Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዘር ፍጅት ወንጀልን በገንዘብ እየደገፈ ነው። 'ፕራይም' የተባለው ሚዲያ | ሽፈራው የሶማው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዘር ፍጅት ወንጀልን በገንዘብ እየደገፈ ነው።

"ፕራይም" የተባለው ሚዲያ በፀረ አማራ ቅስቀሳ የተሰማራ ሚዲያ ነው። አማራ ክልል የሚኖርን ህዝብ እርስ በእርስ ለማጋጨት ከሚነዛው ሀሰት በተጨማሪ ሰሞኑን ጉራጌ ዞን የተፈፀመን ግጭት ጠንሳሽ አማራ አስመስሎ አቅርቧል። ዋና ስራው  ፀረ አማራ ቅስቀሳ ነው። የአማራ ህዝብ በሌላው ላይ በደል የፈፀመ አስመስሎ ሲቀሰቅስ ይውላል።

ይህን ሚዲያ በገንዘብ እየደገፈ፣ የዘር ፍጅትን እንዲፈፀም የሚደረግን ቅስቀሳ እያገዘ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ነው። አንድ ተቋም "ስፖርሰር" ከማድረጉ በፊት ሚዲያው ምን እንደሚሰራ ማየትና መገምገም ይጠበቅታል። ነገር ግን በዚህ ሚዲያ ገዥዎቹ የሚፈልጉት ፀረ አማራ ቅስቀሳ ስለሚደረግ አላማውን በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ እየደገፉት ይገኛሉ። ይህ ሚዲያ የሚሰራውን ለተመለከተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአቋም አማራ ጠላቴ ነው ብሎ ፀረ አማራ ቅስቀሳና የዘር ፍጅትን እየደገፈ እንደሆነ አያጣውም።