Get Mystery Box with random crypto!

[ተጠባቂው የመጋቢት 30 ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ] በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የመላው ዓ | መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

[ተጠባቂው የመጋቢት 30 ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
የመላው ዓለም የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ዐይን በመላ መጋቢት 30 በሰሜን አሜሪካ የሚከሰተውን ሙሉ የፀሓይ ግርዶሽ ላይ ሙሉ በሙሉ ተተክለዋል፤ ይኽ ግርዶሽ ከተለመደው ውጪ የብዙዎችን ትኩረት የወሰደበት ምክንያት፡-

1ኛ. ግርዶሹ የሚያልፍበት መሥመር ከተለመደው ሰፋ ያለ በመኾኑ እጅግ ብዙ የሰሜን አሜሪካ ቦታዎች ይጨልማሉ ማለት ነው፡፡ ይኽ ደግሞ እጅግ ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት ታላቅ የሥነ ፈለክ ክስተት ሊኾን መኾኑ ነው፡፡

ኦገስት 21/ 2017 (ሰኞ ነሐሴ 15, 2009) በነበረው ሙሉ የፀሓይ ግርዶሽ 12 ሚሊየን ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ ይኽኛውን የመጋቢት 30 የፀሐይ ግርዶሽ ግን 32 ሚሊየን ሰዎች ይመለከቱታል፡፡

2ኛ. ይህ ሙሉ የፀሓይ ግርዶሽ በሰሜን አሜሪካ ላይ የመጣው ልክ በ7 ዓመቱ ነው፡፡ 7 ፍጹምነትን የሚያሳይ የሥነ ፍጥረት ቊጥር ነው፡፡ በምድሪቱ ላይ ፍጹም ክስተትና ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል እየተነገረለት ይገኛል፡፡

3ኛ. ከ7 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. በ2017 የተከሠተው ግርዶሽ 7 በሰላም ስም የተሠየሙ የዩኤስ ግዛቶችን አቋርጧል፤ የአሁኑ ደግሞ በነነዌ ስም፣ በዮናስና በመነጠቅ ስም የተሰየሙት የዩኤስ ግዛቶችን ማቋረጡ ልክ እንደ ነነዌ ከአርያም የተላለፈ ታላቅ የንስሐ ምልክት እንደሆነ በተለያዩ አጥኚዎች ጭምር በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡

4ኛ. ግርዶሹ በአማካይ ለ4 ደቂቃ ከ28 ቅጽበት በናዛስ ሜክሲኮ መውሰዱ ነው፤ እንደ ጎርጎርዮሳዊ የዘመን ቀመር ከ2010 በኋላ ትልቁ የግርዶሽ ጨለማ ነው፡፡

5ኛ. የግርዶሹ መንገድ 3 የሰሜን አሜሪካ ሀገራትን የሚያቋርጥ ሲኾን ይኸውን ሰሜን ምዕራብ ሜክሲኮ፣ ከዚያም ወደ ዩ ኤስ ኤ፤ ከዚያም ካናዳን ጭምር ያካልላል፡፡

6ኛ. ቪነስ እና ጁፒተር በሙሉ የፀሐይ ግርዶሹ ጊዜ የመታየት ዕድል ያላቸው ሲሆን ፕላኔቶች ሰልፍ ሠርተው ከታችና ከላይ ይገኛሉ።

7ኛ. ኮሜት 12p/ pont Brooks የተባለ ጅራታማ ኮከብ በዕለቱ መታየቱ ተጠባቂ አድርጎታል።

8ኛ. ኦገስት 21/ 2017 ላይ አንድ አግድሞሽ ግርዶሹ ሲሠራ በመጋቢት 30 ደግሞ አንድ ታላቅ አግድሞሽ ይሠራል፡፡ በደቡብ ኢሊኖይ እና ምዕራብ ኪንታኪ መገናኛ አላቸው፤ እነዚኽ በ2ቱም ሙሉ ግርዶሾች የሚሠራው ቅርጽ ተ ወይም የመስቀል ቅርጽ ነው፡፡ በተጨማሪም ኦክቶበር 14 ቀለበታማ የፀሐይ ግርዶሽ ነበረ፡፡ ግርዶሹ የተጓዘበት መሥመር የኦገስት 21/ 2017 አሌፍ አ ፊደልን ሲሠራ የአሁኑ ደግሞ ተ ሠርቷልና የአሌፍ እና ታው ግርዶሽ ተብሏል፡፡

9ኛ. መጋቢት 16 ወይም ማርች 25 በሰሜን አሜሪካ ፔኑምብራል የጨረቃ ግርዶሽ (ድብዝዝ የጨረቃ ግርዶሽ) የተከሠተ ሲኾን በወሩ ውስጥ ኹለት ታላላቅ ክስተቶች መኾናቸው ነው፡፡

10ኛ. እንደ ኢትዮጵያ የሥነ ፍጥረት ሊቃውንት ዘመነ ዮሐንስ - መጋቢት 29 - እሑድ የምጽአት መታሰቢያ ሲኾን በተለይ በነጋታው ይኽ ታላቅ ጨለማ መከሠቱ ብዙ ምልክቶችን በሚገባ የሚያሳይ ሲኾን ለእስራኤል ይኽ የዘንድሮው ሙሉ የፀሓይ ግርዶሽ የወራት መጀመሪያቸው ኔሣን 1 ነው፡፡

11ኛ. 4.75 በሊየን ደላር የፈጀው በጄኔቫ ሲዊዘርላንድ ያላው 10,000 ሳይንቲስቶች፤ 100ዎች ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉበት የሰርን “አጽናፈ ዓለማችንን በስውር የሚገዛውን የማይታይ ነገር ፍለጋ በሚል የዓለማችን ኃይለኛ እኑሶች አክስራሌተር ሙከራዬን በፀሐይ ግርዶሹ ዕለት መጋቢት 30 አደርጋለሁ ማለቱ መላውን የዓለም ሕዝብ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ብዙዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ሰርን በዕለቱ የተሰወረ መተላለፊያ ሆን ብሎ ሊከፍት ነው እያሉ ሲገኙ ሰርን በበኩሉ አላደርገው ይህን እያስተባበለ ይገኛል፡፡ ቢሆንም ክርክሮቹ ከፍ ብለው የዓለምን ማኅበራዊ ሚዲያ ይዘውታል፡፡ እኛም በዓለም ላይ የሚመጣው አዎንታዊ ይሁን አሉታዊ ነገርን እንደ አንድ የምድሪቱ አካልነታችን መድረስ አይቀርምና ከፍ ብሎ ጉዳዩን ማየቱ አይጎዳም፡፡

12ኛ. በጉጉት ይህን ድንቅ ክስተት ለማየት የጓጉ እንዳሉ ሁሉ አብዛኞቹ የመጋቢት 30 ይህንን ክስተት በእጅጉ የፈሩት ሲሆን ከግርዶሹ በኋላ በምድራችን ላይ ታይተው የማይታወቁ ይልቁኑ በተፈጥሮ ላይ ታላላቅ ለውጦች ይመጣሉ እያሉ ሰፊ ዘገባን እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

በዚያም ሆነ በዚህ በእኔ ምልክታም ፀሓይ ጨረቃ ዘመንን ከመሥፈር ባለፈ ለታላቅ ምልክት መፈጠራቸው የታመነ ነውና ሁኔታውን በአትኩሮት ማየት መልካም ነው፡፡

እኔም ይህን ታላቅ የተፈጥሮ ክስተት አስመልክቶ እሑድ መጋቢት 29 ከፊዚክስ ሊቁ ከዶክተር አበበ ጋር ሰፊ ጥናታዊ ጽሑፍ እጅግ ብዙ ሰዎች በተገኙበት ሙሉ ግርዶሹ በሚታይበት በቴክሳስ ዳላስ ያቀረብን ሲሆን፤ በተለይ የሕፃናቱ መገኘትና ተሳትፎ አስገራሚ ነበር። ይህም በመጪው ተረካቢ ትውልደ ላይ ያለንን ተስፋ ያለመለመ ነው። ነገም በቴክሳስ ዩኒቨርሰቲ ዪቱዲ ሰፊ የጥናታዊ ምርምር መርሐ ግብር እና ከሺዎች ጋር ግርዶሹን የመመልከት መርሐ ግብር ይኖረናል፡፡
(ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ)