Get Mystery Box with random crypto!

'ሁለት መቶ ሪያል ጠፍቶኛል ለልጆቼ ዳቦ የምገዛበት ነውና ያገኘ ይመልስልኝ' የሚል ወረቀት ከአድራ | Reyan Records

"ሁለት መቶ ሪያል ጠፍቶኛል ለልጆቼ ዳቦ የምገዛበት ነውና ያገኘ ይመልስልኝ" የሚል ወረቀት ከአድራሻዋ ጋር ግርግዳ ላይ ተለጥፎ ይመለከታል። ይህን መጠኑ ያነሰ ብር ያገኘ ይመልስ ያስባላት ብትቸገር ነው በሚል ለልጆቿ የዕለት ጉርስ ይሆን ዘንድ ሰደቃ ነይቶ ገንዘቡን አገኘሁ ብሎ ሊሰጣት ወደ አድራሻዋ አቀና።

ወደ ቤቷ ዘልቆ ይኸው ሐቅሽ ብሎ ሊሰጣት እጁን ሲዘረጋ አለቀሰች..
"ልጄ!......" አለች ዕንባን ከዓይኗ እያረገፈች
"ይህን ገንዘብ ይዘህ እኔ ዘንድ ስትመጣ አንተ አሥራ ሁለተኛው ሰው ነህ" አለችው።
ቃል ሳይተነፍስ ሳግ እየተናነቀው ወደ ሊፍቱ በመራመድ ላይ ሳለ ተጣራች
"እባክህ ማስታወቂያውን ቅደድልኝ እኔ አልፃፍኩትም እንዴት እንደሚፃፍም አላውቅም" አለችው።

ለካስ ችግሯን የሚያውቅ አንጀቱ የተላወሰ አንድ ሰው የሚሰጣት ነገር ቢያጣ የሰው ፊት ሳይገርፋት ችግሯን ታስታግስ ዘንድ ጥበብ በተሞላው መልኩ መላ ዘይዶ ማንነቱን ደብቆ በቻለው ነገር እንድትረዳ አደረጋት

"ከፈን ኪስ የለውም ሰድቁ የተቸገሩትን ለመርዳት ስታስቡ ግን ካሜራችሁን ቤት አስቀምጣቹ ሂዱ"

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch