Get Mystery Box with random crypto!

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

የቴሌግራም ቻናል አርማ referal_gibi — ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)
የቴሌግራም ቻናል አርማ referal_gibi — ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)
የሰርጥ አድራሻ: @referal_gibi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 692
የሰርጥ መግለጫ

🖋️✍️ ይህ ቻናል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ጉባኤ የተከፈተና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶች፣ ወቅታዊ መረጃዎች፣ ኪነጥበባዊ ፅሁፎች፣ ዝማሬዎች የሚለቀቁበት ነው።
ጽሑፎቹን ለጓደኞችዎ share በማድረግ የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ! ያሎትን ጥያቄ ሀሳብ አስተያየት በ @referal_gibi_gubae ያድርሱን። 🙏

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 10:55:33 ስንክሳር
~~~

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤  አሜን።

እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

++ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ ++

ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተከተሉበት ሰዓት እድሜአቸው በ3 ደረጃ የተከፈለ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ያሳያል::

እንደ ዮሐንስ_ወንጌላዊ ያሉት በ20ዎቹ ውስጥ:
ቅዱስ_ታዴዎስን የመሰሉት ደግሞ በ30ና በ40ዎቹ ውስጥ የነበሩ ሲሆን እነ ቅዱስ ዼጥሮስ ደግሞ በ50ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ:: ደቀ መዛሙርቱ ከወጣቶችም: ከጐልማሶችም ከአረጋውያንም የተዋቀሩ ነበሩ ማለት ነው::

+ቅዱስ ታዴዎስ በቀደመ ስሙ ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) ስምዖን እና ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል::

+ቅዱሱ ጌታችን ተከትሎ:
¤ከ12ቱ አንዱ ሆኖ በፈጣሪው ተመርጦ:
¤3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታ እግር ተምሮ:
¤በዕርገቱ ተባርኮ:
¤በበዓለ ሃምሳም 71 ልሳናትን ተቀብሎ:
¤ሐዋርያት ዕጣ ሲጣጣሉ የበኩሉን አሕጉረ ስብከት ተካፍሎ ዓለምን ዙሯል::

+ቅዱስ ታዴዎስ አንድ ቀን ከሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ጋር ወደ አንዲት ሃገር ይገባሉ:: ታዲያ ለቀናት ያለ ምግብ ወንጌልን ሲሰብኩ ቆይተው ነበርና ደጐቹ ሐዋርያት ራባቸው:: ወደ ከተማዋ ሳይገቡ አንድ ሽማግሌ ሲያርስ አይተው ሰላምታን ሰጡትና "እባክህ እርቦናልና አብላን" አሉት:: እርሱም ምንም ወገኑ ከአሕዛብ ቢሆነ አሳዝነውት በሬዎቹን ሳይፈታ እየሮጠ ሄደ::

+ያን ጊዜ ቅዱስ ታዴዎስ ሊቀ ሐዋርያትን "እርሱ እስኪመጣ ለምን አናርስም" አለው:: 2ቱ ተነስተው ታዴዎስ ሞፈር: ዼጥሮስ ደግሞ ስንዴውን ያዘ:: ቅዱሳኑ እየዘሩ ያረሱት ሰውየው ምግብ ይዞ እስኪመጣ አድጐ: አፍርቶ: እሸት ሆኖ ቆየው::

+ገበሬው የተደረገውን ተአምራት ባየ ጊዜ ደነገጠ:: ሊያመልካቸውም ወደደ:: እነርሱ ግን "እኛ የልዑል ባሮች ነን" ብለው በክርስቶስ ማመንን አስተማሩት:: "ልከተላችሁ" ቢላቸው "የለም! ከእሸቱ ይዘህ ወደ ከተማ ግባና ራት አዘጋጅልን:: እኛ እንመጣለን" አሉት::

+እርሱ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሕዛብ ነገሩን ተረዱ:: ተሠብሥበውም "እነዚህ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እሳትም ሰይፍም አይበግራቸውም" ብለው ወደ ከተማ እንዳይገቡ ከበሩ ላይ ራቁቷን የሆነች ዘማ አቆሙ::

+ቅዱስ ታዴዎስ ገና ከርቀት ስላያት ቀና ብሎ ቅዱስ_ሚካኤልን "እርዳን" አለው:: ሊቀ መላእክትም ድንገት ወርዶ ዘማዋን ሴት በጸጉሯ በዓየር ላይ ሰቀላት:: በከተማዋ ያሉ አሕዛብም ይህንና ሌሎች ተአምራትን አይተው ሁሉም በጌታችን አምነው ተጠመቁ:: ለሐዋርያቱም ሰገዱላቸው::

+አንድ ቀን ግን አንድ ጐረምሳ ባለ ጠጋ ቅዱስ ታዴዎስ "ሀብት ንብረታችሁን መጽውቱ" ሲል ሰምቶት ዘሎ የሐዋርያውን ጉሮሮ አንቆ ከሞት አድርሶት ነበር:: ያን ጊዜ "ጌታየ! ለካ ሀብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ያልክ ለዚህ ነው!" ብሏል:: ባለ ጠጋው "እንዴት ይሆናል?" ቢለው መርፌ አሠርቶ ግመሉን ከነ ባለቤቱ በሰው ሁሉ ፊት 3 ጊዜ አሳልፎታል::

+ያም ማለት ጌታችን እንዳለው "በሰው ዘንድ የማይቻለው በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል::" (ማር. 10:23) በዚህ ምክንያትም ያ ክፉ ባለ ጸጋ ወደ ልቡናው ተመልሶ ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ሥር ወደቀ:: ሐዋርያውም አለው "ሀብትህን ለነዳያን ስጥ:: ይህንንም በትር እንካና እየዞርክ ወንጌለ መንግስትን ስበክ::" ባለ ጸጋውም የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ በክብር ዐርፏል::

+ቅዱሳኑ ታዴዎስና ዼጥሮስ ግን በሃገሪቱ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው: ካህናትን ሹመው: ያቺን በዓየር ላይ የሰቀሏትን ዘማም የተባረከች መበለት አድርገው: በሌሎች አሕጉራት ወንጌልን ለማዳረስ ወጥተዋል::

+ቅዱስ ታዴዎስም እስከ እርጅናው ድረስ ለወንጌል ሲተጋ ኑሯል:: ጌታችንም በየጊዜው በአካል እየተገለጸ አጽናንቶታል:: ከብዙ የድካምና የመከራ ዘመናት በሁዋላም በዚህች ቀን ዐርፏል::

=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሱ ሐዋርያ በረከት ይክፈለን::

=>ሐምሌ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

=> " ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን 'ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል!' አላቸው:: ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁ:: ጌታ ኢየሱስም ደግሞ መልሶ 'ልጆች ሆይ! በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው! ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል' አላቸው:: +"+ (ማር. 10:23-28)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>


  @referal_gibi
              @referal_gibi
                        @referal_gibi
60 viewsBiruk Tadesse, 07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:36:17 +++ "ጠባቡ በር" +++

ብዙ ቅዱሳን እጅግ አጥብቀው ይፈልጓታል። እርሷንም ለማግኘት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ። እስከ ደም ጠብታ ደርሰው ይጋደላሉ። ባገኙዋትም ጊዜ ውስጣቸው በጸጥታ ይሞላል። ሕዋሳቶቻቸውም እንደ አመዳይ የነጹ እንደ ባዘቶም የጠሩ ይሆናሉ። ይህች ቅዱሳኑ ብዙ የሚደክሙላትና ደጅ የሚጠኗት ጸጋ ማን ትሆን? በአጭር ቃል "ዝምታ" ትሰኛለች።

አንዳንድ ሰው "ንግግር ዋጋ ያለው እና የሚጠቅም ነገር ሆኖ ሳለ፣ ታዲያ ለምን ዝምታ ጥሩ እና የበጎ ሥራዎች ሁሉ ቁንጮ ተደርጎ ይወሰዳል?" ሲል ሊጠይቅ ይችላል። ለዚህ መልሱ ቀላል ነው። የሰው ልጅ በጣም በቀላሉና ብዙ ጊዜ የሚበድልበት ሕዋሱ አንደበቱ ነው። የትም ሳይጓዝ፣ ምንም ሳያይ፣ በጣምም ሳይደክም ባለበት ብቻ ጥቂት ተንቀሳቅሶ ትልቅ ጥፋት ሊያደርስ የሚችል በሰው ውስጥ ያለ ትንሽ ነገር ቢኖር ምላስ ነው። ይህ ስለሆነም አንደበት "ዝምታ" የሚባል ንቁ ጠባቂ፣ ጠንካራ ልጓም ያስፈልገዋል።

ሳይንሱ ሰው የንግግር ችሎታውን ማዳበር እንዲችል ብዙ እንዲናገር ያበረታታል። ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ርቱዕ ተናጋሪ ለመሆን ዝምታ ዓይነተኛ መንገድ መሆኑን ታስተምራለች። ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ "በማይቋረጥ የዝምታ ልምምድ ውስጥ ካልተገባ በቀር መልካም ንግግር (ተናጋሪነት) አይገኝም" ይለናል። ቅዱስ ይሩማሲስም "የኋላ ንግግራችንን ማቅናት እንችል ዘንድ ከሁሉ በፊት ዝምታን እንማር" ሲል ይመክረናል። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙም ይህን ይለናል "ንግግራችን የዝምታ ያህል ጥቅም ያለው ይሆን ዘንድ እመኛለሁ... እንድናገር ግድ በተባልኩ ጊዜ የሚሰሙትን ወደ ጸጥታ በንግግር እና በዝምታም ጭምር እመራቸው ዘንድ ስለ "ዝምታ" ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር አላወራሁም። ይህም ስለ ዝምታ ያለኝ የእኔ እይታ፣ ስለ ንግግርም ያለኝ የእኔ ፍልስፍና ነው"። በሥጋዊ ጥበብ የዐዋቂነት መገለጫው መናገርና ጥሩ ተሟጋች መሆን ሊሆን ይችላል። በመንፈሳዊው ዓለም ያሉ ጠበብት ግን ብዙ ሲያውቁ ብዙ የማይናገሩ በመሆን ይታወቃሉ። በጣም ሲራቀቁ ደግሞ ዝምታና ተመስጦ መገለጫቸው ይሆናል።

አንደበትን መግዛት ማለት የሥነልቡና ባለሙያዎች "Suppression" እንደሚሉት ዓይነት ስሜትን መጨቆን ወይም ማፈን አይደለም። አንደበትን በመቆጣጠርና ስሜትን በማፈን መካከል በጣም ሰፊ ልዩነት አለ። በውስጥ የሚቀጣጠለውን ፍትወት ከፍርሐት የተነሣ በንግግር ወይም በድርጊት መግለጥ ሳይቻል ሲቀር ስሜትን ማመቅ (Suppression) ይባላል። አንደበትን መግዛት ግን ምላስን ለበጎ ንግግር መለየት፣ ማንጻት ነው። በአጭሩ ያኛው Suppression ይህኛው ደግሞ purification ነው።

ዝምታ ራሳችንን የምናይበት ጥሩ መጽሔት(መስታወት) ነው። አብዛኛውን ሰዓት በወሬ ተጠምዶ የሚውል ሰው ራሱን የሚመለከትበት እድል አይኖረውም። በሌሎች ኃጢአት ሲፈርድ፣ ሲተችና ሲያማ ስለሚውል የራሱን ስህተትና ውድቀት ለማወቅ ይቸገራል። ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲያወራ የሚውል ሰው የሚያሳዝነው ዝም አለማለቱ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅም ነገር የማይናገር መሆኑም ጭምር ነው። ነገር ግን ማር ይስሐቅ እንደሚለው "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ብዙ ማውራት ባቆመ ጊዜ ወደ ራሱ ይመለሳል። በእግዚአብሔርም ፊት ምግባሩን ማቅናት ይጀምራል"።

የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?!

ታዲያ ለብዙ ዘመናት ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚንኳኳውን ትጉህ እረኛ ድምጹን ሰምተን ለማስገባት ለምን ዝም አላልንም? ራሳችንንስ ከሁከት እና ከከንቱ መለፍለፍ ስለ ምን አልጠበቅንም? አንደበትን መግታት ቀላል አይደለማ! በአንድ ወቅት ቅዱስ እንጦንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነበር :- "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጠባቡ በር እንገባ ዘንድ አዝዞናል።አንደበትን ከኃጢአት መጠበቅ ካልሆነ በቀር ይህ ጠባብ በር ምንድር ነው? እንግዲያውስ ደካማ እና ክፉ የሆነውን ቃል እንዳያወጣ እየተጋደልን ለአንደበታችን ብርቱ ዘብ እናቁም"

በጠባቡ በር እንግባ!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

@referal_gibi
82 viewsMahi, edited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:27:25 ''ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ'' ማቴ 26:41
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የአደራ ልጆች እንዴት ከረማችሁ ነገ እንደሚታዎቀው ሐምሌ 1 ነው እና የሱባኤ ጸሎት ይጀምራል
ሁላችንም ጠዋት 11:30 ላይ ተቀሳቅስን በር ላይ እንገናኝ ለ ሁሉም share ይደረግ
92 viewsBayisa Girma, 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:52:45
ሰላም!
ለዚኽ ፕሮግራም ትኬት ምትፈልጉ ካላችኹ
በግቢያችን ስለሚገኝ በ 0931561673 በመደወል መግዛት ትችላላችኹ
103 viewsBayisa Girma, 07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:07:38 "የክርስቶስ ስለሆናችሁ በስሜ ፅዋ ውሃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እዉነት እላችኋለሁ" ማር 9:41
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ የበዓለ እግዚአብሔር ፀበል ፃድቅ ስላለ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም ተጠርተዋል

ቦታ፡ ደብረ ኢየሱስ ቤተክርስትያን
113 viewsMahi, edited  12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:52:14 ⒻⒾⓃⓄⓉⒺ ⓀⒾⒹⓊⓈⒶⓃ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

'' #ፍኖተ_ቅዱሳን''

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ከረማችኹ?
እዚኽ ሰዓት ያደረሰን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።

''ቅዱሳንን ማገልገል በብርቱ ፈልጉ።'' ሮሜ 12፥13
- -- --- ---- ---- ---
#ቅዱስ_ብሶይ_ክርስቶፈር
ብሶይ የቅብጥ ቃል ሲኾን ትርጉሙ ታላቅ፣ ኃያል፣ ተወዳጅ ማለት ነው። በላቲን ቋንቋ ቅዱስ ክርስቶፈር ይሉታል፤ ይኽም ክርስቶስን የተሸከመ ማለት ነው። ቅዱስ ብሶይ በ4ኛው መ/ክ/ዘ ከነበሩት ገዳማውያን አባቶች አንዱ ሲኾን ትክክለኛ ሰው ለመባል የበቃ መነኩሴ ነው። የተወለደው ከደጋግ ቤተሰብ በ፫፻፲፫ (313) ዓ/ም ነው። የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ብሶይ እናት ተገልጦ ከሌሎች ልጆቿ ኹሉ እርሱን ለቤቱ አገልጋይ እንዲኾን እግዚአብሔር እንደመረጠው ነገራት። እናቱም በዚህ የምሥራች መሠረት ቃሉን ጠብቃ ልጇን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ታዘጋጅ ጀመር።
- -- --- ---- ---- ---
ቅዱስ ብሶይ በወጣትነት ዕድሜው ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂርን ስላገኘው በወዳጅነት አብረው ይኖሩ ጀመር። ኹለቱም አባቶች ቅዱስ ፖምቦ ለተባለ አባት ደቀ መዛሙርት ነበሩ።
ቅዱስ ፖምቦ ሲያርፍ ኹለቱም እግዚአብሔር ጎዳናውን እንዲመራቸው ጸለዩ። የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ አኹን የቅዱስ ብሶይ ገዳም ወደሚገኝበት ቦታ መራቸው። ብሶይ ቀሪውን ሕይወቱን በምናኔ ያሳለፈው በዚህ ቦታ ነበር። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ብዙ ደቀ መዛሙርት አፈራ። ቅዱስ ብሶይ በሰው አፍቃሪነቱ በትሕትናውና በደግነቱ ከታላላቅ አባቶች ተወዳጅነትን አትርፏል።
- -- --- ---- ---- ---

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድሃ እንግዳ ተመስሎ ወደ ገዳሙ ሊለምን ሲመጣ በርኅሩኅነቱ የታወቀው ቅዱስ ብሶይ ወደ ውስጥ አስገብቶ እግሩን አጥቦና ምግብ አብልቶ አስተናግዶታል። እግሩን በሚያጥብበት ጊዜም የተቸነከረበትን ምልክት በማስተዋሉ ያስተናገደው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ተረዳ።
በሌላ ጊዜም የገዳሙ መነኮሳት ጌታ ይገለጥላቸው ዘንድ አባ ብሶይን ማለዱት። አባ ብሶይም በጸለየ ጊዜ ወደ ተራራ ቢወጡ ክርስቶስ እንደሚገለጥላቸው ራእይ አየ። በዚህ መሠረት በአካባቢው ያለ መነኩሴ ኹሉ ወደ ተራራው አመራ። ኹሉም ቀድሞ ተራራውን ወጥቶ ጌታን ለማየትና የዚህ በረከት የመጀመሪያው ሰው ለመኾን እንዳቅሙ ኹሉም ይፋጠን ጀመር። የበረታው የደከመውን ለማስተዋል ጊዜ አልነበረውም። አቅሙ የፈቀደለት ኹሉ እየተጋፋ ሽቅብ ወደ ተራራው ተመመ።
- -- --- ---- ---- ---

በዚኽ ጊዜ አንድ ደካማና ኮሳሳ ሰው ከተራራው ሥር ኾኖ ''እባካችኹ አትለፉኝ እኔም መድኃኒታችንን አየው ዘንድ እርዱኝ'' እያለ ይማፀን ነበር። ይኹን እንጂ ማን ሰምቶት! ደፍሮ መጠየቁስ ሳይገርማቸው ይቀራል? እነሱ እርሱን ተሸክመው ሲያዘግሙ ሌላው ቀድሟቸው ክርስቶስን ሊያይ? ይኸማ የማይታሰብ ነው።
ደጉ ብሶይ ግን ይኽን ደካማ ሰው አልፎ መኼድ አልቻለም። የፈጀውን ጊዜ ቢፈጅበት እጅግ በጣም ቢደክመውም እንኳን የተቸገረን መርዳት ግዴታው መኾኑን ከማንም በላይ ተረድቶታል። ስለዚህ ሰውየውን ብድግ አድርጎ ትከሻው ላይ ቁጭ አደረገው። አቤት ክብደቱ አይጣል ነው! በቅዱስ ብሶይ ግዙፍነት እንደዚህ የከበደ ሌሎች ቢሸከሙትማ እንዴት ሊኾኑ ነበር? ቅዱስ ብሶይ ግን ለክብደቱ ምንም ቦታ ሳይሰጥ እንደ ምንም ተራራውን መውጣት ጀመረ።
- -- --- ---- ---- ---
ጉዞውን እንዳጋመሰ የሽማግሌው ክብደት እየቀነሰለት መጣ። የተራራው ሲሶ ያህል ሲቀረው ደግሞ ይበልጥ እየቀለለው ነው። ተራራው ጫፍ ሲደርስ ጭራሽ እስከ መሸከሙም ስላልተሰማው ማንን እንደተሸከመ ተረዳ። እንደ ምስኪን ድሃ አትለፉኝ እያለ ሲለምን የነበረው ለካ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር (ክርስቶፈር መባሉ ለዚኽ ነው)። ቅዱስ ብሶይም የድካሙን ዋጋ አላጣም። ▣ለለመነህ ኹሉ ስጥ ያሉት አባቶቻችን ለዚኽ ነው።▣ ኹሉ ቀደም ብሎ የተመመ ሕዝብ ያላገኘውን በረከት በትሕትናው አገኘ።
- -- --- ---- ---- ---
ቅዱስ ብሶይ በተጋድሎውና በትሕትናው ብዛት እስከ ዳግም ምጽአት ድረስ አካሉ ትኩስ ሥጋ ኾኖ እንደሚቆይና በስሙ የተማፀኑ ኹሉ እንደሚባረኩ ክርስቶስ ቃል ገባለት።
ቅዱስ ብሶይ ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅርና አክብሮት የተነሣ በሕይወት ሳለ ጸሎቱን ማቋረጥ አይፈልግም ነበር።የቅዱስ ብሶይ ዕለተ ዕረፍት በ፬፻፲፯(417) ዓ/ም ነው።
- -- --- ---- ---- ---
እግዚአብሔር አምላካችን ከቅዱስ ብሶይ ክርስቶፈር በረከቱን፤ትሕትናውን፣ ደግነቱን ያድለን፤ በጸሎቱም ይማረን።አሜን

@referal_gibi
28/10/2014
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ⒻⒾⓃⓄⓉⒺ ⓀⒾⒹⓊⓈⒶⓃ
125 viewsደስ ይልህ ዘንድ አልቅስ, 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:35:48

'ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን - ከፍ ከፍም እናደርግሻለን እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የህይወት መጠጥን ወልደሽልናልና!' ብለን ከአባቶቻችን ጋር እንቀድስ ዘንድ ፣ ከጥበብ ማዕድም በልተን እንድንቀደስ ፤ የተራብነውን የሕይወት እንጀራ የተጠማነውን እውነተኛ መጠጥ እርሱ ጌታችንን በጉብዝናችን ወራት ለማሰብ - ወደ ልጅነታችን በመመለስ በፊቱ እንቅረብ! በኃጢአት የታመምን ሁላችን ከመድኃኒታችን እንሰለፍ - አብረን እንታከም። ሥጋውን በሚበላ ደሙን በሚጠጣ እርሱ እንዲኖር የተናገረው ቃል የታመነ ነውና።

ለቅዱስ ቁርባን የዝግጅት ትምህርት

ከሐምሌ 1 - ሐምሌ 30
በቴሌግራም ቮይስ ቻት

ለመመዝገብ

• ሙሉ ስም
• የክርስትና ስም
• ጾታ እና ዕድሜ
• የንስሓ አባት መረጃ
• አጥቢያ ቤተክርስቲያን
• ስልክ ቁጥር
• ትምህርቱን ለመከታተል የሚመርጡት ሚዲያ

በቴሌግራም @EOrthodoxbot ይላኩልን።
94 viewsMahi, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 10:39:44
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ወደ ገነትም ነጥቀው ወሰዱት" 2ኛ ቆሮ12፥14


አምላከ ካህን ጥዑመ ልሳን ፈልፈለ ማኅሌት ቅዱስ ያሬድን ለማሰብ ታላቅ መንፈሳዊ መርሐግብር ተዘጋጀ።

ትምህርት ፣ ኪነ-ጥበብ ፣ወረብ እንዲኹም በግእዝ፣ዕዝል እና አራራይ የተለያዩ ዝማሬዎች ተካተው ኑ በአርያም ዜማ እግዚአብሔርን እናመስግን ስንል መንፈሳዊ ግብዣችንን በፍቅር ቃል እናቀርባለን፡፡
በምድራዊት ኢየሩሳሌም ሰማያዊውን አኮቴት !

ቀን ፡ 25/10/14 ቅዳሜ
ሰአት ፡ 11፡30 ጀምሮ
ቦታ ፡ ደ/ኢየሱስ ቤ/ክርስቲያን አዳራሽ
229 viewsBayisa Girma, 07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 20:42:13
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከላይ በምስሉ ላይ የምንመለከተው የእናንተ የማያቋርጥ ትጋት ፩ዱ ፍሬን ነው ፤ ጸንታችሁ ብዙ ደክማችሁ በዕለቱ በአንድም በሌላ ጉዳይ መገኘት ያልቻላችሁ የስራችሁን ውጤት አይታችሁ ሐሴት ታደርጉ ዘንድ ተለጠፈ እንጅ ዓለም ላይ እንደምንመለከተው ይህን አደረግን ብለን ቁጠሩልኝ አለመሆኑን እያሳወቅን**
ዳቦ አወጣሻለሁ እንበላት !የኛን ድርሻ ለማን እንተዋለን!

በቀሩን 6 ቀናቶች የተለመደውን ብርታታችሁን ታጸኑ ዘንድ አሁንም ለመልካም ነገር ትፋጠኑ ዘንድ በአምላከ ሰማይ ወምድር ስም እየጠየቅን ስላደረጋችሁት ቅን ተግባር ግን የስጦታ ባለቤት የድካማችሁን ይስጣችሁ እንላለን !
151 viewsደስ ይልህ ዘንድ አልቅስ, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 18:42:21 ⒻⒾⓃⓄⓉⒺ ⓀⒾⒹⓊⓈⒶⓃ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

'' #ፍኖተ_ቅዱሳን''

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት አላችኹ?
እግዚአብሔር ይመስገን።
እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም፣ ቅዱሳን ሐዋርያት እንዲኹም ኹሉም ቅዱሳን የተመሰገኑ ይኹኑ።

#በእንተ_እግዝእትነ_ማርያም

ዛሬ ማለትም ሰኔ 21 ለአዳም ዘር ኹሉ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች ንግሥተ ሰማይ ወምድር ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓሏ ነው።
1ኛ) በዓለም ኹሉ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል ነው፡፡

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ህንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን የታነጸችው በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኀኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፡፡

እመቤታችን ካረገች በ4ኛ ዓመት ጳውሎስና ባርናባስ በፊሊጲስዮስ ገብተው አስተምረው ሕዝቡን አሳምነው ካጠመቁ በኋላ ‹‹እንግዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ›› አሏቸው፡፡ አሕዛብ የነበሩትና አምነው የተጠመቁትም ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን መካነ ጸሎት ስጡን›› አሏቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያትም ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስም መልእክት ላኩባቸው፡፡ ጴጥሮስና ዮሐንስም ‹‹ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባምና ጸልዩ እኛም እንጸልያለን›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ሁሉም ሱባኤ ይዘው በጸሎት ተጉ፡፡ ጸሎትና ሱባኤያቸውን ከጨረሱ በኋላ ጌታችን በሞት ያረፉትን አስነሥቶ በሕይወት ያሉትንም ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ጌታችን በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን?›› ብሎ ጠየቀ፡፡

ጌታችንም ‹‹በእናቴ ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አለው፡፡ ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ›› ብሏቸው ዐረገ፡፡

@referal_gibi
ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴን ሦስትነት ወደ አንድ ሆነው አንድ ሕንፃ መታጹ የሥላሴን አንድነት ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን መታነጽ ለኛ ለክርስቲያኖች እጅግ ታላቅ በዓልና ደስታ ነው፡፡ ስለዚች ቤተ ክርስቲያን አባቶች ደማቸውን አፍሰውላታል፣ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተውላታል፣ አጥንታቸውን ከስክሰውላታል፣ ቆዳቸው ተገፏል፣ በድንጋይ ተወግረዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዋ ውኃ መሠረቷ ደም ነው፡፡ የማትታደስ ነገር ግን ከኃጢአት ከበደል የሚታደሱባት ርትዕት ናት፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ‹‹የክርስቶስ አካሉና ሙላቱ ናት፡፡›› ኤፌ 1፡13፣ ቆላይ 1፡18፣14፡፡ እናም የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መጣስና ትምህርቷን መቆነጻጸል የክርስቶስን አካል ማድማት ነው፡፡ ዳግመኛም በማግሥቱ ሰኔ 21 ቀን ጌታችን ድንግል እናቱን እመቤታችንንና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ወረደ፡፡ እመቤታችንን መንበር፣ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቁርቧቸዋልና ፍጹም ደስታም ሆነ፡፡ ዳግመኛም ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞታል፡፡ በዚህም ጊዜ ሰማያውያን መላእክት ምድራውያን ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡
ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታችን እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው የእነ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ፣ የአይሁድ ምኩራብ፣ የአይሁድ ሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ሥርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፡፡ እንኪያስ ‹‹ሐዋርያት የት ነበር ሕዝቡን የሚያጠምቁትና የሚያቆርቡት?›› ከተባለ እንደ ማርቆስ እናት ቤታቸው ለሐዋርያት በሰጡ ‹‹በየአማኞቹ ቤት›› ይከናወን ነበር፡፡

ሰኔ 20 ቀን ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ) ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡

ሐዋርያዊቷ ቅድስት ቤተክርስቲያን የጽሑፍ እና የቃል (የትውፊት) አስረጂን ለእምነቷ መመሪያ በመጠቀም ልጆቿን ትጠብቃለች። ለዚህም የተወደደ ቅዱስ ጳውሎስ መመሪያ ሰጥቶናል ፦
“እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።” 【፪ኛ ተሰ ፪፥፲፭ 】

የእመቤታችን ቃልኪዳን ለፍጥረቱ የመዳን ምክንያት እንዲሆን ከአምላክ የተሠጡ መሆናቸውን ቤተክርስቲያን በተቀደሰው ትውፊቷ ትመሰክራለች።

@referal_gibi
2ኛ) ደግሞ "ሰኔ 21 ቀን በኹለት ወገን ድንግል የሆነች እመቤታችን ማርያም የልጇ መቃብር ወዳለበት ወደ ጎልጎታ ተራራ የሔደችበትና በዚያም የጸለየችበት (ቃልኪዳንን የተቀበለችበት) መላእክትም መጥተው ኹለተኛ ወደ ሰማይ ያሳረጉበት ቀን ነው።"
"መታሰቢያዋን ለሚያደርግ ፣ በስሟ ቤተክርስቲያን ለሚሠራ ፣ በስሟ የታረዘ የሚያለብስ የተራበ የሚያበላ የተጠማ የሚያጠጣ ያዘነ የሚያረጋጋ የተከዘ ደስ የሚያሰኝ ፣ ምስጋናዋን የፃፈውን ፣ ልጁን በስሟ የጠራ ፣ በክብረ በዓሏ ቀን ምስጋና ያመሰገነውን እንዲምርላት ወደሲኦል ከመውረድ ነፃ የወጣ እንዲሆን ተማጽና የለመነችውን ሁሉ ሊያደርግላት የፈቀደችውን ሁሉ ሊፈጽምላት'' ቃልኪዳን ገብቶላታል።

እኛም ለእናቱ የተገለጠውን ቃልኪዳን ሁሉ በማሰብ "ምሕረት የአምላክ፥ ኪዳን የእማምላክ" ነውና ከቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ጋር እንዲህ እያልን ልጇን ደጅ እንጠናዋለን፦

☞ ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፣ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርይያችን መመኪያ ናት፣ አንተ መታሰቢያሽን ያደረገ፣ ስምሽንም የጠራ የዘለዓለም ደኅንነትን ይድናል ብለሃታልና »

የዛሬውን በዓል በሚመለከት ተወዳጁን የጸሎት መጽሐፍ የሰኔ ጎልጎታን የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ከ፯ቱ ዲያቆናት ሦስተኛው ቅዱስ አብሮኮሮስ (ጵሮኮሮስ) ጽፎታል።
ምንጭ፦ ከቴሌግራም መንደር የተቀነባበረ

የእመቤታችንን ጣዕመ ፍቅሯን በልባችን፣ ጣዕመ ስሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። አሜን!

@referal_gibi
21/10/2014 ዓ.ም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ⒻⒾⓃⓄⓉⒺ ⓀⒾⒹⓊⓈⒶⓃ
157 viewsMahi, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ