Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሸህ እንዲህ አሉ ''5 ሰዎች ኸቲማቸው ያሰጋቸዋል '' እነማን ይሆኑ ???? ''የመጀመሪ | ረያን meme & islamic post

አንድ ሸህ እንዲህ አሉ
''5 ሰዎች ኸቲማቸው ያሰጋቸዋል '' እነማን ይሆኑ ????

''የመጀመሪያዎቹ
ሶላት የሚታክታቸው ሰዎች ናቸው አሉ''። ኤጭጭ ይሄ የማያልቅ ሶላት ደረሰ, ሰግደን እንላቀቅ.......የምንል ስንቶቻችን ነን ¿¿¿

''2ኛዎቹ,
የወላጆቻቸውን ሀቅ የማያሟሉ ሰዎች ናቸው''እስኪ የሃቂቃ እናውራ እና ስቶቻችን ነን እናት ወይም አባታቺንን ኡፍፍፍ፣አይ፣ፋራ የምንላቸው ስለዚህ comma ውስጥ ነን ማለት ነው

''3ኛዎቹ,
ሰዎችን አዛ የሚያድጉ ሰዎች ናቸው''።ሰላም አደራቺሁ ሲባል ምን አገባህ!!!፣አይይ ይሄ ሰውዬ ጥሩ አይመልስልንም ብለው ዝም ብለውት ሲያልፉ ደሞ ምን ይዘጋሀል የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ።

''4ኛ,
ኸምር የሚጠጣ ሰው ነው,ዛሬ ወጣቱ አራዳነት እየመሰለው ጨብሲ እያለ፣ ትላልቁ ሰው ኮፍያውን በኪሱ እያረገ ቢራ እንደሚጠጣ አሏህ ነው የሚያውቀው ።

''5ኛ,
ሪባ/ወለድ የበላ ሰው ነው አሉ፣ይሄ ደሞ ለየት ይላል አንዳንድ ሰው ጭራሽ ሃራም አይመስለውም ።

እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ ቢያንስ ከ5ቱ ሁለቱ ወይም ሶስቱ እኛ ላይ አለ ፣ይህ ማለት ኸቲማቺን ያሰጋናል ማለት ነው።በተለይ ደሞ የወላጅ ሃቅ.......ይሄ ወሏሂ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፣አሏህ የሚያዘውን እስካልከለከሉን
፣የከለከለውን አስካላዘዙን ድረስ ወላጆቻችንን የመታዘዝ ግዴታ አለብን።

እረ ወሏሂ አደብ አንሶናልና
የወላጆቻችንን ሃቅ እንድናሟላ አሏህ ይርዳን፣ኻቲማቸው ከማይበላሽባቸው ሰዎች አሏህ ያድርገን ።

ከ5ቱ አንደኛው ላይ ተዘፍቆ ላለው ወንድማሽን/እህታችን ይሄን ፁፍ share በማረግ የኸይሩ ተካፋይ እንሁን።
@Reyan_meme_and_islamic_post