳሌ ባላን የራሔል ባሪያ ስትሆን ለያዕቆብ ግን ሚስት ነበረች፥ ከእርሷም የተወለዱት ዳን እና ንፍታሌም ሕጋዊ ልጆች ናቸው፦
ዘፍጥረት 30፥4 ባሪያዋን ባላንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ለእርሱ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ደረሰባት።

በተጨማሪም ዘለፋ የልያ ባሪያ ስትሆን ለያዕቆብ ግን ሚስት ነበረች፥ ከእርሷም የተወለዱት ጋድ እና አሴር ሕጋዊ ልጆች ናቸው፦
ዘፍጥረት 30፥9 ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባሪያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው።

ያዕቆብ አሥራ ሁለት ሕጋዊ ልጆች ያሉት ከባላን እና ከዘለፋ የወለዳቸውን ልጆች ጨምሮ እንደሆነ ሁሉ አብርሃምም ከሳራ ባሪያ ከሚስቱ ከአጋር የወለደው የበኲር ልጁም ሕጋዊ ልጁ ነው፦
ዘፍጥረት 17፥26 በዚያው ቀን አብርሃም ተገረዘ፥ እንዲሁ ልጁ እስማኤልም።
ዘፍጥረት 25፥9 ልጆቹ ይስሐቅ እና እስማኤል.....ቀበሩት።
ዘፍጥረት 16፥15 አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።

ይህ የበኲር ልጅ እስማኤል ሁለተኛው ልጅ ይስሐቅ እስኪወለድ ድረስ የአብርሃም ብቸኛ ልጅ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥16 እንዲህም አለው፦ ያህዌህ፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ ብቸኛ ልጅህንም አልከለከልህምና። וַיֹּ֕אמֶר בִּ֥י נִשְׁבַּ֖עְתִּי נְאֻם־יְהוָ֑ה כִּ֗י יַ֚עַן אֲשֶׁ֤ר עָשִׂ֙יתָ֙ אֶת־הַדָּבָ֣ר הַזֶּ֔ה וְלֹ֥א חָשַׂ֖כְתָּ אֶת־בִּנְךָ֥ אֶת־יְחִידֶֽךָ׃

"ያኺድ" יָחִיד ማለት "ብቸኛ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ የተቀመጠው ወሳኝ ቃል "ያኺድከ" יְחִידֶֽךָ ማለት "ብቸኛክ" ማለት ሲሆን የበኲር ልጅ ሌላ ልጅ እስኪወለድ ድረስ ለወላጅ ብቸኛ ልጅ ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም ለብቸኛ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል። אֲשֶׁר־דָּקָ֑רוּ וְסָפְד֣וּ עָלָ֗יו כְּמִסְפֵּד֙ עַל־הַיָּחִ֔יד וְהָמֵ֥ר עָלָ֖יו כְּהָמֵ֥ר עַֽל־הַבְּכֹֽור׃

እዚህ አንቀጽ ላይ የመጀመሪያ ልጅ ብቸኛ ልጅ መባሉን ልብ በል! ስለዚህ አብርሃም ሊሰዋ የነበረው የዕርዱ ልጅ የመጀመሪያ ልጁን ነው። ሲጀመር የዕርዱ ልጅ ይስሐቅ ቢሆን ኖሮ "ብቸኛ ልጅህን" የሚለው ትርጉም ይሰጣልን? ሲቀጥል ይስሐቅ ከመወለዱ በፊት አድጎ ዘር እንደሚኖረው ለአብርሃም ተነግሮታልም ያውቃልም፦
ዘፍጥረት 17፥19 ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘላለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።

ታዲያ አብርሐም ልጁ ይስሐቅ ሳይወለድ ዘሩ እንደሚቀጥል እያወቀ ፈተና ነው ማለት ትርጉም ይኖረዋልን? ምክንያቱም ልጅህን ዕረድልኝ ፈተና ነው፥ ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ እና ብቻ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ ያህዌህ አብርሃምን "ፈተነው"።
87 views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 22:37:42 ... #ይድረስህ_ብለሀለች_በኑር

#ለካ_ብዙ_ቻልኩህ__!!
----------------------------------
ትሆናለህ ብዬ አይቸህ በስስት፡
ህልሜን አጨለምከው ተቀየርክ እንደ እስስት፡
ጠንካራ ነህ ብዬ አምኘ ብቀርብህ፡
በጥርስህ እየሳቅክ አራቅከኝ ከልብህ፡
#እኔ_የዋኋ_ግን__!!
ምንም ሳላደርግህ ልሒድ ብትል ሸኘሁ፡
ይቅርታ ሳትጠይቅ ብትመጣ ተሞኘሁ፡
በመውደድ ታስሬ እየተሰቃየሁ፡
ልገፋህ አልቻልኩም አይንህን እያየሁ፡
~~~
#አንተ_ግን__!!
የለፋሁበትን ንፁህ ሀብቴን በልተህ፡
ከኔ አንደበት በላይ የሰው ወሬ ሰምተህ፡
በውሸት ተሸነፍክ እውነታውን ትተህ፡
ስንት ስንት ነገር ያኔ እንዳልተናገርክ፡
በቃልህ ፅና እንጂ አሁን ለምን አፈርክ!!
------------------------------------------
በቃልህ ታስሬ ሀላልህ ሆኘልህ፡
ላንተ መናገሻ ልቤን ከፍቸልህ፡
በጋለው ፍቅራችን ብዙ እቅዶች ፅፈን፡
ኢንሻ አሏህ ብለን ብዙ ህልም ነድፈን፡
ስንት ችግሮችን ስንት ነገር አልፈን፡
ምን ተሰማህ ዛሬ ስንለይ ተኳርፈን!!?
-------------------------------------------
የህይወትን ወጥመድ ስንት አቀበት ወጥተን፡
ወድጀህ ወደኸኝ ብዙ ነገር ሰርተን፡
በእምነታችን ደምቀን በሀቅ ላይ ፀንተን፡
ስንት ሀዘኖችን አብረን ተሰቃይተን፡
ዛሬ ግን ያን ሁሉ ግሩም ጊዜ ረስተን፡
ወዳጅ መሳይ ጠላት ነገረኛ ሰምተን፡
ሳናስበው ድንገት ቀረን ተለያይተን፡
~
#እንደው_ምን_ተሰማህ..!

ይህንን ስታደርግ እኔ መች ተከፋሁ!!
በል እስኪ ንገረኝ አሁን ምን አጠፋሁ!?
ስንት ስታደርገኝ ስትነክሰኝ መች ሸሸሁ፡
ፍቅር አስገድዶኝ ከቤትህ አመሸሁ፡
ብትለወጥ ብዬ ብዙ ዘመን ታሸሁ
በእውነተኛ ፍቅር ወስኘበት የምር፡
አላህም አስቻለኝ በረታሁ ለታምር፡
~~
ከምላስህ በላይ በተግባር ነገርከኝ፡
ጥለህ እያነሳህ ገድለህ እያከምከኝ፡
አመልህ ሳይጠፋኝ ስንቴ ሸነገልከኝ!?
~~
ከልቤ እንደገባህ ሁሌ እየነገርኩህ፡
ውሸት ቅዠትህን ደጋግሜ ቻልኩህ፡
ላያስችል አይሰጥም በሚል ጠባብ ተስፋ፡
ባንተ ነው ያየሁት ሆድ ካገር ሲሰፋ፡
~~
ስንት እየበደልከኝ እኔ እየታገስኩህ፡
ስትሰድበኝ ፀጥ ስል እያመሰገንኩህ፡
አንተ ስትርቀኝ እኔ እየቀረብኩህ፡
ጥላቻ ስትሰብከኝ እኔ እየወደድኩህ፡
ከአቅሜ በላይ ሆነ አሁን ግን ራኩህ፡
አትረዳም እንጂ ለካ ስንቱን ቻልኩህ!!?
~~
በቃኝ አሁንማ ከልቤ ተሰወርክ፡
ተቀይረህ እንጂ ያኔ እንድህ መች ነበርክ!!
የትዳር ሚስጥሩ አላማና ግቡ ፡
ለኔ መብረቅ ሆኖ ጀምሯል ተግቡ፡
ባለኝ ማንነት ልክ እኔ እየወደድኩህ!!
አብሬ ለመኖር ሁሌ እየነገርኩህ!!
በይሆናል ተስፋ ለካ ብዙ ቻልኩህ!?
~~~~
#አሁን_ግን_በቅቶኛል.....
#የሚለው_ሰው_በዛ...ለምን....!?
~~
http://t.me/Sami_Habib
190 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 10:20:41 #ደጃል___!!(በኑር)
<~~~~>
ካፊር የሚል ፅሁፍ ግንባሩ ላይ ያለው፡
ከአሏህ ባሪያ ውጭ ማንም የማይችለው፡
አስፈሪ ፍጡር ነው አንዳይኑ የጠፋ፡
ያየውን የሚረግጥ ጥመት እየተፋ፡
የአንድ ቀን ቆይታው አመት የሚሰፋ፡
ወር ያክል ሚቆይ የሁለተኛው ቀን፡
የመከራ ክምር የኑሮ ሰቀቀን፡
ሶስተኛው ቀን ደግሞ ሳምንት የሚለጠጥ፡
አለምን የሚቃኝ አርፎ እማይቀመጥ፡
ስቃዩ የሚገዝፍ ከነድድ ረመጥ፡
~~~~
እነዚያን እርኩሶች አይሁድ አስከትሎ፡
በውሸት ሰበካው ሴቶችን አታሎ፡
ተውሒድን ለማጥፋት የሚራመድ ቶሎ፡
አስፈሪ ፍጡር ነው ለመግለፅ ይከብዳል፡
አመንኩብህ ላለው ጀነት ይመነዳል፡
እምቢ ላለው ደግሞ እሳት ይማግዳል፡
አሏህ ግን ጀነቱን በእሳት ቀይሮበት፡
ጀሀነቡን ደግሞ ጀነት አድርጎበት፡
እሱን አስደስቶ ጀነት የከተተው፡
በእሳት ይሰቃያል ጉዱን ተመልከተው፡
ደግሞ በርሱ አምፆ ከእሳት የተጣለ፡
ጀነት ነው ማረፊያው እንደዚህም አለ፡
#ደጃል__!!
እየተጃጃለ አርባ ቀን ይቆያል፡
የቀኖቹ ርዝመት ግን በጣም ይለያል፡
አመትም፣ሳምንትም፣ወርም ያስቆጥራል፡
በዚህ ሁሉ ጊዜ እኔ ነኝ ፈጣሪ እያለ ይጣራል፡
አስነዋሪ ቃላት ደፍሮ ይናገራል፡
------------------------------------------
ይላል ደፋር ሆኖ ሙታን አስነሳለሁ፡
አባት እናትህን ህያው አደርጋለሁ፡
ፊትና አርጎታልና አሏህ ለፍጥረቱ፡
ያስመስልብሀል ይሳካል ጥረቱ፡
የዚህን ጊዜ አንተ በተውሒድ ካልፀናህ፡
ለይምሰል ከሆነ ዱሮም እስልምናህ፡
የደጃል ፈተና ያሰናክልሀል፡
ውሸቱ ቅጥፈቱ እዛው ያስቀርሀል፡
አሏህን አመፀህ በርሱ ትገባለህ፡
የደጃሉል ካዚብ ጭፍራ ትሆናለህ፡
ከዚህ ሸይጧን ፊትና አሏህ ይጠብቀን፡
መከራው ከባድ ነው ያበዛል ሰቀቀን፡
---------------------------------------
#ደጃል___!!
በቆይታው ሁሉ ፊትና እያሰራጨ፡
ውሸት እያስፋፋ ሀቅ እያቀጨጨ፡
እንደዚህ እያለ ህዝቡን ሲያሰቃየው፡
ውሸት እየነዛ ከእውነት ሲለየው፡
የሙስሊሞች መሪ መህዲ ኢማማችን፡
ስሙ እንደ ስሜ ነው ያሉት ነብያችን፡
አይዟችሁ እያለ አማኝን ሲያበስር፡
ሸያጢኑ ደጃል ሲያሳድደው ከስር፡
በቀኝም በግራ በመለክ ታጅበው፡
ከላይ ይወርዳሉ በድምቀት ተውበው፡
ውሸት ሲንፀባረቅ እውነት እየከሳ፡
በዚህ ጭንቅ ሰአት ይወርዳሉ ዒሳ፡
ኢሳን ሲመለከት ደጃል ይራወጣል፡
በፍርሀት ብዛት እንደ ጨው ይቀልጣል፡
ባቡ ሉድ ሲደርስ ይገድሉታል ኢሳ፡
ያ የኢስላም ነብይ የተውሒዱ አንበሳ፡
በኢሳ ምክንያት ደጃል ይገደላል፡
መከራ የናጠው አማኝ እፎይ ይላል፡
#ደጃል__!!
አላህ የጠበቀው ከፊትናው ይድናል፡
እድለ ቢስ ደግሞ በርሱ ይፈተናል፡
አሏህን ዘንግቶ በዚህ እርጉም ያምናል፡
#ደጃል__!!
አይገባም በፍፁም መካና መድና፡
ጠባቂያቸው አምላክ የእውነት ነውና፡
አለምን ይቃኛል ከነዚህ በስተቀር፡
ምድር የተባለ ማንም ምንም አይቀር፡
ግዙፍ ክፉ ፍጥረት መልኩ የሚያስፈራ፡
እርምጃና እሩጫው ፈጣን ከጦያራ፡
እመኑብኝ ብሎ ህዝብን የሚጣራ፡
አስተሳሰቡ እውር አይኑም ነው ጠንባራ፡
#ደጃል___!!
~~
የሚል ከንቱ ፍጡር አምላካችሁ እኔ፡
በጣም መጥፎ ፍጥረት ጨካኝ አረመኔ፡
ዘራፊ ቀማኛ ሸረኛ ወመኔ፡
አሏህ ይድረስልን ከደጃል ፈተና፡
ነብያቱ ሁሉ ከርሱ ፈርቷልና፡
አሏህ ይጠብቀን ከደጃል ፈተና፡
#ደጃል__!!
አያ ሱረቱል ከህፍ መቅራቱ ይበጃል፡
በፀሎት መጠንከር መልካም ነውኮ ጃል!
ፈጣሪ ነኝ ብሎ ደፍሮ የሚጃጃል፡
አሏህ ይድረስልን ብዙ ሰው ይፈጃል፡
በአጭሩ ስገልፀው በቃ ይህ ነው ደጃል፡
~~~~
http://t.me/Sami_Habib
461 views07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 23:55:44 የዘመናችን ነሺዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

የዘመናችን ነሺዳህ በሙዚቃ እና በመሳሪያ የታጀቡ እንጉርጉሮ ነው፥ ዘፈን ሙዚቃ፣ የሙዚቃ መሳሪያ እና እንጉርጉሮ የታጀበት ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት ”አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ”፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 31፥6
“ኢብኑ መሥዑድ እንደተናገረው፦ *”ከሰዎችም ከአላህ መንገድ ሊያሳስት ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ” የሚለው ወሏሂ እርሱ “ዘፈን” ነው”*። كما قال ابن مسعود في قوله تعالى : ( ومن الناس من يشتري لهو الحديث ) قال : هو – والله – الغناء .

“ለህወል ሐዲስ” لَهْوَ الْحَدِيث ማለትም “አታላይ ወሬ” ማለት ሲሆን “ጊናእ” ነው፥ “ጊናእ” غِنَاء የሚለው ቃል “ገና” غَنَّى‎ ማለትም “ዘፈነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዘፈን” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል። ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦
17፥64 *ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል*፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 17፥64
*”ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል” የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ “ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው”*። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك

"ሐላል” حَلَال ማለት “የተፈቀደ” ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት “የተከለከለ” ማለት ነው። ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ ሙዚቃም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን”ﷺ” ሐዲስ ተነግሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ *”ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሣሪያ ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

የዘመናችን ነሺዳህ ከፕሮቴስታንት መዝሙር የተኮረጀ ፈሣድ ነው፥ ትተን የመጣነው የጴንጤ እምነት ትዝ ያስብሉኛል። ዜማው፣ የሙዚቃ መሣሪያው እና ጭፈራው ምንም ልዩነት የለውም፥ ከዚህ ፈሣድ እራሳችንን መጠበቅ አለብን። አሏህ በሙዚቃ መሣሪያ የሚነሽዱትን ሰዎች ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

"ይህ ፈሣድ መጋለጥ አለበት፥ ለሌሎች ሠበቡል ሂዳያህ ይሆናል" ካላችሁ እንግዲያውስ ሼር ማድረግ ግድ ይላል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ

http://t.me/Sami_Habib
http://t.me/Sami_Habib
490 views20:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 21:10:51 ሰሜን ምድር ዔጁ!!በኑር!!!

የጀግንነት ሞገድ መፍለቂያ የወንዶች፡
የቆራጥ እናት ልጅ የፍቅር ዘመዶች፡
ይሔ የኤጁ ልጅ አንድ ነው አቋሙ፡
ሀገሩን አይሸጥም ቢፈስ እንኳን ደሙ፡
ይናገር ይመስክር የራያ ተራራ፡
በጀግና ልጆቹ ምን ገድል እንደሰራ፡
ይጠዬቅ ወልድያ ዶሮ ግብር ሐራ፡
ስንቴ እንዳከሸፈ የጠላትን ሴራ፡
ይጠየቅ አረባል ይናገር ኩልባይኔ፡
ምን እንደፈፀመ ያ ጀግና ወገኔ፡
ወራሪውን ጠላት ሞቱን እንዳበጁት፡
ያንን ባንዳ ጁንታ ለጉድ እንደ ፈጁት፡
ጠላትን ያሮጠው በግር ያለጫማ፡
ያ ሰላም ወዳድ ህዝብ ያ የፍቅር አርማ፡
ይመስክር ይናገር ትጠየቅ ሰዶማ፡

የማይከፈተው የፀናው ውብ ሳንቃ፡
በእጁ የጨበጠው የጠላትን ላንቃ፡
ያ ገበሬ ተኳሽ መገን ዱሬ ሮቃ፡
ወራሪውን ጠላት የሚለው በል በቃ፡
ሐራ እና ወርጌሳ ሀብሩና ሲሪንቃ፡
ጠላትን መክቶ ፆሙን የሚያሳድር
የጀግኖች ሀገር ነው ይሔ ኤጁ ምድር፡
የሙስሊሞች ውህደት የገበሬ ተኳሽ፡
ጠላትን የሚፈጂ እንደ እሳት ትርኳሽ፡
አሏሁ አክብር ብሎ ወስኖ ሲነሳ፡
ይደለቃል ልቡ እንደ ደልግ አንበሳ፡
ለሀገሩ ሲባል መሞት የማይሳሳ፡
አኩሪ ታሪክ ሰርቷል ሁሌም የሚወሳ፡
ሽርጡን ሸብ አርጎ ሲስብ ያንን ቃታ፡
በጨለማም ቢሆን አልሞ እሚመታ፡
ይህ ነው የኤጁ ልጂ ገበሬው ወታደር፡
የወገን አለኝታው ያገር አንባሳደር፡
አምሳያ የለውም ምን ወንድ ቢሰደር፡

ያምርበታል ኤጁ ሲለብስ ጀበርና፡
ክላሹን ሲሸከም ሆኖ በፅሞና፡
ዝናሩን ሲታጠቅ አጊጦ በጥምጣም፡
የሰሜኑ ልዑል ያ ባለ ሽርጣም፡
በህይወት እስካለሁ ከውስጤ ባትወጣም፡
ይድረስህ መልዕክቴ ወድሀለሁ በጣም፡
ወራሪውን ቡድን አድርገሀል እንክት፡
ተዋድቀሀል ለኛ ብቻህን ስትመክት፡
ልዩ ሀይልም ፋኖ አልደረሰልህም፡
ብቻህን ታግለሀል እኛ አንረሳህም፡
እውነትም ጀግና ነህ የሀበሻ አርበኛ፡
አልተንበረከክም ለዚያ ለሴሰኛ፡
መውዜርህን ታጥቀህ ከጫካ ገብተሀል፡
ሽርጣሙ ኮከብ ክብር ይገባሀል፡

የያዝከው መሳሪያ ከተኮሰ አይስትም፡
ጠላቶቹን ያውቃል ፈፅሞ አይሰስትም፡
ደቡብ ወሎ ሆኘ ገድልህን ብሰማ፡
ተደሰትኩኝ ባንተ ኮራሁኝ እኔማ፡
እግረኛህ መሆንን በልቤ ብመኝም፡
የት ሔጀ ላግኝህ አማራጭ የለኝም፡
ያን የጋራ ጠላት ቀጥቅጠህ አሶጣ፡
ወይ እዛው ጨርሰው ወደኛ እንዳይመጣ፡

ወሎ ላይ ቢዘምትም ያ የናት ጡት ነካሽ፡
ሰው በላው ወራሪ ያ የሰው ርካሽ፡
ጨካኝ አረመኔው ውሻ ጁብ ተናካሽ፡
አንተ ተዋድቀሀል ባለህ ሰሜን ክላሽ፡
#ጀግናዬ__!!
ታሪክህ በዝርዝር ባይፃፍልህም፡
ጀግንነትህ ላንተ ባይታወቅህም፡
በዜና መፅሔት ባያቀርቡልህም፡
ሰበር ዜና ብለው ባያካብዱህም፡
ልባችን ውስጥ ነህ እኛ አንረሳህም፡
አብሽር ጀግናችን ሆይ ፈፅሞ እንዳይከፋህ፡
ሞራልህ እንዳይጓሽ እንዳይወይብ ተስፋህ፡
ታንክም ስናይፐር ዶሽቃንም ማርከሀል፡
ጠላትህን ደፍረህ ታግለህ አታግለሀል፡
ኢቲቪ ባይዘግብ ምን ያደርግልሀል፡
ጀግንነትህ ማርኮን ልባችን ፅፎሀል፡
ቀጥቅጠህ ገርፈኸው ጠላትህ አውቆሀል፡

ይሔ የኤጁ ልጅ አይስትም ጥይቱ፡
ሲተኩስ ይለያል ሲወጣ ካፎቱ፡
መሪ መሪውን ነው የሚወጋው ቀስቱ፡
የሚኒሽር ጥይት ከቶ አያባክንም፡
ባንዴ ሁለቱን ኑው ምቱ አያስኮንንም፡
ዜናህን ሲሰማ ጠላትህ ይፈራል፡
ዝናህ የቆዬ ነው ዛሬም ይከበራል፡
ሁሌም ትኖራለህ ሆነህ ለኛ ሞራል፡
ባንተ ላይ ነውኮ ወራሪው የመጣው፡
አንተን አጥቅቶ ነው ወደኛ ያጣው፡
እያለ ወሬኛ ወሬውን ቢነዳም፡
የጦርነቱን ልክ ፈፅሞ አልተረዳም፡
ባሉባልታ ወሬ አትረበሽ ከቶ ፡
ጆሮህን አትስጠው ለዘረጦ እንኩቶ፡
ማንም ሆነ ምንም ሳያግዝህ ብፊት፡
ወጥረኽው ነበር ልክ እንደ ንፋፊት፡
ይህንን እውነታ ሁሉም ፍጥረት ያውቃል፡
ለጀግንነትህ ልክ ይህ ብቻ ይበቃል፡
ሰላም ሰፍኗል አሉኝ ሁሉም በዬ ፈርጁ፡
ኢንሻ ኣሏህ ብዬ ሆንኩልህ ዝግጁ፡
መጥቼ አይሀለሁ ሰሜን ምድር ኤጁ፡

አንት የጦር ገበሬ የሰሜኑ ጀግና፡
የወሎ ሸቂቅ ልጂ የአብስኒያው ሳተና፡
አንተን ለመዘዬር ልቤ ቋምጧልና፡
በሰንሰለታማው በራያ ሸንተረር፡
የጠላት ሰራዊት ደም ባለበት ቆረር፡
ወይም ድሬሮቃ ወልዲያ ጎብዬ፡
አይንህን ለማዬት በፍቅር አባብዬ፡
እንድትቀበለኝ መጣሁ አንተን ብዬ፡
#ባይሆን____!!
ምንም እንኳ እንዳንተ አልሜ ባልመታም፡
ጠላት ከመጣብኝ ግን አላመነታም፡
እናማ አንተኑ ፈልጌ ወዳንተ ከመጣሁ፡
አብሬህ በልቼ አብሬህ ከጠጣሁ፡
የሰሜኑ ተኳሽ ለስምህ መጠሪያ፡
ገና ሳትተኮስ ጠላት ማስፈራሪያ፡
ታጣፊ ክላሿን እንድትሸልመኝ፡
እርሷን እስታጥቅና በፈገግታ ሳመኝ፡
አቦ እወዳችኋለሁ
ጉዞ እጀምራለሁ ሁኛለሁ ዝግጁ፡
ካረፈበት ቦታ ክላሹና ፈንጁ፡
ሔጄ ልመለከት ሰሜን ምድር ኤጁ፡

http://t.me/Sami_Habib
http://t.me/Sami_Habib
399 views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 19:47:17 #ሰለፍይ_ወንድሜ_ሆይ_አደራህን_!!

#ይህችንስ_አታግባት_!#በኑር
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የወንድ ልጂ ክብር ትልቁ ገፅታ፡
ነውና ሚስጥሩ የትዳር ጨዋታ፡
የፈጣሪ ፀጋ የቤተሰብ ፌሽታ፡
የባለቤት ሀሴት የጓደኛ ደስታ፡
የፍቅር ተምሳሌት ውብ ገፀ በረከት፡
ተግባር የሚገልፀው እውነተኛ ስብከት፡
ደስታን የሚለግስ ወደር የታጣለት፡
ነውና ውብ ግርማ ትዳር ብሎ ማለት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የትዳር ምርጫህን አስተካክለህ ምረጥ፡
ከመጥፎ አስተያየት ፍጠን ተስፋ ቁረጥ፡
ማንም ስለጮኸ ማንም ስለገፋህ፡
ሐሳብክን አትቀይር አስተውል አይክፋህ፡
መልካም መካሪያችን መልካም ሰው ቢሆንም፡
ውስጥህ ካላመነ የማይሆን አይሆንም፡
ጯሒ ድምፅን ሁሉ ወደህ ተቀብለህ፡
ስህተት አትፈፅም ለቤተሰብ ብለህ፡
ሳትፈልግ አግብተህ ከመደነጋገር፡
ከመግባትህ በፊት እውነትን ተናገር፡
የማትወዳትን ሴት ከቶ እንዳታገባ፡
ትዳር ጌም አይደለም ግራ እንዳትጋባ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከመግባትህ በፊት አስተውል አስተንትን፡
ከደረቅ መሬት ላይ ዘርክን እንዳትበትን፡
የተውሒድ የሱና #ንሽ የሌላትን ሴት፡
ተዋት አትፈልጋት አትሰጥህም ሀሴት፡
የሱና ምርኮኛ በተውሒድ ያበበች፡
ሀያዕ ቁጥብነት የተከናነበች፡
አቋሟም ውበቷም ኒቃቧም የሚያምር፡
ውጯም ሆነ ውስጧ ተውሒድ የሚዘምር፡
ሌሎቹን ተዋቸው እርሷን አግባ ከምር?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ፀንታ የምትጓዝ በመንሀጀ ሰለፍ፡
በአዳድስ ጥመቶች የማትዝለፈለፍ፡
በችግር ጊዜና የምትሆን ፅናት፡
ሰለፍይ ምረጥ እውነተኛ እርሷ ናት፡
ላንተ እምትጨነቅ የምታስብልህ፡
አዕምሮዋ ምጡቅ እቅዷም የብልህ፡
የተውሒድ ደረሳ የሱና ተማሪ፡
የሰላም የፍቅር የመውደድ ዘማሪ፡
ማዕበልን ሰንጥቃ እንደ አሳ ነባሪ፡
ሱና ላይ የፀናች ቢዲዐን ቀባሪ፡
እናት አባትህን አንተንም አክባሪ፡
ስኬትን ከፈለክ ጀግናው ይህችን ምረጥ፡
አጥብቀህ ዱአእ አድርግ ተስፋ ባለመቁረጥ፡
ከእንዲህ አይነቷ ጋር ትዳር ነው ረመጥ፡
ከእንድህ አይነት ትዳር ለብቻ መቀመጥ፡
አወ ላጤነትህ ሳይሻል አይቀርም፡
እውነትን እያወቅክ ባጢል ከምትፈርም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#ስለዚህ_ይህችንስ_አታግባት__!!
ሐቅን የማትፈልግ ጥመት ያሰከራት፡
ቁርአንና ሐዲስ ደሊል የማይመራት፡
ሽርክ እየጣፈጠ ተውሒድ የመረራት፡
ሸይጧን ሰውነቷን ተብትቦ ያሰራት፡
ፊትና የምትናፍቅ ስሟን ለማስጠራት፡
ሽርክን እንደገና ጠፍጥፎ ለመስራት፡
ከእግር እስከራሷ ድርቀት የወጠራት
የምታሳንስህ በንቀት በኩራት፡
ይህችን አይነት ፍጡር በሩቁ ነው መፍራት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የአህባሽን ጥመት ወዳ ከተጋተች፡
ሀቅን እየተወች ጥመት ካሸተተች፡
ኢኽዋን ከጋለበት በቁሟ ከሞተች፡
ከሰለፎች መስመር ከተንሸራተተች፡
ሁሉም ሹብሀውን የሚቀረሽባት፡
ማንም መጥፎ ጠረን የተነፈሰባት፡
አድስ ፊትና ሁሉ ግራ የሚያጋባት፡
ሱፍያና ተግሊግ ምራቅ የተፋባት፡
ሀዳድዩ ሁሉ የተጫወተባት፡
ተውሒድ ሱና ሲባል ግራ ከሚገባት፡
ሌላ ፈልግ እንጂ ይህችንስ አታግባት፡

http://t.me/Dr_Sami_Habib
http://t.me/Dr_Sami_Habib
619 views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 19:24:57 #ለሳዳት_ከማል_አድርሱልኝ_አደራ

#ለኔ_ፍቀድልኝ!?(#በኑር)
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አህባሽና ኢኽዋን ሁሌ እየዛተብህ፡
ሱፍያና ተብሊግ ጫት እየቃመብህ፡
ይሙትልን ብለው እየፀለዩብህ፡
ይህን ሁሉ ጫና ጆሮ ዳባ ብለህ፡
በተውሒድ ስብከት ላይ ዛሬም ድረስ አለህ!?
#ታዲያ__!!
ሰዎችን በመልካም-ዘውትር እያዘዝከን፡
ወንጀል እንዳንፈፅም እየከለከልከን፡
በአሏህ ውድ ቃል_ሁሌ እያሳመንከን፡
አሏህን ተገዙ አንዱን ጌታ እያልከን፡
ለተውሒድ ለሱና በቻልከው ከለፍህ፡
ባለህ ትርፍ ጊዜ ሽርክን ከተጋፋህ፡
ፕሮግራም አውጥተህ ሱናውን ካስፋፋህ፡
በረድ አንበርክከህ ቢዲአን ካጠፋህ፡
ዳዒያችን ነህ ብዬ መስክሬ በእውነቱ፡
ኡስታዝ ሳዳት ብልህ ምንድን ነው ጥፋቱ!?
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኡስታዝ አትበሉኝ ካልክ እሽ ግድ የለኝም፡
ግን ፈቃድ ይሰጠኝ እኔ አያስችለኝም፡
በስምህ ስጠራህ አዎ ይጨንቀኛል፡
እደነግጣለሁ ፍርሀት ይሰማኛል፡
አንገት እደፋለሁ ይሰቀጥጠኛል፡
ስለዚህ ኡስታዜ ብልህ ይሻለኛል፡
ችግሬን ተረድተህ ፍቀድልኝ ለኔ፡
የተውሒድ ሰባኪው የሱናው ወገኔ፡
----------------------------------------
#ሳዳት_አንተ_ማለትኮ_!!
ሱናን ለመዘመር ይሉኝታ አይዝህም፡
የአድናቂህ ጫጫታ አያታልልህም፡
የወቃሽ ወቀሳ አላሸነፈህም፡
ጥቅምና ዝና አላማለለህም፡
#ሰለፍይ ወንድም ነህ #ኢኽዋን አይደለህም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አትፈልግም እንጂ ብዙ ብዙ ባልኩህ፡
የውስጤን እምቅ ሀይል ፅፌ በነገርኩህ፡
ግን አንተ አትፈልግም እንድህ አይነት ነገር፡
እንጂማ ጀግና ነህ እውነት ለመናገር፡
ታጠቅ ሚዲያ ላይ ድምፅህን ሰማሁት፡
አሳማኝ ምክርህን በጥልቀት አየሁት፡
ገረመኝ አቋምህ ደነቀኝ ድፍረትህ፡
ለሐቅ ያለህ ቦታ አመለካከትህ፡
ትላንት ሆነ ዛሬ ተውሒድ ነው ስብከትህ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አሏህ በአንተ ሰበብ ብዙ ሰው አቅንቷል፡
ሳይሰለቹ መምከር ላንተም ፅናት ሰጥቷል፡
ብዙዎች መጥተናል ከሱፍያ ገዳም፡
ዛሬ ለሐቅ እንጂ ለሽርክ አንነዳም፡
ይህንን ሁሉ እውነት አንተ ባትረዳም፡
ለዚህ ነው ስምህን የምናነሳሳህ፡
ሰበብ ሆነኸናል አንችልም ልንረሳህ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንጂማ ፈፅሞ ድንበር አላለፍንም፡
ያለ ቦታህ ቁጭ በል በፍፁም አላልንም፡
ነገር ግን ኡስታዝ ነህ እወቀው እውነቱን፡
ተጨባጩ ክስተት መረጃ ነው ፍቱን፡
ከፍ ከፍ አድርገን አናካብድህም፡
እውነት ሀቂቃን ግን እመን ግደለህም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከኢኽዋን መንጋጋ ከጥርሳቸው መሀል፡
አሏህ ሰበብ አርጎ እኔን አውጥተሀል፡
እኔ ኡስታዝ ብልህ ላንተ ምን ያንስሀል!?
#በተቻለህ_አቅም፤
ባረፍክበት ሁሉ ሐቅ አስተላልፈሀል፡
#የሱና_ጠበቃ፤
የጥመት መብረቅ ነህ እኛ ወደንሀል፡
#አሏህ_ይጠብቅህ፤
በተውሒድ ስብከትህ ክብር ይገባሀል፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንባ ተናነቀኝ ምክርህን ሰማሁት፡
ሀሳብ ምኞትህን አሻግሬ አየሁት፡
በኔ ቁንፅል ሀሳብ በትንሿ ማንኪያ፡
መስፈርት አሟልተሀል በኡስታዝ መለኪያ፡
እባክህን ሳዳት ይቅርታ አድርግልኝ፡
ኡስታዜ ልበልህ ለኔ ፍቀድልኝ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
http://t.me/Sami_Habib
http://t.me/Sami_Habib
998 views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-28 10:32:45 #ወንድ___ከሆንክ____አግባ___!!

#ዱንያ_ላይ_የለችም__በኑር!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ትዳርን ስትፈልግ አስበህ ተነሳ፡
አቧራህን አራግፍ ጉድፍህን አንሳ፡
አለምን ብትቃኝ ብትዞር ዳር እስከ ዳር፡
ከግንቦት-ነሀሴ ከመስከረም_ህዳር፡
ብትፈልግ ብትለፋ ሁሌ ቀንና አዳር፡
ብዙ ሴት በማየት አይገኝም ትዳር ፡
አይን መስፈርት አታርግ ልብህን አስውበው፡
በውስጥ ጥምረት ነው ፍቅር የሚደልበው፡
አብሮ በመኖር ነው ሁብ የሚከሰበው፡
ከዕለት ወደ እለት ነው ትዳር የሚያብበው፡
ከአመት ወደ አመት አብቦ ያፈራል፡
ስኬታማ ጥምረት ቀልጂ ይበሰራል፡
ሌላም ይደገማል እያደር ይገራል፡
ይህንን እውነታ ሁሉም ይናገራል፡
ስለዚህ ቶሎ አግባ ምኞት አታስረዝም፡
አንዷን ፅደቅባት አትበል ዝምዝም፡
ከዛውጭ አቃቂር በማውዛት መስፈርት ካበዛህ፡
ወጣትነት ያልፋል ሳትፈካ ጠነዛህ፡
ከጓሮ ሳትወጣ በታዛ ጠነዛህ፡
ዋጋህን አርክሰህ በነፃ ተገዛህ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ይህንንም ስልህ አትፍራ ፈፅሞ፡
ከልክህ አትነስ ስሜትህ ተዳክሞ፡
ሚዛንህ ሀቅ ይሁን አትውጣ ከመስመር፡
በሱና ተወዳጂ በመንሀጂ ተጣመር፡
በቃ ወንድ ከሆንክ ሴት ተፈጥሮልሀል፡
በሀላሉ ድፈር አግባ ተብለሀል፡
ከዚህ ውጭ ክብር ምን ያደርግልሀል፡
#የኔ_እህት___!!
አንችም ሸርጥ አታብዥ ሀላሉን ድፈሪው፡
እየተግደረደርሽ በተስፋ አታኑሪው፡
ሞቅ በረድ እያልሽ በቃ አታደናግሪው፡
በሀላሉ እሽ በይ ሱናውን ድፈሪው፡
ሰለፍይ ከሆነ ምን አለው አትበይ፡
አርኪ መልስ ስጭው አግቢ መርሀባ በይ፡
#ወንድሜ__!!
መስፈርት አትደርድር ላይሆን አትውተርተር፡
በል ደርሰሀል አግባ በሱናው ተሰተር፡
ውሸት አትቀምም በወሬ አትተርተር፡
እውነትን ተናገር ውሸት አትጨምር፡
የሀሰት ጂማሮ ፍፃሜው ላያምር፡
የተባረከች ሴት በምርጫ አትገኝም፡
ሱንይ ጀግና እንስት ፈፅሞ አትሞኝም፡
ስለዚህ ወዳጀ አንዷን ፅደቅባት፡
ሞክረው ትዳሩን አለው ግሩም ቅባት፡
ንፁህ እህትህን ተው ግራ አታጋባት፡
ቀጠሮን አታብዛ በል ወስነህ አግባት፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዛሬ ከአንደኛዋ ነገ ካንደኛዋ ሁሌ ቃል አትግባ፡
አቋም የለሽ ዋላይ አትሁን የማትረባ፡
ምርጫ እሚያበዛ ሰው ፍፃሜው አያምርም፡
ደስታ ይርቀዋል ስኬቱም አይሰምርም፡
ብዙ ሴት በማየት ሙራድህ ላይሞላ፡
በል ወስንና አግባ አትበል ወደ ኋላ፡
አንዷ ላይ አተኩር አትይ ወደ ሌላ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አግባ አትጨናነቅ ወንድ ነህ ሴት ሞልቷል፡
ነው ወንድ አይደለህም ስብዕናህ ሞቷል!?
ጤና ይጎድልሀል አዕምሮህ ተነክቷል!?
በህመም ምክንያት ልብህ ቀልብህ ጓሽቷል!?
በወንጀልህ ብዛህ አዕምሮህ ታውኳል!?
ከጂስምህ ርቋል የወንድነት አስኳል!?
ምርጫህን አታብዛ ከዚችም ከዛችም፡
ይህች አለም ጠፊ ነች ዘውታሪ አይደለችም፡
ለተጣመረ እንጂ ለላጤ አትመችም፡
አቋምህን ግለፅ ወሬን አትቸምችም፡
የብቻ ኑሮህን ለምን አትሰለችም?
ምድራዊ ሴት አግባ በተስፋ አትገችም፡
ሁረልዒን ከሆነች ዱንያ ላይ የለችም፡

http://t.me/Sami_Habib
http://t.me/Sami_Habib
620 views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ