Get Mystery Box with random crypto!

#ሰበር_መረጃ! ተመድ በመቐለ ነዳጅ መዘረፉን ገለፀ!! የ WFPን መረጃ ያረጋገጠ መግለጫ UN ሰጥ | የብልፅግና ወዳጅ/Prosperity Lover

#ሰበር_መረጃ!
ተመድ በመቐለ ነዳጅ መዘረፉን ገለፀ!!
የ WFPን መረጃ ያረጋገጠ መግለጫ UN ሰጥቷል። ለእርዳታ የገቡ 12 ነጃጅ የያዙ ቦቴዎችን ዛሬ ከመቀሌ በሽብርተኛው ህወሃት ታጣቂዎች ተዘርፈዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ፤ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ ዛሬ ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ጥዋት በትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) መጋዘን መዘረፉን ገልፀዋል።
ዱጃሪች ፤ ዛሬ ማለዳ የትግራይ ኃይሎች መቐለ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል በመግባት 12 የነዳጅ ታንከር ተሽከርካሪዎችን 570,000 ሊትር ነዳጅ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
በቦታው የነበረው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቡድን ዘረፋውን ለመከላከል የተሳካ መኩራ አድርጎ እንደነበር ተናግረዋል።
የተዘረፈው ነዳጅ ለሰብዓዊ ድጋፍ ፣ ምግብ፣ ማዳበሪያና ሌሎች አስቸኳይ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚውል ነበር ያሉት ዱጃሪች " ነዳጁ በመዘረፉ በመላው ሰሜን ኢትዮጵያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ለመድረስ የሚሰራው የሰብዓዊው ድጋፍ ስራ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል " ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰብዓዊ ስራ ሊውል የነበረው ነዳጅ ላይ የተፈፀመውን ዝርፊ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።