Get Mystery Box with random crypto!

Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter)

የቴሌግራም ቻናል አርማ researchrc — Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter) R
የቴሌግራም ቻናል አርማ researchrc — Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter)
የሰርጥ አድራሻ: @researchrc
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.11K
የሰርጥ መግለጫ

🔷 Business proposal
🔷 Proposal(Masters)
🔷 Research ማማከር
🔷 survey questionnaire ለማዘጋጀት እናማክራለን
🛑 ለተመራቂዎች ተማሪዎች ጥሩ ርዕሰ እንዴት መምረጥ እንዳለባችሁ እናማክራለን!

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-29 13:46:31 ሪሰርች Guideline በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!


GOOD NEWS
በማንኛውም የትምህርት መስክ በማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው፣ #የመመረቂያ_ፅሑፍ ለመስራት ልዩ ድጋፍና እገዛ ለሚፈልጉ ተመራቂ ተማሪዎች ሁሉ፥ ያሉበት ቦታ ሳይገድበን #ጥራት ያለው አገልግሎት #በተመጣጣኝ ክፍያና #በተፈለገው_ጊዜ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
Contact us @rese100arch
+251920256875
7.3K viewsedited  10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 09:20:34 Referencing & Citation ምንነት!
ዛሬ ስለ APA/ Harvard style ስለሚባለው እንመልከት በሚቀጥለው ስለ Vancouver እመለሳለሁ ።

Harvard style እና APA Style Author-Data style System የሚከተሉ ስሆኑ፣ በጣም ተመሳሳይ ናቸው፣ ነገር ግን የተወሰኑ ልዩነት አላቸው።ልዩነቶቹን እመለስበታለሁ ።

ሁለቱም በጽሁፋችሁ(Citation) ላይ የሚቀመጠው Author እና year ነው። የአጻጻፍ ላይም በጣም ተመሳሳይነት አላቸው ።

APA/Harvard በጣም ተመሳሳይ ስለሆኑ አንድ ላይ እንመልከት፣ የAPA እና Harvard ልዩነት በሚቀጥለው ጽሁፍ አቀርበለው።

ባparagraph መጀመሪያ የAuthor name ስገለጽ ከታች በለው መልኩ Cite በመረግ መጀመር ይቻላል።

Cormack (1994) states that "when writing...".
OR
Smith (1946) and Jones (1948) have both shown ...
OR
Further research (Green, Harris and Dunne, 1969) showed...

ከparagraph መጨረሻ ላይ ስሆን
፣በዚህ ጊዜ ከጽሁፉ መጨረሻ ላይ ከታች እንደለው መስቀመጥ ይቻላል።

After the paragraph (Cormack, 1994)

ብዙ Authors አንድ ጽሁፍ ላይ ከሆነ፣ et al የሚለውን እንጠቀማለን ፣
ለ Harvard ከሶስት በላይ የሆኑ Authors ስሆን et al የምንጠቀመው ፣ ለ APA ደግሞ ከሁለት በላይ ስሆን et al የሚል ጽሁፍ በመጨመር Cite መድረግ ይቻላል

Green, et al. (1995) found that the majority ...

ወይም ከ paragraph መጨረሻ ላይ (Green, et al., 1995)

የብዙ Authors የተላያዩ ጽሁፎችን በአንድ አንቀጽ(paragraph)Cite መድረግ ስያስፈልግ


Recent research (Collins, 1998; Brown, 2001; Davies, 2008) shows that...

ወይም ከparagraph መጨረሻ ከታች በለው መሠረት የሁሉንም ጻሀፊዎች ስም በመጥቀስ መስቀመጥ ይቻላል

(Collins, 1998; Brown, 2001; Davies, 2008)

አንድ Author ብቻውን የተላያዩ ጽሁፎችን በተላያያ ጊዜ(ዓመት) የጻፈውን ለመስቀመጥ ስሆን ደግሞ



as suggested by Patel (1992; 1994) who found that...

የተላያዩ ጽሁፎች በአንድ Author በተመሳሳይ ጊዜ(ዓመት ስሆን

Earlier research by Dunn (1993a) found that...but later research suggested again by Dunn (1993b) that ...

Author (ጻሀፊው) ባይተወቅስ? ጻሐፊውን ለማውቅ ትግል ያስፈልጋል፣ ግን ይህ ባይሆን እና የግድ ጽሁፉ Cite ማድረግ አስፈላጊ ከሆነ፣ title በ italic ይጻፋል ከዓመተ ምህርት በፊት ግን Anon.. የሚል ይሁፍ እንጠቀማለን ።

Marketing strategy (Anon., 1999)

Second hand referancing( cross referencing) የሚበል አለ፣ ይህ ማለት ሌላ ሰው Cite ያደረገውን ነገር ግን በእናንተ እጅ ላይ የሌላውን ጽሁፍ ከሌላ ጽሁፍ ላይ ስተገኙ፣ እና Cite ስታደርጉ ነው


Research recently carried out by Brown (1966 cited in Bassett, 1986) found that ...

ወይም በ paragraph መጨረሻ ላይ፣
(Brown, 1966 cited in Bassett, 1986, p.142)

ይህ ማለት፣ Brown በጻፈው አድስ ጽሁፍ ውስጥ Bassett የጻፈውን Cite አድርጓል፣ እናንተ ግን ከ brown ዶክሜንት ውስጥ የ Bassettን ሀሳብ ስትወስዱ ነው፣ ነገር ግን የBassett ዶክሜንት በእጀችሁ የለም፣ ወይም አለነባባችሁም ማለት ነው፣

ይህ መንገድ ግን አይመከርም፣ በብዙ ምሁራን ዘንድም ተቀባይነት የለም።

ጊዜ ወይም year የሌላው ከሆነስ? ከAuthor ቀጥሎ n.d. የሚል ተቀጽላ እንጠቀማለን፣


Smith (n.d.) has written and demonstrated......

ነገር ግን Author ወይም year የሌላውን ጽሁፍ እንደ Reference እንድንጠቀም አይመከርም ።

ሁለቱም Author እና Year የሌላው ቢሆንስ

APA vs Harvard citation

ከዚህ በፊት እንደተመለከነው ፣ APA እና Harvard Style በጣም ተመሳሳይ ስሆኑ፣ ትንሽ ልዩነት አለችው ። ልዩነቱን እንመልከት፣

ከ paragraph መጨረሻ( intext citation)

APA: (Shadid, 2020)
Harvard: (Shadid 2020)

Page Number ለማሳየት

APA:(Armstrong, 2015, pp. 3-17)
Harvard:(Armstrong 2015: 3-17)

ለብዙ Authors et al አጠቀቀም ይለያያል። et al አጻጻፍም ትንሽ ይላያያል et al የሚለውን ተመልከቱ


APA: use (et al.,) for more than two authors
Harvard: use (et al.) for more than three Authors

Referancing

APA: Ryan-Flood, R., & Gill, R. (2010). Secrecy and silence in the research process: Feminist reflections. Routledge.

Harvard : Ryan-Flood, R., and Gill, R. 2010. Secrecy and Silence in the Research Process: Feminist Reflections. London: Routledge

ነገር ግን ያላቸው ልዩነት ውስን ቢሆንም፣ ይህ ብቻ አይደለም ።
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ!
Automatic References
Automatic List of tables
Automatic List of figures
Citation
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!





ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
Automatic Tables of Content.
Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ




#share
8.8K viewsedited  06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 19:41:19 ምን አይነት የሪሰርች ርእስ ይፈልጋሉ?
7.0K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 19:13:33 Mechanical engineering Project titles
1: vehicle breaking system
2: wind energy based water pump
3: harvesting machine
4: solar energy based automatic florr cleaner machine
5: air conditoning system
6: Design of mechanical driven reaper
7: Design of inline seeder with mechanical metering system for maize & wheat/barley
8: Design of inline seeder with mechanical metering system for maize & wheat/barley
9: Solar Enjera Cooker with Energy Storage system
10: Mathematical modeling and experimental test of heat pipes for solar thermal application
11: Design of a Solar Tracker
12: design of the feeder system for stone crusher plant
13: Design of Solar absorption
14: refrigeration of 5TR Design of Milk Transportation Vessel & Cart
15: Design of Milk Transportation Vessel & Cart
6.9K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 17:32:25 GOOD NEWS
በማንኛውም የትምህርት መስክ በማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው፣ #የመመረቂያ_ፅሑፍ ለመስራት ልዩ ድጋፍና እገዛ ለሚፈልጉ ተመራቂ ተማሪዎች ሁሉ፥ ያሉበት ቦታ ሳይገድበን #ጥራት ያለው አገልግሎት #በተመጣጣኝ ክፍያና #በተፈለገው_ጊዜ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
Contact us @Aman_research_100
0923224714
6.2K viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 07:27:04
ቻናላችን?
Anonymous Poll
97%
3%
431 voters6.5K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 20:13:05 ጥናታዊ ጽሁፍ/research ማዘጋጀት ትፈልጋለህ? እነዚህን 15 ነጥቦች ልብ በል።
የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡ ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡
በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡ ዝርዝሩን ተመልከቱት፤

የጥናቱ ርዕስ/ Topic
የጥናት ርዕስ ቃላት ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ትክክለኛ ስዋሰው፣ ገላጭ ቃላት፣ የጥናቱን ችግር፣ ሥፍራ/ቦታ በተቻለ መጠን በሚስብ ሁኔታ ቢጻፍ ይመረጣል፡፡ ርዕሱን የሚያነብ ሰው የጥናቱን ይዘት በቀላሉ እንዲረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚሁ በፊት ገጽ ላይ ከርዕስ በተጨማሪ፣ የአጥኚው/ዎቹ ሙሉ ሥም፣ ጥናቱ የሚቀርብለት ሠው/ተቋም፣ጥናቱ የተዘጋጀበት ወቅትና ሥፍራ ይጠቀሳሉ፡፡

ምስጋና/ Acknowledgement
የምሥጋና መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ ጥናቱ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በተለያዩ መልኩ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠዎች የሚመሰገኑበት ክፍል ነው፡፡ ሠው ብቻ ላይመሰገንበትም ይችላል፡፤ ሥፍራዎች፣ ሁኔታዎች፣ ወቅቶችና ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ክፍል ሊመሰገኑ ይችላሉ፡፡

ማውጫ/Table of content
በማውጫ የጥናቱ የተለያዩ አቢይና ንዑስ ክፍሎች የሚገለጽበት ገጽ ይጠቀሳል፡፡

መግቢያ/ Introduction
በዚህ ክፍል የጥናቱን መነሻ ለአንባቢዎች መረጃ የሚሰጥበት ነው፡፡ መግቢያ መንዛዛት የለበትም፡፡ አንድ ገጽ ይበቃል፡፡ ዞሮ ዞሮ የአንድ ጥናት መግቢያ የአንባቢውን ስሜት የሚቀሰቅስ፣ የጥናቱን ወሰንና አቅጣጫ የሚያመላክት፣ጥናቱን እንዴት እንደሚሰራና የጥናቱን ጭብጥ የሚያሳይ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡

የጥናቱ ዓላማ /Objective
የጥናት ዓላማ ከተለያዩ ርዕሶች ጋር ጥልቅ ቁርኝት አለው፡፡ የጥናት ዓላማ፣ ከጥናቱ ችግሮች፣መላ ምቶች መረጃና ውጤት አቀራረብና አተናተን፣ ማጠቃለያና መደምደሚያ ጋር ይተሳሰራል፡፡ የጥናት ርዕሰ ከተመረጠ በኋላ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በሚገባ ከተረዳን በኋላ የጥናት ዓላማዎች ይዘጋጃሉ፡፡
የጥናት ዓላማዎች አቢይና ዝርዝር ተብለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዓላማዎች በጥናቱ የተጠቀሱ ቁልፍ ችግሮችን ወይንም መላምትን መሰረት ተደርገው ይቀረጻሉ፡፡

Statement of the problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።

የጥናቱ አስፈላጊነት/ Significance of the study
ጥናት ለተለያየ አገልግሎት ይውላል፡፡ በዚህ ክፍል የዚህን ጥናት ውጤት አስፈላጊነት ግልጽ በሆነ መልኩ በዝርዝር ይቀመጣል፡፡
የጥናቱን ወሰን/ Scope of the study
በዚህ ንዑስ ክፍል የጥናቱ አጠቃላይ ስፋት፣ ርዝመትና ጥልቀት ይገለጻል፡፡ ለምሌ ያህል፣ ጥናቱ የት እንደሚሰራ፣ በእነማን ላይ እንደሚሰራ፣ ጊዜና የመሳሰሉ ወሰኖች በግልጽ ይቀመጣሉ፡፡ ወሰን ያልተበጀለት ጥናት መጀመሪያውንና መጨረሻውን ማወቅ ይቸግራል፡፡

የጥናቱ ታሳቢ ክፍተቶች/ Limitation
አንድ ጥናት ሲካሄድ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ሊሆን አይችልም፡፡ የተለያዩ ክፍተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉና በዚህ ክፍል በጥናቱ ወቅት ሊገጥሙን የሚችሉ ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ችግሮች ከአጥኚው አቅም በላይ ሊሆኑ ይገባል እንጂ ሁሉንም ችግር መጥቀስ አይገባም፡፡ ታዲያ በዚህ ክፍል ክፍተቶቹን ለማጥበብ በአጥኚው ሊደረጉ የሚገቡ ጥረቶችም ሊካተቱ ይገባል እንጂ ክፍተቶችን ብቻ ጠቅሶ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ አይገባም፡፡

የጥናቱ ዘዴና አካሄድ/ Methodology of the study
የአንድ ጥናት ዘዴና አካሄድ/ Methodology እንደየ ጥናቱ ጠባይ፣ችግር፣አይነትና ዓላማ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ዘዴና አካሄድ መጥቀስ ማለት በአጭሩ ጥናቱ እንዴት እንደሚሰራ፣ የት እንደሚሰራ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ፣ የመረጃውም መሰብሰቢያ ዘዴ እንዴት አንደተዘጋጀ፤ ምን አይነት ጥናት እንደሆነ፣ የናሙና ይዘት፣ አመራረጥና መጠን (ናሙና ያለው እንደሆነ) ፣ ውጤቱ እንዴት እንደሚተነተን፣ውጤቱ እንዴት እንደሚሰራጭና የመሳሰሉ የጥናቱን አጠቃላይ አሰራርና አካሄድ መግለጽ ማለት ነው፡፡

የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ/ Literature Review
በዚህ ክፍል ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶችንና ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈ-ሃሳቦችን በጥልቀት ይመረመራሉ፡፡ ተዛማጅ ጽሁፍ በጥናት ውስጥ በተለያየ መልኩ ማካተት የሚስችል የጥና ጽሁፍ ምልከታ አጻጻፍ አለ፤ ከዚህ ውስጥ የሚስማማንን መርጠን መጠቀም የእኛ ምርጫ ነው፡፡ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ሥራ ሰፊና ጥልቅ ነውና በዚህች አጭር ንዑስ ርዕስ ሁሉን መግለጽ ይከብዳል፡፡

የጥናት ግኝት አቀራረብ ትንተና/ Data analysis & Interpretation
የአንድ ጥናት ውጤት እንደ ጥናቱ አይነትና የመረጃ ማጠናቀሪያ ሥልት ሁኔታ፣ በተለያየ መልክ ሊቀርብና ሊተነተን ይችላል፡፡ አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና የሎጂክን ስልት በመከተል በግኝቶቹ ላይ የሚደረገው ትንታኔና ትርጉም እንጂ ጥሩ የሆኑ መረጃ ማቅረብ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በግኝት አቀራረብና አተናተን ወቅት አስተያየትን ከተጨባጭ ሁኔታ መለየት፤የጥናቱን ወሰን ማስታወስ እንዲሁም የተሳሳተ ትንታኔና ትርጉም ላለመስጠት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ/ Conclusion
ጥናቶች የተለያየ ስፋትና ጥልቀት አላቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክፍል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሉ የወቅቱን ሁኔታና ግኝቶች በማጠቃለል አጠር ተደርጎ የሚቀርበት ነው፡፡

የመፍትሔ ሐሳብ/ Recommendation
በጥናቱ የተለዩ ችግሮችና መንስዔዎቻቸው ከታወቁ በኋላ የመፍተሄ ሃሳቦች በዝርዝር ይቀመጣሉ፡፡ ስለዚህ የመፍተሄ ሃሳቦችን ከማቅረባችን በፊት ችግሮቹን በሚገባ መረዳት ይገባል፡፡
በዚህ ክፍል ሁሉም የመፍሔ ሀሳብ ሊገለጽ አይገባም፡፡ ተጨባጭ ሁኔታን በመረዳት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት በቅደም ተከተል ማቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

አባሪ/ Appendices
በዚህ ክፍል ለጥናቱ የተገለገልንባቸውን ዝርዝር የመረጃ ማጠናቀሪያ ቅጾችና ሌሎች ዝርዝር ግብዓቶች ይቀመጣሉ፡፡
ጥናቱ ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡

ማጣቀሻ /Reference
ይህ ክፍል ለጥናቱ የተጠቀምናቸው መረጃዎች የሚገለጽበት ነው፡፡ መረጃዎቹ በማን፣ መቼ፣የት እንደተጻፉ በግልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ስምምነት የተደረሰባቸው የተለያዩ ማጣቀሻ አጻጻፍ ስልቶች አስተምህሮዎች አሉና በተፈላጊው ስልት ማጣቀሻን በግልጽ በማስቀመጥ የጥናቱ እውነተኛነት በዚህ ክፍል ይረጋገጣል፡፡
7.1K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 19:49:48 ሪሰርች Guideline በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ!
6.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 16:17:48 ለተመራቂ ተማሪዎች (Research info)፦
#ጥሩ_የጥናት_አቀራሪብ_መረጃ
Good research presentation (Defense)
.
ጥሩ አቀራረብ እንዲያደርጉ የሚረዱዋችሁን አንዳንድ ነጥቦች።
.
ጥናታዊ ጽሑፍን በጥሩ ሁኔታ ለማቅረብ (good presentation) ከሚረዱ ቁልፍ ነገሮች አንዱ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (PowerPoint) ነው። ጥሩ ማብራሪያ ነጥብ (power point) እንዲኖርዎ ደግሞ እነዚህን ይጠቀሙ፦
.
#1ኛ. ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Powerpoint) ብዙ ስላይድ አይኑረው። በ15 ደቂቃ ለማቅረብ እስከ 15 በዛ ከተባለ ከ20 እስከ 25 ማሳያ (slide) እጅግ በቂ ነው።
.
#2ኛ. ማሳያ (slide) በብዙ ጽሑፍ የተጠቀጠቀ መሆን የለበትም። ፎቶዎችንናቃላት ሰንጠረዦችን የበለጠ በደምብ ይጠቀሙ። "አንድ ፎቶ ወይም ሰንጠረዥ ከ1000 በላይ ገላጭ ነው" የሚለውን አባባል ልብ ይበሉ።
.
#3ኛ. መብራራት የሚፈልጉ ቃላትን ብቻ በርዕስ መልክ ይጻፉ። ማብራሪያቸውን የግድ ማሳያ (slide) ላይ መፃፍ አይጠበቅብዎትም።
.
#4ኛ. የሚቀርበው ጥናት እጅግ ሰፊ ይዘት ያለው ቢሆን ለመመጠን ሳይቸገሩ በማሳያ (slide) ላይ ለመዳሰስ ማሳያዎትን (slide) በክፍል በክፍል (part) ይክፈሉት።
....... Introduction (መግቢያ)
....... Main Body (ሃተታ) as Discussion
....... Conclusion ( መደምደሚያ) ያድርጉት።
.
#5ኛ. ከአንዱ ማሳያ (slide) ወደ ሌላው ሲዘዋወሩ (ሲሸጋገሩ) ጊዜ እንዳይወስድብዎ (እንዳይንቀረፈፍ) Animation ባይጠበሙ ይመረጣል።
.
#6ኛ. በማሳያዎ (slide) ላይ ሚሰፍሩ ጽሁፎች በትንሹ በ24 መጠን (Font Size) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
.
#7ኛ. የጽሑፎቹ ቅርጽ አይነት (Font type) "Time new roman" ቢሆን የተሻለ ነው። ከዚህ ካለፉ ግን Nyala እና Countur ይጠቀሙ።
.
#8ኛ. የማሳያ (slide) ጽሑፎች እጅግ ብዙ የቀለም (Font colour) ዝብርቅርቅ የበዛበት ከሆነ አትኩሮትን ግራ ስለሚያጋባ ብዙ ቀለም አይጠቀሙ። ከተቻለ በአንድ አይነት ቀለም ቢሆን ካልሆነ ግን ልዩ ገለጻ የሚፈልጉትን ለማቅለም ሁለት ቀለሞች በቂ ናቸው።
.
#9ኛ. አስተያየት (professional recommendation) በሚለው የጥናት ክፍልዎ ውስጥ ከተማሩበት አንጻር ለደረሱባቸው ችግሮች መንገዶችን ለመጠቆም ይሞክሩ ይንጅ "
#ድርጅቱ_ይህንን_ችግር_ማስተካከል_አለበት " የሚል ደረቅ ትዕዛዝ ከማስገባት ይቆጠቡ። የሚያስተካክለው እንዴት ባለ ዘዴ፤ መቼ፣ በማን፣ የት፣ .. እንደሆነ ሙያዊ ድጋፍ መስጠትዎን አይርሱ።
.
. ኃይል ሰጪ ማብራሪያ ነጥብ (Power point) እንዲህ ካዘጋጁ በኋላ፦
.
#1ኛ. አለባበስዎን ያስተካክሉ። እርቃንን የሚያሳይ፣ ተመልካችን የሚያሳፍር፣ ለመታደም የመጣን ሰው ሰላም የሚነሳ፣ ማንነትን የማይገልጽ ልብስ ለእርስዎ የሚኖረውን ክብርና ዋጋ በእጅጉ ይቀንሳል። ጥሩ አለባበስ በራስ መተማመንንም ከፍ ያደርጋል። ወንዶች ሙሉ ልብስ (በተለምዶ 'አምባሳደር' የምንለው) ሴቶች ቢያንስ እስከ ጉልበታችሁ የሚዘልቅ የጨርቅ ጉርድ እና ኮት ወይም እጀሙሉ ዠሚዝ የተሻለ ነው። እንደ ገምጋሚው ፍላጎት ሊለይ ይችላል እንጂ ባሕልንና ሀገርን የሚገልጽ ቢሆን በግሌ ደስ ይለኛል።
.
#2ኛ. ለንግግር ቅላጼ (pronounsation) ከመጨነቅ ይልቅ የሚፈልጉትን ሀሳብና ማብራሪያ ለማስረዳት መሞከር የተሻለ ነው። የቋንቋ ተማሪዎች በዋና የቋንቋ መስክ፣ ከዚያ ውጪ ያላችሁት ደግሞ በሚችሉት የእንግሊዘኛ ቃላት ለማቅረብ ይሞክሩ።
.
#3ኛ. ያዘጋጁትን ማሳያ (slide) ከማቅረብዎ በፊት ደጋግመው ያንብቡ።
.
#4ኛ. የማያውቁትን ነገር ከመናገርም ሆነ በየማሳያ (slide) ላይ ከመጻፍ አጥብቀው ይቆጠቡ።
.
#5ኛ. በሚያቀርቡበት ጊዜ በክፍል ውስጥ ያሉትን ሰዎች በአይን ቅኝት መቆጣጠርዎን አይርሱ። ፈጽሞ አይደንግጡ አይፍሩ። የተሰበረቡት ሰዎች ድሮ የነበሩ እንጂ እንደ አዲስ ፍጥረት አያስቧቸው።
.
#6ኛ. ለሚጠየቁት ጥያቄ በተረጋጋ ስሜት ሆነው ከጥናትዎ አንጻር የተደረሰበትን ውጤት አገናዝበው ይመልሱ።

"A good presentation should be like a women's skirt long enough to cover the subject and short enough to create interest" Winston Cherchil
.
.
.
መልካም እድል!!!!
8.9K viewsedited  13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:48:45 ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ቢሆንም ለሥራው ጥራት ሲባል ሳይታለፍ መከናወን ያለበት ተግባር
ነው፡፡
የቃል መጠይቅ/Interview/
ቃለ መጥይቅ ብዙውን ጊዜ ከጽሑፍ መጠይቅ ጋር አብሮ የሚሄድ ሲሆን በዚህ ዘዴ
አማካኝነት የሚገኝ መልስ እንደጽሑፍ መጠይቅ ውሱን ሳይሆን ሰፋ ያለ ይሆናል፡፡ ሆኖም
ለጽሑፍ መጠይቅ እንደሚደረግ ሁሉ ለቃለ መጠይቅም ዝግጅትና ዕቅድ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጥያቄዎችም አመክኖን/logic/ በተከተለና ተገቢ በሆነ ቅደም ተከተል
መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
በቃለ መጠይቅ አማካኝነት የሚገኝ መልስ በጠያቂውና በተጠያቂው መካከል በማካሄድ ነፃ
ውይይት ነው፡፡ ለዚህም በሁለቱ መካከል የተቀራረበና መተፋፈር የሌለበት ግንኙነት
እንዲኖር ጠያቂው ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ጠያቂው ሞቅ ያለ ፈገግታና ትህትና
የተሞላበት አቀራረብ ቢኖረው ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ይረዳዋል፡፡ በቃለ መጠይቅ
ወቅት ተጠያቂውን የሚያስከፉ አባባሎች መቅረብ የለባቸውም፡፡ በተጨማሪም ጠያቂው
ግትርነትንና በውይይት ውስጥ የተደጋገመ ጣልቃ ገብነትን ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
ከውይይቱ የሚገኙትን መልሶች/ሃሳቦች/ ውይይቱ በሚካሄድበት ወቅት መመዝገብ ወይንም
በቴፕ መቅዳት በተጠያቂው በኩል ጥርጣሬንና ፍርሃትን ሊያስከትልና አንዳንድ ሃሳቦችን
ሊደብቅ ስለሚችል ቢቻል መልሶችን/ሃሣቦችን/ ከውይይቱ በኋላ መመዝገብ ይመረጣል፡፡
የመስክ ምልከታ (Field Observation)
የመስክ ምልከታ የተቀነባበረ በቅድሚያ ለታወቁና ለታቀዱ ጥያቄዎች መልስ ከማግኘት
አኳያ የጠለቀ ማሰብንና መመራመርን ተመርኩዞ የሚካሄድ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም
በየዕለቱ በዘልማድ ከሚካሄደው ምልከታ በጣም የተለየ ነው፡፡
በመስክ ምልከታ አማካኘነት የሚገኝ መረጃ ሪፖርት ቀደም ሲል በመስኩ ከነበሩ መሪ
ንድፈ ሃሳቦችና ከጥናቱ መነሻ መላምት ጋር ተገናዝቦ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ለጽሑፍና
ለቃለ መጠይቅ እንደሚደረገው ሁሉ የመስክ ምልከታ ሪፖርት በጥንቃቄ ተመዝግቦ
አጥኚው እንደ ማስረጃ ሊያቀርበው ይችላል፡፡
የጽሑፍ መረጃ (Related literature) እና ፈተና (Test) ሌሎች ተጨማሪ የመረጃ
መሰብሰቢያ ስልቶች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡

በቀጣይ የናሙና አመራረጥ (Sampling) ይቀጥላል...........
8.9K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ