Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከEBS ጋር ባደረጉት ቆይታ በ2014 ዓ.ም የ1 | QesemAcademy

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከEBS ጋር ባደረጉት ቆይታ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ የመንግስትን ሦሥት ውሳኔዎች አብራርተዋል።

1. 50 በመቶ ባያመጡም መቶ ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች በመንግስት እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለአንድ ሴሚስተር የማብቂያ ትምህርት ተከታትለው በቀጣይ ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

2. በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት እንዲገቡ ይደረጋል።

3. በዚህ ዓመት መጨረሻ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በድጋሜ በግል መውሰድ ይችላሉ።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስተዳደር "ተማሪዎቻችን እና ትምህርት ቤቶቻችን ምን እንደሚመስሉ" በደንብ ያሳየ እንደነበር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

"ውጤቱ ያስደነግጣል። ትምህርት ሚኒስቴር ያለን የሥራ ኃላፊዎች ውጤቱን ለመቀበል ቀናት ወስዶብናል" ሲሉም ተደምጠዋል።

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በመንግስት በሚወሰን ነጥብ "ዕጩ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ" ሆነው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡበት ዕድል እንዳለ መገለጹ ይታወቃል።

ከHigh school  እስከ Campus አብረናችሁ ነን !
SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @QesemAcademy
JOIN: @QesemAcademy
╚════════════╝