Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 2 ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ከወደውጪ ድምፅ ተሰማ፡፡ አስር አለቃ ጎረቤታቸውን በዱላ አናቱን ብ | ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

ክፍል 2

ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ከወደውጪ ድምፅ ተሰማ፡፡ አስር አለቃ ጎረቤታቸውን በዱላ አናቱን ብለው በሩ ላይ ደፍተውት ነበር፡፡

ሰይጣን አጀንዳውን ይዞ አስር አለቃ ግቢ ሲደርስ ነገር ተደበላልቆ ጠበቀው፡፡ ጉዳዩን በጥንቃቄ አጣራና አጀንዳው ላይ እንዲህ ሲል ከተበ "የአስር አለቃው ጉዳይ ከእቅድ በላይ ተፈፅሟል፡፡"

ሦስት ፖሊሶች ኮሌታቸው ጨምድደው ወደያዟቸው አስር አለቃ ጆሮ ጠጋ አለና "አንተ ሸፋፋ! ስማ..! አሁን በግድያ ሙከራ ዘብጥያ ትወርዳለህ የተበደረው ጎረቤትህ ተሽሎት ወደ ቤቱ ይመለሳል..፡፡ ያች አንቋራሪ ልጅህም የትም ስታንቋር

ር ስለምትውል ቤትህ ሰው የለም፡፡ ሚስትህና ጎረቤትህ ብቻቸውን እዚህ ሰፊ ግቢ ራስህ አልጋ ላይ...ሂሂሂሂሂሂ ቂቂቂቂቂቂ አይ ሸፋፋው!!

ይልቅ ሚስትህን ዓይንህ እያየ ከምትወሰድ አንዱን ፖሊስ በካራቴ ድፋውና አምልጥ...ወታደር አይደለህ...? አስር አለቃ አይደለህ?.... ኮማንዶ ነኘ እያልክ በየጠላ ቤቱ ስታወራ አልነበር...? ወይስ ዝም ብለህ ስትወሽክ ነው...፡፡"

አስር አለቃ ቀስ ብለው ከጎናቸው የቆመውን ፖሊስ ተመለከቱት፡፡ክስት ያለ ነው...በዛ ላይ የያዘው መሳሪያ የከበደው ይመስላል፡፡ ሁለቱም ፖሊሶች ቢሆኑ ያን ያህል የሚስፈሩ አይደሉም ቀድረ ቀላል ነገር ናቸው፡፡ " ይሔኔንንስ መሣሪያውንም መንጠቅ አያቅተኘ " ሲሉ አሰቡ፡፡ ፖሊሶቹ አስር አለቃን እያጣደፉ ወደ ጣቢያ ወሰዷቸው፡፡

ዷ....! ዷ............መንደርተኛው ከሩቅ የተኩስ ድምፅ ሰማ

"ምንድነው....?"

"እስረኛ ሊያመልጥ ሞክሮ.....ፖሊሶቹ እግሩን ሰንክለው አቆሙት.....!

ሰይጣን በሳቅ ፍርስ አለ፡፡ እናም አጀንዳው ላይ እንዲህ ሲል ፃፈ "የእግሩ ጉዳይ አልቋል አሁን ነፍሱን ማንሻፈፍ ይቀረኛል!!"

ከዛም ሰይጣን ቀይ እስኪሪቢቶ አወጣና እየተፍነከነከ እንዲህ ሲል ፃፈ

"አስር አለቃ አምሳ አለቃ መቶ አለቃ ሻለቃ ጄነራል ሚኒስተር ...ጠቅላይ ሚኒስተር ሁሉም እግር አላቸው፡፡ እንኳን እነርሱ አገርም እግር አላት ስንፈልግ እናንሻፍፋታለን!!!"

ደራሲ #አሌክስ_አብርሃም
#ዙቤይዳ ከሚለው መፅሐፍ

#እግር_በእግር
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD