Get Mystery Box with random crypto!

ታሪኩ የሚጀመረው በ 2002 ዓ.ም ከቤሩት ወደ አዲስአበባ የሚበረውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አይር | ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

ታሪኩ የሚጀመረው በ 2002 ዓ.ም ከቤሩት ወደ አዲስአበባ የሚበረውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አይር መንገድ የሆነው ቦይንግ 787 አውሮፕላን ተከስክሶ ከ90 ሰዎች ጋር ባሏ የሞተባት ሎዛ የተባለች ትንታግ ገፀ-ባህሪ የአደጋውን መንስዔ በራሷ መንገድ ለማጣራት የምታደርገውን ውጣ ውረድ በመተረክ ነው።
የሎዛ ይህ ድርጊት በኢትዮጵያና በሊባኖስ አይር መንገዶች አልተወደደላትም። እንዲያውም በግዙፉ ቦይንግ ካምፓኒ እንደ ጭራቅ እንድትታይና እሷን ማስወገድ የመጨረሻ አማራጫቸው አድርገው እንዲወስዱ አነሳሳቸው።

ሳታውቀው እንዲህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ የገባችው ሎዛ ገለልተኛ የአደጋው መንስኤ አጣሪ ኮሚቴ ያወጣውን ድምዳሜ ስታይ ይብሱኑ እንድትበሳጭና ነገሩን ገፍታበት ትክክለኛውን የአደጋውን መንስዔ በራሷ መንገድ ማጣራት በአደጋው ለተቀጨው ባሏ ጥልቅ ፍቅሩን የምትገልጽበት አይነተኛ ማካካሻ አድርጋ ወሰደችው።

ግን ደግሞ የውርደት ካባ ላለመከናነብ በመላው ዓለም የዕዝ ሰንሰለቱን የዘረጋው የቦይንግ ካምፓኒና ስሙ ምስጢራዊ የሆነ ድርጅት ሎዛን ለማስወገድ የመጨረሻ ካርዳቸውን መዘዋል--ግብግቡ የሚጀምረው እዚህ ጋ ነው እንግዲህ !

መጽሐፉ ልቦለዳዊ ቢሆንም የተከሰቱ እውነተኛ ሁነቶች ላይ ተንተርሶ የተጻፈ ነው(በ2002 ዓ.ም ከቤሩት አዲስአበባ በረራውን ያደረገ ቦይንግ 787 አውሮፕላን ተከስክሶ 90 ያህል ሰዎች እንደተቀጠፉ ልብ ይሏል )።

በተያያዘና ተመጋጋቢ በሆነ ሁኔታ የተማሩ የኢትዮጵያ ምሁራን ከዚህ በፊት ባልተካሄደበት መንገድ ኢትዮጵያን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ቁጥር አንድ ሀገር ለማድረግ እንቅስቃሴውን ሲያጧጥፉ መጽሐፉ ይተርካል። እነዚህ ምሁራን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን በቴክኖሎጂ ለማመንደግ የተነሳሱ ናቸው። ይህ ሁኔታ የእርዳታ ድርጓቸውን እየበተኑ ጥሬ እቃችንን በሚያጋብሱ ምዕራባውያን አልተወደደም--ሌላ ግብግብ!


በመጨረሻም ኢትዮጵያ በራሷ ባንዲራ ያጌጠች ሳታላይት ስታመነጥቅ የመጽሐፉ ሽፋን ላይ ይታያል።( ልብ በሉ! ይህን ሽፋን ይዞ መጽሐፉ የታተመው በ2008 ዓ.ም ነው)። ይህ ነገር መጽሐፉን ትንቢታዊ ያደርገዋል። ምክኒያቱም ከሁለት ዓመት በኋላ በቻይና ጀርባ አሳዝላም ቢሆን ኢትዮጵያ የራሷን ሳታላይት አመጥቃለች!


ሌላውን ከመጽሐፉ ......

መጽሐፉን በነጻ በ PDF ለማውረድ ከታች ያለውን link ተጠቀሙ!!!

ምርጥ :ልብ አንጠልጣይ
:ፍቅርን
:ስለላን
:ሳይንስን
:ትንቤትን
:መድሃኒቶችን አጠቃሎ የያዘ!!!!

*እመኑኝ.አንዴ ከከፈታችሁ ሳትጨርሱ አታቆሙም!

*ኢትዮጵያን የሚወድ ያንብበው!!!
ብርሃኑ በቀለ ሰንዶታል!!!
*NB..የፈጠራ ክህሎት ያላችሁ ምናባችሁን ስለሚያሰፋው ሳታነቡት አትለፉ!!

መልካም ንባብ