Get Mystery Box with random crypto!

ጀምሮ መጨረስ መቻል ብዙ ነገሮችን እንጀምራለን ነገር ግን የጀመርናቸውን ሁሉ አንጨርስም፡፡ በጣም | ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

ጀምሮ መጨረስ መቻል

ብዙ ነገሮችን እንጀምራለን ነገር ግን የጀመርናቸውን ሁሉ አንጨርስም፡፡ በጣም በጉጉት፣ በተነሳሽነት፣ በፉከራ እንጀምርና ከጥቂት ቀናት በኋላ ስንቀጥለው አይታይም፡፡ ለምን ይመስላችኋል?

አንድ ሰው አንድን ነገር ጀምሮ የማይጨርስ ከሆነ ቀጥሎ ካሉት ውስጥ የማይችላቸው ነገሮች አሉት ማለት ነው፡፡

ፍላጎት፡ ፍላጎቱን ለይቶ የማያውቅ ሰው በጀመረው ነገር ላይ መጽናት አይችልም፡፡ ምክንያቱም በራሱ ፍላጎት ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ፍላጎትና ግፊት ስለሚጀምሩ ከጊዜ በኋላ ያስጠላቸውና ይተውታል፡፡
ውሳኔ፡ ውሳኔ ማለት የጀመርኩትን ነገር መጨረሻውን ሳላይ አላቆምም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከጫፍ እስከምደርስ ድረስ ጉዞዬን እቀጥላለሁ ማለት ነው፡፡ ውሳኔ የአንድን ሰው ሙሉ ህይወት የማስተካከል ሀይል ያለው ትልቅ ችሎታ ነው፡፡
ትኩረት፡ ትኩረቱን የሚፈልገው ነገር ላይ ማድረግ ያልቻለ ሰው የሚጀምረው ብቻ እንጂ የሚጨርሰው ነገር የለውም፡፡ ትኩረታችን በፈለግነው ነገር ላይ ብቻ ለማድረግ ከወሰንንና ከጠበቅን የጀመርነውን ለመጨረስ እንችላን፡፡
ከሌሎች ሰዎች ጋር በህብረት መስራት መቻል፡ አንዳንዶቻችን የጀመርነውን ነገር ያለማንም እርዳታ ብቻችንን ለማድረግ እንለፋለን በኋላም ከአቅማችን በላይ ይሆንብንና እንተወዋለን፡፡ ሰዎችን የመያዝ ጥበብ የሌለው ሰው የጀመረውን ማንኛውንም ነገር ለመጨረስ ይከብደዋል፡፡ በህብረት መስራት መቻል የጀመርነውን ለማሳክት በጣም ቁልፍ ችሎታ ነው፡፡
በለውጥ ውስጥ መማር መቻል፡ ሁሉም ነገሮች እኛ በምንፈልገው ፍጥነትና መንገድ ብቻ አይሄዱም፡፡ አንዳንዴም ከጠበቅናቸው ውጪ የሆኑ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ ስለዚህ የጀመርነውን ነገር በማሳካት ሂደት ውስጥ ለሚገጥሙን ማንኛውን ነገር ራስን ማዘጋጀትና ራስን ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡
Temu