Get Mystery Box with random crypto!

Rehoboth Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ rehobothmedia — Rehoboth Media R
የቴሌግራም ቻናል አርማ rehobothmedia — Rehoboth Media
የሰርጥ አድራሻ: @rehobothmedia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

Spiritual Media Ministry to Equip the generation with the word of GOD

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 22:41:23

108 views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 17:55:21 ሰሞኑን ኢየሱስ አማላጅ ነው በሚል ጽሁፌ በሉቃ 19 ላይ ኢየሱስ ሊፈርድ እንዳልመጣ በደምን ጠቅሼዋለው። ኢየሱስ ለፍርድ እንዳልመጣ እና ከፍርድ ቀን በፊት ማንም መፍረድ እንደሌለበት ተናግሯል።
ስለዚህ አንድ ሰው ተግሳፅ በተናገረ ቁጥር አትፍረድ ከማለት ይልቅ የቃሉን ፍቺና ትርጉም ማወቅ ያስፈልጋል። ሌሌው ደግሞ አሁን ቤተክርስቲያን ምትገኝበት ዘመን የፀጋ እንጂ የህግ ዘመን አይደለችም ስለሆነውም ፈራጁ እስኪመጣ ማንም መፍረድ( ቅጣት ሊሰጥ) አይችልም። ስለዚህ ኢየሱስ ያወራው አትፍረድ ያለው አውድ በሙሴ አይን ለአይን ጥርስ ከጥርስ ህግ መሰረት ቅጣት(ፍርድ) መሰጠት እንደሌለበት በሚል አውድ እንጂ የሳተውን ተው ተመለስ የሚለው ሀሳብ ጋር ፈጽሞ ገይገናኝም።ምክንያቱም ማንም ለሰራው በደል ቅጣትም ሆነ ለሰራው በጎ ነገር ፍርድ ሚቀበለው በመጨረሻ ከክርስቶስ ዳግም ምጻት በኋላ ነው። ሲጠቃለለ በአሁኑ ዘመን ማንም የመፍረድ Mandate ሆነ ስልጣን የለውም ምክንያቱም ክርስቶስ ብቻ ነው ፈራጅ ሆኖ በመጨረሻ ሚመጣው።ስለዚህ አትፍረድ ብሎ ከመናገር በፊት ፍርድ ምንድነው አንድ ሰው ምን ሲያረግ ነው ፍርድ ሚባለው ብሎ የእግዚአብሔር ቃል ማንበብ እና መረዳት ጥሩ ነው።
መልካም ንባብ

ከጽሁፉ ከተማሩበት ለሚወዱት አንድ ሰው ሼር ያድርጉ ። ከትልቅ አክብሮት ጋር!
...........................
Join us
@RehobothMedia
@RehobothMedia
@RehobothMedia
632 views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 17:55:21 #አትፍረድ
=====
ይህ ቃል ብዙ ጊዜ ትክክል ባልሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውልን ይስተዋላል። ቃሉ ደግሞ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ሚውለው አንዳንድ ሰዎች ትክክል ያልሆነ ተግባር ሲፈፅሙ ለዚያ ድርጊታቸው ሲተቹ፣ ሲነቀፉ ያ ድርጊታቸው ልክ እንዳልሆኑ ሲነቀፉ ለድርጊታቸው ማምለጫ ወይም እነሱን ሚደግፉ ሰዎች እንደማገዝ መስሏቸው ያንን ድርጊት መሸፈኛ አትፍረድ፣ አንተን ማን ፈራጅ አረገህ ይላሉ።
ለመሆኑ ፍርድ ምንድነው? የቃሉ ታሪካዊ አመጣጥስ ምንድነው?
ፍርድ የሚለው ቃል ከህግ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ቃል ነው።
ፍርድ ለመፍረድ ህግ ያስፈልጋል ሚፈረደውም ህጉን መሰረት ተደርጎ እንጂ ያለ ህግ አንድ አካል ላይ መፍረድ አይቻልም ። ምክንያቱም ፍርድ የአንድ ህግ የመጨረሻኛው ውሳኔ ነውና።
አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ፍርድ በራሱ ሊፈርድ አይችልም።
ፍርድ ለአንድ ነገር የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥ ውሳኔ እንጂ ትችት መሰንዘር አይደለምና።
አሁን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያለውን ለጊዜው እንተውና ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ጎራ ብለን ትክክለኛውን ትርጉምና አጠቃቀም ትንሽ እንይ እስቲ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ይህንን ቃል ሚጠቀሙ ሰዎች አትፍረድ የሚለውን መሰረት ሚያደርጉት መፅሀፍ ቅዱስን ስለሆነ ።
እግዚአብሔር አምላክ ለህዝበ እስራኤል ህግ በሙሴ አማካኝነት የሰጠው ህግ ነው( ዘፀአት 20፣ ዘዳግም 6) እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ህግ ሲሆን አስርቱ ትዕዛዛት በመባል ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ያሉት አምስቱ መፅሀፍ የህግ መፅሀፍት(Pentateuch ወይም Tora)በመባል ይታወቃሉ። ከዚህ መነሻ ተነስተን እግዚአብሄር ለሙሴ ህግን ሲሰጥ ለህጉ ተገዢ የሆኑትን ሲያመሰግን ህጉን ለሚጥሱት ምን ቅጣት እንደሚያስከትል በእነዚህ አምስቱ የህግ መፅሀፍት በግልፅ ሰፍሯል። በእነዚህ ህግ መፅሀፍት ላይ ህጉን ለሚተላለፉ ሙሴ እንዲፈርድ ፍርዱም ምን እንደሆነ በግልፅ ተፅፏል። ለዚህ ነው በፅሁፌ መጀመሪያ ላይ ፍርድ የህግ የመጨራሻኛው ውሳኔ እንደሆነ የገለፅኩት።ስለሆነም በዚያ ህግ መሰረት አንድ ሰው ህጉን ቢጥስ በህጉ መሰረት ፍርድ ይሰጠዋል።
ለምሳሌ
=====
1.“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በበጉም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።” ዘጸአት 22፥1
ህግ:- አትስረቅ ፍርድ:- አራት ወይም አምስት እጥፍ መመለስ

2. ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥
⁴ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
⁵ ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ።
ቢያመነዝር በድንጋይ ተወግሮ ይሞታል"
ዘዳግም 17
ህግ:-ሌሎች አማልክት አታምልክ ፍርድ:- በድንጋይ ወግሮ መግደል

ስለዚህም ነው በኢየሱስ ዘመን በዮሐ 8:10 ላይ ስታመነዝር የተያዘችውን ሴት ሊወግሩ ፍርድ ሊሰጡ ተሰብስበው ሊወግሩ(ሊፈርዱ) ፈልገው። ህጉ ወግረን እንድንገድል (የሞት ፍርድ እንድንፈርድ)ያዝዛል አንተ ምን ትላለህ ያሉት።

እነዚህንና ሌሎች የመፅሀፍ ቅዲስ ክፍሎች ስንመለከት ፍርድ ተብሎ የተፃፈው ወይም ሰዎች ሲፈርዱ የነበረው በህጉ መሰረት የመጨረሻ ቅጣት በመስጠት ማለትም በመስቀል፣ በመውገር ወዘተ እንጂ በአፍ በመናገር አይደለም አይደለም።በሌላ አባባል ፍርድ ድርጊት የሚከናወን ስርዓት ነው።
ታዲያ በዚህ ዘመን አንዳንድ ሰዎች ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ ልምምድ ሲያደርጉ ቃሉ ያልፈቀደውን ሲያደርጉ ወይም ትክክል አይደለህም ተብለው ሲተቹ ቶሎ ብለው አትፍረድ ይላሉ። ታዲያ ይህ በታሪክም በቅዱስ ቃሉም ስንመዝን ምንም መሰረት የለለው እና ትክክልም ያልሆነ አባባል ነው።
አንድ ሰው ትክክል ያልሆነ ነገር ሲያደርግ ትክክል አይደለህም ማለት ፍርድ ተብሎ አይጠራም ፍርድም አይደለም። መፍረድማ ቢሆን ያ ሰው አመንዝሮ ከሆነ በድንጋይ ወግሮ መግደል ነው። ሰርቆ ከሆነ አራት ወይም አምስት እጥፍ ማስከፈል ነው። ታዲያ አንድ ሰው ሀጢያት ሲሰራ ሰርተሃል፣ ተሳስተሃል ማለት መፍረድ አይደለም?
አወ መፍረድ አይደለም መገሰፅ ይባላል።
ብዙ ሰዎች ተግሳፅን እና መፍረድን ቀላቅለውታል።
የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ለጢሞቴዎስ ዝለፍና ገስፅ ይለናል።
“ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ #ዝለፍና #ገሥጽ ምከርም።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2
በሌላም ክፍል ጢሞቴዎስን እንዲህ ይላል።
“ይህን በሙሉ ሥልጣን #ተናገርና ምከር #ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።”
— ቲቶ 2፥15
ታዲያ አንድ ሰው በስህተት ስራ ወይም ትክክል ባልሆነ ነገር ሲገኝ መንቀፍ፣ ትክክል አለመሆኑን መናገር መገስፅ ቃሉ የሚደግፍ ትክክለኛ መፅሀፉ የሚያዝ ተግባር እንጂ ፍርድ ነው የሚል ድምዳሜ ከየት የመጣ ትርጉም ነው?
ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን አትፍረድ ይፈረድብሃል ያለው ዘመነ ኦሪት ሰዎች በህጉ መሰረት የሚፈርዱትን ፍርድ ማብቃቱን እና ፍርድ መጨረሻ እሱ ዳግም መምጣቱን ለማሳየት እንጂ ፍርድ የሚለው አውድ ዛሬ ብዙዎች በሚጠቅሱት አውድ አይደለም።
ዛሬ ብዙዎች ፍርድ ብለው የሚጠሩትን ኢየሱስ በብዙ መልኩ ገስጿል። ለምሳሌ ማቴ 23:13
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።”
በዚህ ክፍል መንግስተ ሰማይ አትገቡም ይላል ይህ ፍርድ ነው ማለት ነው?
እናንተ ግብዞች ይላል ፍርድ ነው ማለት ነው?
ይህ ፍርድ አይደለም እነዚህ ሰዎች ከስህተታቸው ተመልሰው ትክክለኛውን መንገድ እንዲመለሱ እየገሰጻቸው እንጂ እየፈረደ አይደለም። ፍርድማ ቢሆን ወዲያው መንግስተ ሰማይ እንዳይገቡ ከልክሎ ወደ ገሃነመ እሳት መላክ ነበረበት።
ከላይ በአጽኖት እንደጻፍኩት ፍርድ የመጨረሻ ውሳኔ ነው አንድ ሰው ከተፈረደ ቀጣዩ እርምጃ መተግበር ብቻ እንጂ ሌላ እድል የለውም።
በዘመነ ህግ የነበረው አሰራርም ይህ ነበር። ስለዚህ አንድን ነገር ያለ አውዱ ያለ ቦታው መጠቀም አላጎሪ ነው።
ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ሲያገለግሉ በተመሳሳይ መልኩ ሰዎችን ሲገስጹ ነበር ለምሳሌ
3.እናንተ #የእፉኝት ልጆች (ዮሃንስ ማቴ 3:7))
4. #ውሾች ፊሊ 3:2 (ሀዋሪያው ጳውሎስ)
እነዚህ ሁሉ ለእግዚ/ር የተመረጡ አገልጋዮች በአንዳንሶች ስሌት ፈርደዋል ወይም እየፈረዱ ነው ማለት ነው። እነዚህ አገልጋዮች ፍርድ ምን እንደሆነ ኦሪቱንም ሀዲሱንም ጠንቅቀው ያውቃሉ። ማወቅ ብቻ አይደለም ይህ ድርጊት ተግሳጽ ስለሆነ ቃሉም ገስጹ ብሎ ስላዘዛቸው በመገሰጻቸው አክሊል እንደሚያገኙ ጠንቅቀው አውቀው ነው ሚገስጹት እንጂ ፍርድ እንዳልሆነ የፍርድ ቀን ደግሞ ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በኋላ እንደሆነ ጠንቅቀው ሚያውቁ ሚያስተምሩም ጭምር ናቸው።
የተሰሎንቄን መጽሀፍ የጻፈው ስለ መነጠቅ ያብራራው በእጅ ስላልተሰራችው በሰማይ ስላለችው መኖሪያ የጻፈው ይህንን ሁሉ የተግሳጽ ቃል ሲያዘንብ ፍርድ መሆኑን ተምታቶበት አይደለም።
476 views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 13:21:42 #ኢየሱስ_አማላጅ_እንጂ_ፈራጅ_አይደለም።
********************************
ይህ ርእስ ብዙ ጊዜ አጨቃጫቂ ሲሆን ብዙ ጊዜ እንመለከታለን ለምን ቢባል ብዙዎቹ የሚነሱበት መሰረት (ground) ከሚያምኑበት ቤተእምነት ዶክትሪን እንጂ ከመፅሀፍ ቅዱስ ስላልሆነ ነው።
ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ ለሰው ልጆች ሀጢያት ዋጋ ከፍሎ ሰውንና እግዚአብሔርን ሊያስታርቅ (ሊማልድ) እንጂ ሊፈርድ አይደለም የመጣው ። ለዚህም እራሱ ሲናገት እንዲህ ብሏል። “ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም።” ዮሐንስ 12፥47"
ከዚህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ ንግግር ምንማረው ወደ ምድርም የመጣው የሰውን ልጅ ሊያድን እንጂ ሊፈርድ እንዳልመጣ ነው። ሌላኛው ክፍል ሉቃስ 19:10 ላይ " የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና "ይለናል።
ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዓላማ ፍንትው አድርጎ ይነግረናል።ብዙ ሰዎች የኢየሱስን የምልጃ ሚረዱት በተሳሳተ መንገድ ነው።ኢየሱስ ሲያማልድ ሰዎች ሲጣሉ አንተም ተው አንተም ተው ብለው ሰዎች ጎረቤቶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው ወዘተ እንደሚያስታርቁት ልክ ኢየሱስም በዚያ መንገድ ያማለደ( ያስራረቀ) አድርገው ያስባሉ። ልመና ሚለምንም ሚመስላቸው ሰዎች አሉ ለዚያም ነው ብዙዎች የሰዎችን፣ የመልአክትን ምልጃ ከኢየሱስ ምልጃ ጋር አንድ አድርገው ሚያነፃፅሩት።
ኢየሱስ ሰውንና እግዚአብሔርን በዚህ መንገድ አይደለም ያማለደውም ያስታረቀውም። በሮሜ 6:23 ላይ ሲናገር “ የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነውና” ይለናል።
በዚህ ክፍል በተፃፈው መሰረት እና በዘፍ 3 ላይ የሰው ልጅ በሰራው ሀጢያት በሞት መቀጣት እንዳለበት እግዚአብሔር ደንግጎ ነበር ። እግዚአብሔር ሀጢያትን በሰራችሁ ቀን ሞትን ትሞታላችሁ ባለው መሰረት ያ ህገ የአምላክ ትዕዛዝ ስለሆነ መፈፀሙ ግድ ነው። ስለዚህ ያ የሰው ልጅ የሰራው የሀጢያት ክፍያ በሆነ አካል ካልተከፈለ በስተቀር ከቅጣት ማምለጥ አይቻልም። ኢየሱስ በአማላጅነት ስራው የሰራው ያንን ነው። የሰው ልጅ የሰራውን የሀጢያት እዳ የራሱን ደም መስዋዕት አድርጎ ከፍሎ ነው ያስታረቀው እንጂ ከላይ እንደጠቀስኩት ብዙዎች ቅዱሳን ማራቸው ተውላቸው እንደሚሉት በዚያ መልክ አይደለም። ስለዚህ የኢየሱስን ምልጃ በምድር ማንም አልማለደምም ሊማልድም አይችልም የእሱ ምልጃ የራሱን ደም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሰው ልጅ ሁሉ ከፍሏልና። ለዚህ ጉዳይ የዕብራውያን መልእክት እንዲህ ተፅፏል “የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።”
ዕብራውያን 9፥12
“እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።”ዕብራውያን 7፥25
ታዲያ ብዙዎች ስለ ክርስቶስ አማላጅነት ያላቸው ግንዛቤ ልክ ከላይ እንደጠቀስኩት አንተም ተው አንተም ተው አይነት ስለሆነ ጉዳዩንም በዚህ መንገድ ስለተረዱትም ኢየሱስ አማለደ ሲባል ያዋረዱትን ሚሰማቸው። አንድ ሰው ነገሩን በዚም መንገድ ከተረዳ ለዚህ አይነት ድምዳሜ ቢደርስ አይፈረድበትም ምክንያቱም የማማለድ ስራ የሰው አይነት ከሆነ የኢየሱስ መሞት አስፈላጊ አይደለምና። ስለዚህ ነገሩን ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም ወደሚል ድምዳሜ አመጡት። ነገር ግን ኢየሱስ ያማለደውን ምልጃ ቅዱሳን፣ መላእክት ማንም ፍጥረት ሊማልድ በሚችለው መልኩ ሳይሆን የገዛ ስጋውንና ደሙን አፍስሶ ለእግዚአብሔር በመሰዋት የሀጢያት ክፍያ አድርጎ በማቅረብ ነው። ኢየሱስ የሰውን ልጅ ሀጢያት ለመክፈል ነው የመስቀል ላይ መሰቀል የነበረበት እንጂ ለሌላ ጉዳይ አይደለም። የኢየሱስ ምልጃ የተከናወነው በዚህ መንገድ ነው። እስከ ዛሬ ለሰው ልጅ ሀጢያት በዚህ መንገድ የገዛ ደሙን ከፍሎ በመስቀል ላይ ሞቶ ዋጋ የከፈለ ያማለደ ቅዱስ ወይም መልዓክ የለም። ክርስቶስ ኢየሱስ ግን ኣራሱ መስዋእት ሆኖ የሰውን ልጅ ሀጢያት ከፍሎ ነው ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀው ያ በመስቀል ላይ የተሰራው ስራ ነው ማማለድ(ማስታረቅ) የተባለው እንጂ ዛሬ እኛ እንደምናስበው ቅሱዳን፣ ማርያም ልጇን ተውላቸው ትላለች በሚል መልኩ አይደለም። የገዛ ደሙን ይዞ ዕብ ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣል በገዛ ደሙ የሰውን ልጅ ሀጢያት ከፍሎ ሊያስታርቅ(ሊማልድ) እንጂ ሊፈርድ አይደለም።
ታዲያ ኢየሱስ ዳግመኛ ሲመጣ አማላጅ ነው ወይስ ፈራጅ? ይህ በማያሻማ መልኩ ቁርእርንም ሳይቀር ሊፈርድ እንደሚመጣ ግልፅ ነው። ኢየሱስ ዳግም እስኪመጣ ድረስ አሁን በአብ ቀኝ ሳይቀር ያኔ በመስቀል የከፈለው ዋጋ እስከ ዳግም ምፅአት ወይም እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለሰው ልጅ ሀጢያት ያስተሰርያል። ያ የስርዬት ስራ ማማለድ ይባላል።
ስለዚህ ኢየሱስ አሁን ፈራጅ ሳይሆን አማላጅ ነው።
ዳግም ሲመጣ ግን ፈራጅ ሆኖ ሊፈርድ ነው ሚመጣው።
...........................
Join us
@RehobothMedia
@RehobothMedia
@RehobothMedia
486 viewsedited  10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 18:45:43
439 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 19:12:20

518 views16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 17:34:10



...........................
Join us
@RehobothMedia
@RehobothMedia
@RehobothMedia
539 viewsedited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 09:51:24 #ጽዮን_ማርያም_ወይስ_እስራኤል??
=====================================

የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" (ኢሳ.60፥14) ብዙ ሰዎች ይህን ጥቅስ ለማርያም ስግደት(አምልኮ) ያስፈልጋል ለማለት በብዛት ይጠቅሱታል።
እውነት ይህ ጥቅስ ስለ ማርያም ይሆን የሚያወራው???
ለማርያምስ አምልኮ (ስግደት) ያስፈልጋልን???

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል፦
-----------------------------
መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ጊዜ
-አውዱን መጠበቅ
-የመጽሐፉን ሐሳብ ማስጨረስ
-ለማን ነው የተጻፈው
-መቼ ተጻፈ የሚሉትን ጥያቄዎች ጠብቀን ማጥናት ይኖርብናል።

የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" (ኢሳ.60፥14)

ይህ ቃል ስለ ጽዮን መነገሩ እውነት ነው። ሆኖም ይህንኑ ቃል ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ስለማርያም ሲጠቀስ በስፋት እናያለን፥ እንሰማለን፡፡ እውነት ይህ ቃል ስለ ማርያም ይሆን የሚያወራው???

የዚህ ክፍል ሀሳቡ የሚጀምረው ቁጥር 14 ላይ ሳይሆን ከቁጥር 1 ይጀምራል ነገር ግን ማርያም ናት ለሚሉ ሰዎች ቃሉን ከፍ ብለን እንኳን ቁጥር 10 ጀምሮ ስንመለከት "በቁጣዬ ቀስፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና..." ይላል። ታዲያ ይህ ማርያምን እንዴት ያመለክታል? እርስዋ "ከሴቶች መካከል የተባረከች" (ሉቃ 1:28) እንጂ በቁጣው የተቀሰፈች አልነበረችምና።

ስለዚህ ጽዮን በዳዊት የተመሰረተችውና እግዚአብሔር ማደሪያው ትሆነው ዘንድ የመረጣት፥ መቅደሱ የተሰራባት የእስራኤል ከተማ ማለትም ኢየሩሳሌም ናት፡፡ ይህችም ከተማ በቁ.10 ላይ ቅጥር እንዳላት፥ በቁ፡11 ላይ በሮች እንዳሏት፥ እንገነዘባለን። ስለዚህ ከተማ ናት፡፡

ይህንንም አስረግጦ ሲናገር የአሕዛብ ሀገሮች ሁሉ ወደ እግርዋ ጫማ ሲሰግዱ "የእግዚአብሔር ከተማ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን" እንደሚሏት ይናገራል ቁ፡ ጥር 14 ላይ፡፡

ስለዚህ ቃሉ የሚናገረው ወደፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ክብር በምታበራበት በሺው አመት የበረከት ዘመን ቀደም ሲል የናቋት ጠላቶችዋ አሕዛብ ወደ ብርሃንዋ እንደሚመጡ (ቁጥር 3)፥ እንደሚያገለግሏት (ቁጥር 10)፥ እንደሚገዙላት (ቁጥር 12)፥ የመቅደሱንም ስፍራ እንደሚያስጌጡ (ቁጥር 13)፥ ... የሚናገር ትንቢት ነው እንጂ ስለ ማርያም የሚናገር ንባብም ምስጢርም የለውም፡፡

አምልኮን በሚመለከት ለእውነተኛው አንድ አምላክ ብቻ እንደሚገባ ለፍጡር ለመልአክትም ሆነ ለሰው ልጆች (ጻድቃን ለተባሉት) አምልኮ እንደማይገባ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል ያስጠነቅቃልም።

ዘዳግም 6 (Deuteronomy)
4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤

ዘዳግም 4 (Deuteronomy)
15፤ እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤
16፤ እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥
17፤ በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥
18፤ በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥
19፤ ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።

እንዲሁም ንጉሱን ኢየሱስን ለማየት በኮከብ እየተመሩ የመጡት ሰብዓ ሰገል ህጻኑን ከእናቱ ጋር ቢያገኙትም ነገር ግን ስግደትን ለማርያም ሳይሆን ለኢየሱስ እንዳቀረቡ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።

ማቴዎስ 2 (Matthew)
11፤ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ #ወድቀውም_ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።

ይሁዳ 1 (Jude)
17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤

ዮሐንስ 8 (John)
31፤ ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፡— እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው።

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

በወንድም ሀብታሙ አዲሱ
የወንጌል እውነት አገልግሎት ጂማ
...........................
Join us
@RehobothMedia
@RehobothMedia
@RehobothMedia
661 viewsedited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 10:16:48 ስለዚህ ኢየሱስ አማላጅ ነው ሲባል ሌላኛው አቻ ትርጉም ማስታረቅ ሲሆን በምድር ላይ አምላክንና ሰውን በገዛ ሰውነቱ የሀጢያትን ዋጋ በመስቀል የከፈለውን ሂደት አማለደ ወይም አስታረቀ ይባላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀው ወይም ያማለደው በገዛ ስጋው በመስቀል ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በከፈለው ዋጋ እንጂ በየቀኑ የአልም ህዝብ ሀጢያትን በሰራ ጊዜ ሁሉ እባክህ እባክህ ማለቱ አይደለም። ኢየሱስ ሰው በሆነው ማንነቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሏል ያ በመስቀሉ ላይ የሰራው ስራ የማማለድ ስራ ይባላል።ይህ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ የሰራው የማማለድ ስራ ዛሬም ነገም ዳግም እስኪመጣ ይሰራል።
አምላክ የሆነው ኢየሱስ
ኢየሱስ ሰው ብቻ ሳይሆን አምላክም ነው። አንዳንድ ቤተ እምነት አማኞች ኢየሱስ ፈራጅ ነው ይላሉ ይህን ማለታቸው ልክ ነው ነገር ግን ኢየሱስ ፈራጅ የሆነው በአምላክነቱ እንጂ በሰውነቱ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ በአማልክነቱ ይፈርዳል የሚፈርደው ደግሞ ዳግም ሲመጣ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ፈራጅ ሆነ አልነበረም የመጣው አማላጅ ሆኖ እንጂ በሌላ አባባል ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው ስጋ ለብሶ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው ። ምንም እንኳን ኢየሱስ ስጋ ለብሶ ፍጹም ሰው ቢሆንም ፍጽም አምላክም ነው። ኢየሱስ በአምላክነቱ ሀጢያትን አስተሰረየ፣ ሙታንን አስነሳ፣ ድንቅንና ተዓምራትን አደረገ፣ ተሰወረ። እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች በሙሉ አምላክ እንጂ ሰው ማድረግ አይችልም። በሌላ መንገድ አገላለጽ አምላክ ብቻ ማድረግ የሚችላቸው ነገሮች ናቸው።
ማጠቃለያ
ኢየሱስ ፍጹም ሰው እና ፍጹም አምላክ መሆኑን አንድ ሰው ካልተረዳ ስለ ኢየሱስ አማላጅነትም ሆነ ፈራጅነት ይምታታበታል።
ስለዚህ ኢየሱስ አማላጅ የሆነው ስጋ በለበሰው እና ፍጹም ሰው በሆነው ማንነቱ እንጂ በአምላክነቱ አይደለም።
ኢየሱስ ፈራጅ የሆነው መለኮት በሆነው አምላክነቱ እንጂ ስጋ በለበሰው ሰውነቱ አይደለም።
ኢየሱስ አማላጅ ነው ያ ሰው በሆነ ማንነቱ ነው።
ኢየሱስ ፈራጅ ነው ያ ደግሞ አምላክ በሆነ ማንነቱ ነው።
ምክንያቱም ኢየሱስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ስለሆነ። መልካም እሁድ።
...........................
Join us
@RehobothMedia
@RehobothMedia
@RehobothMedia
871 viewsedited  07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 10:16:00
ኢየሱስ አማላጅ ወይስ ፈራጅ?
ኢየሱስ አማላጅ ነው? መልሱ አወ ከሆነ ከማን ጋር ነው ሚያማልደው? እሱ አምላክ ነው አምላክ ከሆን ደግሞ ፈራጅ እንጂ አማላጅ ሊሆን አይችልም።
ብዙ ጊዜ አንዳንድ የወንጌላውያን አማኞችም ሆነ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ወንድሞቻን ጭምር እነዚህ ጥያቄዎች ይነሳሉ፣ ታዲያ ይህ ብዥታ ከምን የመጣ ነው።
በመስቀል ለምታምኑ ወገኖች፣ ኢየሱስ አማላጅ ነው ካላችሁ ከማን ያማልዳል ለምትሉ አንድ ጥያቄ ኣለኝ። እርሱ አምላክ ከሆነ በመስቀል ለምን ሞተ? አምላክ ይሞታል እንዴ? ኢየሱስን ሲገርፉት ነበር አምላክን መግረፍ ይቻላል እንዴ? ይህንን ጥያቄ መመለስ ግድ ይላል።
በብዙዎች ዘንድ ይህ ብዥታ ሊፈጠር የቻለው ምክንያት ኢየሱስ ማን እንደሆነ ካለማወቅ ወይም ስለ ክርስቶስ ማንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ ነው።
ኢየሱስ ማነው?
ኢየሱስ ፍጹም ሰው እና ፍጹም አምላክ ነው።
ሰው የሆነው ኢየሱስ።
================
ኢየሱስ በሉቃ 2 እና ኢሳ 53 በተጻፈው መሰረት ። የሰው ልጅ በአዳም ምክንያት በሀጢያት መውደቁን ተከትሎ የሰውን ልጅ ለማዳን ስጋ ለብሷል። ይህ ስጋን የለበሰው ማንነቱ ፍጹም ሰው ይባላል። ፍጹም ሰው ሲባል የሚባላ፣ የሚጠጣ፣ እንደ ሰው ልጅ የሚደክም፣ የሚገረፍ፣ የሚሰቀል፣ ብትችል አባቴ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ብሎ የሚጸልይ ማለት ነው። ኢየሱስ በአዳም ምክንያት በሀጢያጥ የወደቀውን የሰው ልጅ በመስቀል ላይ የሀጢያትን ዋጋ የከፈለው በዚህ በለበሰው ሰው በሆነው ማንነቱ እንጂ በአምላክነቱ አይደለም።
752 views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ