Get Mystery Box with random crypto!

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ የናዚ ተጽእኖ በከፋባቸው ዓመታት ጃኔዝ (Janez Rus) የ | MEDITATION🎯

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ

የናዚ ተጽእኖ በከፋባቸው ዓመታት ጃኔዝ (Janez Rus) የተባለ አንድ ሰው በናዚ
ዘመን በነበረው አቋም ምክንያት በቀልን በመፍራት ለ32 ዓመታት ከአንድ
ስፍራ ሳይወጣ እንደተደበቀ ይነገራል፡፡ ይህ ወጣት በፍርሃት ከመደበቁ በፊት
የጫማ ስራ ባለሞያ ነበር፡፡ ፍርሃቱ ከነገሰበት በኋላ ግን የቀረውን የወጣትነቱን ዘመን በመደበቅ ነበር ያስበላው፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በJune, 1945 ይህ ወጣት በእህቱ እርሻ ውስጥ በሚገኝ ቤት (Farmhouse) ውስጥ ለ32 ዓመታት ተደብቆ ሲኖር የእናቱን ቀብር እንኳን ለመካፈል አልወጣም፡፡ ከዚህ ስፍራ ከወጣ በኋላ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ከተደበኩበት ቦታ ሆኜ ውጪ የሚገኙ ሰዎች ሲደሰቱና ሲስቁ ስሰማ ምርር ብዬ አለቅስ ነበር”፡፡
ይህ ወጣት በእነዚያ አመታት ውስጥ ያገኘውን ነገር እየበላ ከላይ ሆኖ
ወደታች ያለውን መንደር ከማየት ውጪ ምንም ነገር አላደረገም፡፡

ፍርሃት እንዲህ ይልሃል …

◆ አትመልከት - አንድ ነገር እንዳታይ!
◆ አታድምጥ - አንድን ነገር እንዳትሰማ!
◆ አታስብ - አንድ ድምዳሜ ላይ እንዳትደረስ!
◆ አትወስን - ስህተት እንዳትሰራ!
◆ አትራመድ - እንዳትወድቅ!
◆ አትኑር - እንዳትሞት!
◆ አትማር - ፈተና እንዳትወድቅ!
◆ አትውደድ - እንዳትጎዳ!

በሕይወትህ ልታነግሱ የምትችሉት ስሜት አንዱን ብቻ ነው - የፍርሃትን ወይም የመኖር ድፍረትን፡፡ አንዱ እንዲነግስ ስትፈቅድለት ለሌላኛው የባርነት ትእዛዝን እያስተላለፍክ ነው፡፡ ፍርሃት ሲነግስ የመኖር ጣእም ይጠፋል፡፡

#ተነሱና_ፈጣሪን_ተማምናችሁ_ቀና_ብላች_ኑሩ!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
@RASN_MEHON