Get Mystery Box with random crypto!

ራስን መግለጽ መቻል እስቲ ራሳችሁን ግለጹት? ተብለው ሲጠየቁ ብዙ ሰዎች “እንዴት እኔ ራሴን እገ | ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

ራስን መግለጽ መቻል

እስቲ ራሳችሁን ግለጹት? ተብለው ሲጠየቁ ብዙ ሰዎች “እንዴት እኔ ራሴን እገልጻለሁ ሌሎች ሰዎች ይግለጹኝ እንጂ” ይላሉ፡፡ ይህ ትክክለኛ መልስ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኛ በእኛ ውስጥ ነው የምንኖረው እንጂ በሌሎች ሰዎች ውስጥ አይደለም፡፡ ሲቀጥል ሌሎች ሰዎች የራሳቸው ጉዳይና ህይወት ያለባቸው ናቸው ስለዚህ እኔን በደንብ መግልጽ አይችሉም፡፡

ሰዎች ስለኛ የሚናገሩት ያሳየናቸውን ባህሪ ብቻ ነው፡፡ ይህን ሊያዉቁ የሚችሉት ደግሞ ለጅም ግዜ አብረናቸው ካሳለፍን ነው፡፡ አንዳንድ ባህሪያቶች ደግሞ የተለዩ ሁኔታዎችን ጠብቀው ነው የሚገለጹት ስለዚህ ሰዎች ስለኔ ይናገሩ የሚለው የሚያዋጣ አይደለም፡፡
ስለራስ መናገርም በኩራት መንፈስ ራስን መካብ አይደለም፡፡ እኛ ምን አይነት ሰው እንደሆንን ስለራሳችን የምናውቀውን መንገር ማለት ነው እንጂ ራስን መስቀል ማለት አይደለም፡፡

ለምሳሌ አንድ ሰው እኔ ስሜቴ ቶሎ ቶሎ የምቀያየር አይነት ሰው ነኝ ብሎ ራሱን ቢገልጽ ተገቢነት አለው፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለውን ማንነቱን ነው የነገረን፡፡ ስለዚህ ራስን መግለጽ አሁን ላይ ያለንን ባህሪና ማንነት መንገር ማሳየት መቻል ነው፡፡

በእርግጥ ከራሱ ጋር ያልተገናኘና ስለራሱ ማንነት አስቦ ለማያውቅ ሰው ይህ ጥያቄ ከባድ ነው፡፡ የዘወትር ትኩረቱ በሰዎችና በሁኔታዎች ላይ ብቻ ለሆነ ሰውም ቢሆን ይህን ጥያቄ መመለስ አይችልም፡፡

ራስን መግለጽ ራስን ከማወቅ ከጥሎ የሚመጣ ችሎታ ነው፡፡ ስለዚህ ራሱን ያወቀ ሰው ብቻ ነው ራሱን መግለጽ የሚችለው ማለት ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች እኛ ለተናገርነው ማንነታችን ማረጋገጫ የሚሰጡ አካላቶች ናቸው እንጂ ስለኛ ከእኛ የተሻለ የሚገልጹ አይደሉም፡፡
ራሰን መግለጽ መቻል በጣም ጤናማና ትክክል የሆነ ችሎታ ነው፡፡


ተመስገን አብይ