Get Mystery Box with random crypto!

'እኛ ተከሳሾች ከዚህ ሥርአት ፍትህን አንጠብቅም ህዝባችን እንዲገነዘበው የምንፈልገው እና በድጋሚ | ሽፈራው የሶማው

"እኛ ተከሳሾች ከዚህ ሥርአት ፍትህን አንጠብቅም ህዝባችን እንዲገነዘበው የምንፈልገው እና በድጋሚ የምናረጋግጠው አማራነትና ፋኖነት እንደወንጀል ተቆጥሮ በሃሠት ተከሠናል ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ በዶክመንተሪ ተፈርዶብናል ወደፊት እውነቱን ህዝብና ታሪክ ይፈርዳል።"

በአዲስ አበባ በእስር ላይ የሚገኙ የአማራ ልጆች

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
   ሚያዚያ 28/2015 ዓ/ም
      አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

        ዳኛው ማነው?

እኛ የአማራ ልጆች በመንግስት የሀሠት ክስ ተከሠን በእስር እንገኛለን።

አብዛኞቹ ወጣቶች በህግ ጥላ ስር ሲውሉ በፖሊሶች ተደብድበው በጨለማ ቤት ቆይተው ፍ/ቤት ይቀርባሉ በመንግስት የሀሠት ዶክመንተሪ ተዘጋጅቶብን በእስር  እንድንቆይ በብልፅግና ፖለቲከኞች ተፈርዶብናል።

በዚህም ምክንያት ለምን ፍ/ቤት ታመላልሱናላችሁ ብለን ጠይቀናል ብዙዎቹ በሀሠት የተከሠሡ ምሁራን እና ወጣቶች የፀጥታ አስከባሪዎች ሀገርን ከመፍረስ ህዝብን ከመዋረድ ለመታደግ የመንግስትና የህዝብን ጥሪ ተቀብለው በግንባር ተዋግተው በደረታቸው የጥይት እርሳስ በግንባራቸው የቦንብ ፍንጣሪ ይዘው ነው የተከሠሱት።

ወጣቶቹ ህክምና ሲገባቸው የውንጀላ ዶክመንተሪ ሠለባ ሆነዋል።

በእስር ላይ እያለን በአማራ ክልል መንግስት በፈጠረው ረብሻ ወንጀለኞች ተብለናል።

በኛ እምነት አማራነትን ለማሠርና ለመወንጀል የአማራ መሪዎችን መግደል እና ህዝቡን ማተራመስ አያስፈልግም።

መንግስት አማራነትን ፋኖነትን የሚያጠለሽ ተጨማሪ ዶክመንተሪ እንደሚያዘጋጅ እምነታችን ነው።

ስለሆነም በዚህ የቆርጦ ቀጥል ዶክመንተሪ ህዝባችን እንዳይደናገጥ እንጠይቃለን የተዘጋጁና የሚዘጋጁ ድክመንተሪዎች በፍትህ ሥርአቱና በዳኝነት ስራው ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠርና ህዝብን ለማደናገር እንደሆነ እንድትገነዘቡ እንጠይቃለን።

ሀገራችን ባለፉት አመታት በሀሠት ዶክመንተሪ ፍትህን በአደባባይ ሠቅላለች እነዛ ተከሳሾች ዛሬ የት ናቸው?

እኛ ተከሳሾች ከዚህ ሥርአት ፍትህን አንጠብቅም ህዝባችን እንዲገነዘበው የምንፈልገው እና በድጋሚ የምናረጋግጠው አማራነትና ፋኖነት እንደወንጀል ተቆጥሮ በሃሠት ተከሠናል ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ በዶክመንተሪ ተፈርዶብናል ወደፊት እውነቱን ህዝብና ታሪክ ይፈርዳል።

መንግስት የድሮን ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ በማዋል በሀገራችን የክፍለ ዘመኑን ታላቅ የእርስ በርስ ጦርነት አድርጓል።

ውጤቱም አውዳሚ ነበር እንዲሁም መንግስት ከኦነግ ሸኔ ጋር የከፈተውን የተራዘመ ጦርነት ለመፍታት እየጣረ እንደሆነ እየሠማን ነው። 

ሆኖም በፋኖነት እና በአማራነት ላይ አዲስ ጦርነት ማወጅ አውዳሚ እና ጥፋት እንጂ ውጤት እንደማይኖረው እናሳስባለን።

መንግስት ችግሩን በሠላም መፍታት ካልቻለ ህዝብ ራሱን ከመጥፋት የማዳን የሞራል ግዴታ አለበት።

     ሠላም ለሀገራችን ይሁን!
      የደም ዘመን ይብቃን!!

  በእስር ላይ የምንገኝ የአማራ ልጆች።

   ሚያዚያ 24-08-2015 ዓ.ም