Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ሰለሞንን እናመስግን:- የራይድ መልካም ገፅታ የሚለካው ለህሊናቸው በሚሰሩ የራይድ ቤተሰብ አባ | ❤️RIDE (™️) Drivers Update

አቶ ሰለሞንን እናመስግን:- የራይድ መልካም ገፅታ የሚለካው ለህሊናቸው በሚሰሩ የራይድ ቤተሰብ አባላት ነው:: አቶ ሰለሞንም የሞራል ጥግ የተላበሱ ታማኝ የራይድ አምባሳደር በመሆናቸው የሞባይል ቀፎ ተሸላሚ ሁነዋል:: ነገሩ እንዲህ ነው:: ከቀናት በፊት የራይድ ድራይቨር ቴሌግራም ግሩፕ ላይ ባጋሩን መልዕክት እንዲህ ብለውናል - "ሲደሰቱ አይቼ ደስስስስ አለኝ!!!" በመቀጠልም ሁኔታውን ሲያስረዱን"ዛሬ አመሻሽ ላይ ከጃክሮስ አካባቢ ወደ ሰሚት ስራ ገብቶልኝ ሁለት እናቶች ከነህፃናት ልጆቻቸው አድርሻቸው በባዶ ጎሮ ሰደርስ ከወንበሬ ጀርባ ባለው ኪስ ውስጥ ስልክ ይጠራል; ሳወጣዉ ይሄን የመሰለ ዘመናዊ ስልክ ነው ሳበራው የሚያምር የአባትና ልጅ ፎቶ screen saver። ራይድ ያዘዘላቸው ሌላ ሰዉ ስለነበር ስልካቸው የለኝም። ምንም እንዃ ስልኬ የተበላሸና ለስራ እያስቸገረኝ ቢሆንም በዚ መልኩ መቀየር አልፈለኩም እናም ወደተነሱበት ተመልሼ ለሰውየው ስሰጠው ቤተሰብ ሙሉ ወተው እያቀፉ ያሳዩኝ ደስታና ክብር በቃላት አይገለፅም እኔም በጣም ደስስስ አለኝ።" የራይድን ስም ከፍ ስላደረጉልን እናመሰግናለን::