Get Mystery Box with random crypto!

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በህክም | Paradise valley university college

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ ባለሙያዎች በሚያዝያ 2014 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የፈተናው ምዝገባ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም የሚካሄድ ስለሆነ ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃ በማያያዝ online እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1) ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቃችሁ ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ህጋዊነትና ትክክለኛነት በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (የቀድሞው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጄንሲ-HERQA) በኩል ማረጋገጥ (Authenticate ማስደረግ) እና ስማችሁ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ ተቋማችን እንዲተላለፍ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡

2) ከዚህ ቀደም የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን Authenticate ያስደረጋችሁ እና ስማችሁ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወደ ተቋማችን የተላለፈላችሁ ተመዛኞች ድጋሚ Authenticate ማስደረግ አይጠበቅባችሁም፡፡

3) ምዘናው ለሁሉም ተመዛኞች online የሚካሄድ ሲሆን online ያልተመዘገበ ተመዛኝ ለፈተና መቀመጥ የማይችል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

4) የonline ምዝገባችሁን አጠናቃችሁ Submit ካላችሁ ከ 72 ሰዓት (3 ቀናት) በኋላ ወደ ሲስተሙ በመመለስ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) መዝግባችሁ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

Tg- t.me/healthinovation
group t.me/HIVN19 ይከታተሉን