Get Mystery Box with random crypto!

#የቅዱስ_መርቆርዮስ_ታሪክና_ስዕሉ_ባጭሩ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን | ራዚኤል ዘኢትዮጵያ

#የቅዱስ_መርቆርዮስ_ታሪክና_ስዕሉ_ባጭሩ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ አገሩ ሮም አስሌጥስ ነው። አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈጸመ ሲያውቅ አባቱ ከነቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል። የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ “ፕሉፖዴር” ነው፤ ገብረ
እግዚአብሔር ማለት ነው። በጥበብ በፈሪሀ እግዚአብሔር አድጎ አባቱ
ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ።
ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል። መምለኬ ጣዖት ነበር።

በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አጽናንቶት ዘመቱ።

መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት። ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን “አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ /እኔ ጌታዬን አልክድም/ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ።

መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፤ #ፈረሱ_ለሰባት_ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን:: ዘኁልቁ 22፡28

በዚያን ዘመን ቅዱስ ባስሊዮስ ንጉሱን ይገስጸው ነበር ። ከዛ ባስሊዮስን አሰረው። ጳጳሱ በታሰሩበት እስር ቤት የቅዱስ መርቆርዮስ ስእል ነበር። ባስሊዪስም ስዕሉ ፊት ይፀልይ ነበር። ከዛም የመርቆርዮስ ስዕል ታጣ። ያ ስዕል ወደ ንጉሱ ኡልያኖስ ቤት ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለው። በስዕሉ ላይ ያለው ጦር ጫፍ ላይ ደም ይንጠባጠብ ነበር።

የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕልም በአዎንታ አንገቱን ዘንበል አድርጎ ምስክርነት ሰጥቷል። ይህም ሊታወቅ ዛሬ በሀገራችን #ኢትዮጵያ_በምድረ_ተጉለት
በስሙ ከታነጸ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ደነነ ስዕሉ እያሉ ሲዘምሩ ጎንበስ
ቀና ሲሉ እንደሚታይ ይነገራል።
የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤቱ፣ በረከቱ፣ አማላጅነቱና ቃል ኪዳኑ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።

join & share
@razielethiopia
@razielethiopia