Get Mystery Box with random crypto!

ወንድማችሁ ፀጋዬ ጳውሎስ ነኝ ሰላም፣ ፍቅር፣ ጸጋ፣ ምህረት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ የቃሉ ኃይልና ህይ | ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ

ወንድማችሁ ፀጋዬ ጳውሎስ ነኝ
ሰላም፣ ፍቅር፣ ጸጋ፣ ምህረት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ የቃሉ ኃይልና ህይወት ይብዛላችሁ!! እንዴት ናችሁ የተወደዳችሁ የዚህ ድንቅ ቡድን አባላት በሙሉ!?
እናም አመጣጤ ከላይ በተነሱ ሃሳቦች ላይ የራሴን ምልከታ በታላቅ ትህትና ለማስቀመጥ ነው።
ዩኒቨርሲቲ የሚታየውን የተቃራኒ ጾታ ግኑኝነቶችን ፍቅር ብለን ሊንጠራው እንችላለን?
እይታዬ፦ ልንጠራውም ላንጠራውም እንችላለን! እንዴት ፍቅር ነው ማለት እንችላለን?
መቼስ እያወራን ያለነው በሁሉቱ ተቃራኒ ጾታዎች መካከል የምፈጠረውን መሳሳብና መፈላለግ የሚያመጣው፤ ይሄም ትክክለኛ የሰውኛና የወጣትነት ጤናማ ባህሪ ነው ብለን እንወስዳለን፥ በተቃራኒው ደግሞ በፍቅር ስም የሚደረግ የአመንዝራ ህይወት ልምምድ ነውና ስለእሱ ብዙም ማውራት ሳያስፈልግ ኪሳራውን እንረዳዋለንና ልለፈው። ስለዝህም በአጠቃላይ ማንሳት የምፈልገውና የምጠይቀው ነገር ብኖር፦ አንድ ወጣት ተማሪ ሆኖ ወደ ዩኒቨርስቲ ስገባ ምን አላማ አንግቦ ይገባል ነው ትልቁ ጥያቄ!! ትምህርትን በውጤታማነት ለመማርና በዚያውም እግዚአብሔርን በመሠጠት ማገልገል ነው ብዬ አስባለሁ። የህይወት አኗኗር ደረጃ(Steps) መዛባት አደገኛ ነው ወገኞቼ። አስቡት፤ አንድ ታዋቂ ሯጭ ቀነንሳ በቀለ እየሮጠ በመሐል ውሃ ተጠምቶ ውሃን አይቶት ቆም ይልና ጊዜውን ቢያባክንና ቢሸነፍ ከእሱ አልፎ ለእኛም ምተርፍ መሠበር፤ በርግጥ አንዳንድ ሰዎች አሉ አትሌቱ ውሃ ተቀብሎ እየሮጠሞ እየጠጣም ሩጫውንም እንደምያሸንፍ ሁለቱን አብሮ ማስከየድ የሚችሉ፤ የእኛ ስኬትም ውድቀትም እኛን ብቻ አይጎዳምም አይጠቅምም፤ ከጀርባችን ብዙ ትውልዶች አሉና ምንም ይሁን ምን ከመንገዳችን ወሳኔ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ።
እናም በዚህ ዘመን በብዛት ብዙወቻችን በልጅነት/በሌጋነት ወደ ዩኒቨርስቲ እንገባለንና ፍቅር ቀጥሎም ትዳር የምጠይቀውን የአዕምሮና ስነልቦና፣ የገንዘብ፣ የእውቀት ዝግጁነት አይኖረንም። ስለዝህም ከሁለት ያጣች መሆናችንን ጸሐይ የሞቀው ሀቅ ይሆናል ማለት ነው፤ ለዋናው አላማችን፤ ለትምህርታችንም ለፍቅርም ሳንሆን ውዱንና እንቁን የመዝራትና የፈሬያማነት ወጣትነት ዘመን እናባክናለንና ፍቅር ቢይዘንም እንኳን እራሳችንን ከአላማና ከጊዜ አንጻር challenge ቢናደርግና ለነጊያችን ጥንቃቄ ቢደረግ ባይ ነኝ። በዚህም ከብዙ መባከን ከአላማችን አለመሰናከል ከከንቱ ልብ መሰበር ለቅድስና ፈተና ከምሆኑ ነገሮች መትረፍን ጨምሮ በአጠቃላይ ለነገያችን ባለውለታ ለመሆን!!
ጌታም ከመባከን ህይወት ይጠብቀን ዘንድ ተግተን እንጸልይ።

ግኑኝነታቸውስ ምን ያኽል የሚጸና ነው?
በብዙ ወጣቶች እንዳየሁት almost ለlife ካልሆነ የለም ማለት ይቻላል! እንዴትስ ይጽና!?
ስሜት እንጅ ጽኑ አላማ ለዚያ የምያበረታ environment ስለሌላቸው ግንኙነቱም አይጸናም!!
እውነትም ለክርስቲያን ተማሪዎች ፈሎ እንደትዳር አጋር ማገኛ ማሰብ እንችላለን? ነው ብለን ካሰብንስ ከትምህርት አላማ ጋር አይጋጭብንም?
አዎን ማገኛ ልሆን ይችላል፤ እኛው በእኛው ካልተግባባንና ካልተጋባን ማን ይሁን ታድያ!
በዚያው ተዋውቀው በንጹ ልብ አብሮ እያገለገሉ ቆይቶ ከተመረቁ በኃላ አንዳቸው በአንዳቸው ልብ ከብዶ ብገኙና በፍቅር ቢጣመሩ እጅግ ድንቅና ውብ ነው ነገር ግን በግቢ እያሉ relationship ከጀመሩ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር መሠናክል መሆናቸው ነጭ ሀቅ ነው፤ ይሄም ባይታሰብና ለእግዚአብሔር ቤት ስራ እንቅፋት ሆንን ባለቤቱ እንዳይቆጣን!!
ግንኙነቶች በተፈጥሯቸው ግልጽ ካልሆኑ ብዙ መዘዞችን ይዞ ይመጣሉ፤
ግልጽ እንዳናደርጋቸው ጊዜው አይደለምና እንደብቃቸዋለን
በዚህ መሐል እግዚአብሔር ለክብሩ የሠራው ነገር የሠይጣን መጠቀሚያ ስሆን እናገኘዋለን።
ስለዚህ የተኛውንም ነገር ለማድረግ
የነገሩ አስፈልጎትና ዝግጁነታችንን ጥያቄ ውስጥ ምስገባት እጅግ ወሳኝ ነገሮች ናቸው!!
ፍቅር ስንጀምር ከስሜቱ በዘለለ እነዚህም ጥያቄዎች እራሳችንን ብንጠይቅ እላለሁ
ጊዜው ነው ወይ!?
በአዕምሮ፣ በስነምግባር፣ በስነልቦና፣ በቁስና በኤኮኖሚ ዝግጁ ነኝ ወይ!?

ገና ስለትዳር ሳናስብም
ስለትዳር እያሰብንም
በትዳር ውስጥ ሆነንም
እግዚአብሔር አባት በጤናማ ትዳር ህይወት እንዲባርከን መቼም ከመጸለይ አንቦዝን እላለሁ!!
ሻሎም!!

@relationship4christ
@relationship4christ