Get Mystery Box with random crypto!

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN #ስውር_አይን የ | ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ስውር_አይን

የመርሐ ግብሩ መሪ እኒያን ሊቅ ሲያስተዋውቅ "በአይነ ሥውር አቅማቸው ይህን ሁሉ ትምህርት ተምረው ይህም ያህል ደቀ መዛሙርት አፍርተው.....እያለ በእርሱ አመለካከት ማድነቅ ያለውን ነገር አወረደው፡፡

ሊቁ ግን ሲነሱ:- "ይህ ወንድሜ ያለውን ሰምቻለሁ ፡፡ በዓይነ ስውር አቅማቸው.......ብሏል፡፡ ወንድሜ #አምፑል ተቃጠለ ማለት መብራት ሄደ ማለት አይደለም ዓይነ ስውር ማለት የሳሎኑን መብራት አጥፍቶ የጓዳውን አብርቶ የተቀመጠ ነው ብለዋል፡፡...."፡፡በእርግጥም ሊቅ ናቸው፡፡

የሚንከባለል ዓይን ያለው አብዛኛው ሰው የጓዳውን አጥፍቶ የሳሎኑን አብርቶ የተቀመጠ ነው፡፡

የላይኛው ዓይን አምፑል ነው፡፡ አምፑል የሚሰራው በራሱ አይደለም ዓይንም ያለ ልብ ከኃይል ምንጩ እንደተለያየ አምፑል ነው፡፡ ማስተዋል ከሌለ የላይኛው ዓይን ከጌጥነት አያልፍም፡፡ እግዚአብሔር የሠራውን ለማድነቅ የወደቁ ሰዎችን ለማንሳት ወዳጆችን በፍቅር ለመመልከት.....የሚያገለግለው የውስጥ ዓይን እንጂ የውጭ አይን አይደለም፡፡

ጌታችን ወደዚህ ዓለም የመጣው እያዩ የማያዩትን እናያለን እያሉ የማያስተውሉትን ሳያዩ እንመራለን የሚሉትን ለመውቀስ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚታየው እውነት የሚገኘው በውስጥ ዓይን እንጂ በላይ ዓይን አይደለም፡፡


ወደ ተመስጦ ስንገባ ዓይናችንን እንጨፍናለን፡፡ የላይኛው ዓይን ባካና ያደርጋል፡፡ ለኅሊና የቤት ስራ እየያዘ ይመጣል፡፡

የቀደሙት አባቶች የቋንቋ እውቀታቸው ይደንቃል፡፡ ሲሰይሙ "ዓይነ ስውር" ብለዋል፡፡ ሥውር አይን ያለው ማለት ነው፡፡ አንዱ የግልፅ አንዱ የውስጥ ዓይን ተደርጎለታል ማለት ነው፡፡ የላይኛው ዓይን ማጣት ሳይከለክላቸው ብዙ ታላላቅ ሥራ የሠሩ ሊቃውንትን ይቺህ ዓለም አስተናግዳለች፡፡

የላይኛውን ብርሃን ማጣት ኃጢያት አይደለም፡፡ በውስጥ ጨለማ ተዝናትቶ መቀመጥ ግን ሀጢያት ነው፡፡ የላይኛው በተዓምራት ይወገዳል የውስጥ ጨለማ ግን ያለትምህርትና እምነት አይወገድም፡፡

ዓይን ተመልሳ እራሷን አይታ አታውቅም፡፡ ሌሎችን ታያለች ራሷን ግን አታይም፡፡ ሌሎች ያጎደሉት ትገመግማለች የራሷን ግን አታውቀውም፡፡ የላኘኛዋ ዓይን ለሌሎች የሆነውን እያየች #ቅንዓትን የሌሎችን ሰላም እያየች #ምቀኘነት የሌሎችን መውደቅ እያየች #ፍርድን የሌሎች ርኩሰት እያየች #ውድቀትን ይዛ ትመጣለች፡፡

#በላይኛው_አይን_ብቻ_ማልቀስ_አይቻልም

በመንገድ ላይ እናቶቻችን "እያዩኘ ሰላም ሳችሉኘ አለፉ" ስንላቸው የተለመደ መልስ ይሰጣሉ፡- "አይ ልጄ የሚያየው ልብ እንጂ ዓይን መሰለህ?" ይላሉ፡፡

ትልቁ ብርሃን ያለው ልብ ላይ ነው፡፡ የልብ ብርሃን ከጨለመ የላይኛው አይቶ #መርገጥ አይቶ #መጠንቀቅ አይቶ #ማዘን አይችልም፡፡

ሥውር ዓይን ያስፈልጋል፡፡ ሥውር ዓይን ሲኖረን:-

✿ ያለንን እናውቃለን፡፡ ስለጎደለን የምንጨነቀው ያለንን በትክክል ስላላወቅን ነው፡፡

✿እግዚአብሔር ዛሬም በሥራ ላይ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ ተስፋችን ይታደሳል፡፡

✿ በአሁኑ ሁኔታ ሕይወትን አንመዝን፡፡ አሁን ያለው ደግም ይሁን ክፉ እርሱ መጨረሻችን አይደለም፡፡ #የሚመጣው_የሚልቀው_ነው፡፡

✿ ለጎዱን ሳይቀር በችግራቸው እንገኛለን፡፡

✿ በተገፉት ላይ አንጨክንም፡፡ ዓለም ተራ መሆኑ ይገባናል፡፡

✿ ለሌሎች ማካፈል አንረሳም፡፡ ሌሎች እኛ ጋ ድርሻ አላቸው፡፡

✿ አንደበታችንን እንገዛለን፡፡ መልካሙን ቀን ለማየት አንደበትን መቆጣጠር ያስፈልጋልና፡፡

እርሱ ሥውር አይን ይፍጠርልን


@jahABP ነኘ ሳነብ ካገኘሁት መልካም ሰዎችን ይገልፃል ብዬ አሰብኩና እንዲህ አቀረብኩት፡፡

ክብር ይስጥልኘ

አስተያየታችሁን አድርሱኘ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD