Get Mystery Box with random crypto!

ጌጅ ዩኒቨርሲት ኮሌጅ አንድ ሺህ መጻህፍት ለአብርሆት ቤተመጻህፍት አበረከተ ************** | Queen's College

ጌጅ ዩኒቨርሲት ኮሌጅ አንድ ሺህ መጻህፍት ለአብርሆት ቤተመጻህፍት አበረከተ
**************
(ኢ ፕ ድ)
ጌጅ ዩኒቨርሲት ኮሌጅ አንድ ሺህ መጻህፍት ለአብርሆት ቤተመጻህፍት እንዲሰጥለት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አሰረከበ።
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ከኩዊንስና ግሬት ኮሌጅ ጋር በመሆን በድርጅቱ ስም ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ለኢፕድ አስረክበዋል፡፡
ጌጅ ኮሌጅ 400 መጻህፍት፣ ኩዊንስ ኮሌጅ 300 መጻህፍት፣ ግሬት ኮሌጅ 300 አበርክተዋል፡፡
ጌጅ ዩንቨርሲት ኮሌጁ ሰርቨስና ትሬድንግ PLC ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሞገስ ግርማ በርክብ ወክት እንደገለጹት፣ ለአብርሆት ቤት መጻህፍት የሚሆን አንድ ሽህ መጻህፍት ማበርከታቸዉን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ መጻህፍቱ መማሪያ መጻህፍት ፣የኮሚፕዩተር፣ የማኔጅንት፣ የታሪክ፣ ስነጽሁፍ፣ሙዚቃ ፣ ልበ ወለድና ለህጻናት የሚሆኑ 200 መጻህፍ እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርስትዉ እንደ ሀገር የራሱን አሻራ ለማስቀመጥ በአብርሆት ቤተመጻፍት አንድ ኮርነር እንዲሰጠዉ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የህትመት አስተዳደርና ኮሮፖሬት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድም ተክሉ በበኩላቸው፣ ትዉልድ ለመቅረጽ ሁሉም በጋራ በመስራት አለበት። አብርሆት ቤተመጻህፍት የሀገርን ገጽታ በመቀየር ለአፍርካ የሚተርፍ የልቀት ማዕክል ለማድረግ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መጻህፍት እያሰባሰበ ይገኛል ብለዋል።
ለተደረገዉ አበርክቶ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በገመቹ ከድር