ጥር 01 /2015 ዓ.ም ህይወት በየ Instagram ፎቶ እንደምናያው ሁሌም ድሎት እና ምቾት የሞላባት አደለችም! አንዳንዴ እኔ አሁን እየኖርኩ ነው ታሰኛለች? ሰዎች መንገድ ላይ አጊንተው ሃይ ፣ ሰላም ነው ? ሲሉን ደህና ነኝ እንላለን እውነታው ግን ውስጣችን ህመም መያዛችን ነው! ጠዋት መነሳት -በድብርት ሙድ ውስጥ መዋል- ማታ መተኛት ፣ ጠዋት መነሳት - በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውሰጥ መዋተት- ማታ .... አሰልቺ የሆነ ደባሪ ኑሮ ፣ያማል! አዎ ይህ ሁላችንም ጋር ያለ እውነታ ነው ፣ ማድረግ የማንፈልጋቸው ነገሮች ካረግን በኋላ እንፀፀታለን ፣ ድጋሜ አላረገውም ብሎ ማልቀስ ችግሩ ግን መልሰን ያንን ስህተት መስራታችን ነው! ታጥቦ - ጭቃ መሆን ፣ በጣም ያማል! አንዳንዴ በራሴ ማድረግ የከበዱኝን ነገሮች ፣ ለእግዚአብሔር መተው ፣ እንደ ሽንፈት ይሆንብኛል! ህይወት ሲሰለቸኝ ፣ ኑሮ ሲያደክመኝ ፣ መከራው ሲበዛ ፣ ጌታዬ ሆይ ፣ አግዘኝ ብሎ ማለት እንኳ ስንፍና መስሎ ይሰማኛል! ወደ ቤቱ መሄድ ተውኩ ፣ አንድ ወር ሆኖኛል ። ችግሮቼን በራሴ ብቻ ነው መፍታት የምፈልገው! መፅሀፍ አንብቦ ወይ ሰው ጠይቆ ፣ ለችግሩ መፍትሄ ማግኘት! አይገርምም ይሄን ሁሉ ሳረግ እንኳን አምላኬ የረዳኝ አይመስለኝም ፣ወዴት እና እንዴት እንደምሄድ ፣ ምን ማረግ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ፣ ሁሉንም በራሴ ለማስተካከል ስሞክር መሸከም ከምችለው በላይ ጫናው ከበደኝ! ደከመኝ! ሰው ለካ ምን አይነት ትዕቢተኛ ነው ፣ ወደ ሳንባው የሚሸጉጠውን ትንፋሽ አስቦ ፤ ከፍሎበት ይመሰል ፣ ይሄን ያክል መመፃደቅ አሁን ምን ይሉታል?ለነገሩ ለካ ሁሉም ሰው አደለም! ዘግይቶም ቢሆን ትንሽ ትንሽ እየገባኝ ነው ፣ ያለ እግዚአብሔር ፍቃድ አሁን ላይ መድረስ እንዴት ይቻለኝ ነበር! ያለእሱ ከንቱ ነኝ ፣ .... እልና ካዲያ ለምን እሱ እያለ ይሄ ሁሉ ፈተና በዛብኝ ? ብዬ ጠይቃለሁ! መልሱ ሩቅ አደለም ፣ ሊያስተምረኝ ነው ፣ ካዲያ እስከመች ነው ይህ ሁሉ ሲቃይ የሚቀጥለው?፣ እስክማር! እስኪገባኝ! በስቃይ ውስጥ ያለውን መራራ እውነት እስቀምሰው። https://t.me/Chalu_A 3.0K viewsMr.x, 10:44