Get Mystery Box with random crypto!

Estifanos 🇪🇹 Info

የቴሌግራም ቻናል አርማ prosperityfirst — Estifanos 🇪🇹 Info E
የቴሌግራም ቻናል አርማ prosperityfirst — Estifanos 🇪🇹 Info
የሰርጥ አድራሻ: @prosperityfirst
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.04K
የሰርጥ መግለጫ

ለብልጽግና የፊት እንጂ የኃላ ማርሽ የለንም

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 14:32:49 የሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡
https://t.me/ProsperityFirst
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ያወጣው ወቅታዊ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የሕወሐት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው!

መንግሥት ለሰላም አማራጭ ዕድል ለመስጠት ሲል የሕዝብ ማዕበል አስነሥቶ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ለመማገድ የመጣውን የሕወሐት ታጣቂ፣ በምሥራቅ አማራ በኩል በጀግንነት ሲከላከል ቆይቷል።

ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም።

በዚህም ምክንያት ለሰላም የተሰጠውን ሁለንተናዊ አማራጭ አሽቀንጥሮ ጥሎ ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ይገኛል።

ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው ሕወሐት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል። ይሄንን የሕወሐት ወረራ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈቱበትን ጥቃቶች በጽናት እየተከላከለ፣ አሁንም ለሰላም አማራጮች የዘረጋቸውን እጆች ዛሬም ድረስ አላጠፈም።

ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም ያሳስባል። ወገናችን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሐት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
78 viewsfanaye tesfaye, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:32:45
76 viewsfanaye tesfaye, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:23:13 በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች የተጣለ የሰዓት እላፊ ገደብ መረጃ
https://t.me/ProsperityFirst
ወልድያ ከተማ
ለሰው - ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 1፡00 ሰዓት
ለተሽከርካሪ - እስከ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ
https://t.me/ProsperityFirst
ሰቆጣ ከተማ
ለሰው - ከምሽቱ 1፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት
ለተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት
ለተፈናቃይ - ከካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ ሙሉ በሙሉ ክልክል ነው
https://t.me/ProsperityFirst
ሐይቅ ከተማ
ሰው - ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ
ለተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ
መጠጥ ቤቶች - ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ
https://t.me/ProsperityFirst
ኩታበር
ተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ
መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ
ሰው - ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ
https://t.me/ProsperityFirst
ደሴ ከተማ
ለከተማው ነዋሪ - ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ
ለምግብና መጠጥ ቤቶች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ
ለማንኛውም እንግዳ - ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ
ለታክሲ - ከምሽቱ 2፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ
ለባጃጅ - ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ
https://t.me/ProsperityFirst
ኮምቦልቻ ከተማ
ለሰውም፣ ታክሲዎችም - ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ
https://t.me/ProsperityFirst
መቅደላ ከተማ
ለሰው - ከምሽቱ 2፡00 እስከ ጧቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ
ለተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡ዐዐ እስከ ጧቱ 12፡ዐዐ ሰዓት
ለምግብና መጠጥ ቤቶች - ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ
https://t.me/ProsperityFirst
ደብረ ብርሃን ከተማ
ለተሽከርካሪ - ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ
ለምግብና መጠጥ ቤቶች - ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ
ለተፈናቃይ - ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ከተማዋም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።
https://t.me/ProsperityFirst
ደባርቅ ከተማ
ለባጃጅ - ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በኋላ
ለተፈናቃይ - ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በኋላ ወደ ከተማውም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል፡፡
127 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:22:38
93 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, 20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:13:43 #ከልደታዎቹ_ሁለት_ንግስቶች_አንዷ_መቅዲ_ብረቷ
https://t.me/ProsperityFirst
ልደታ ሁለት ጀግና ሴት የወረዳ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች አሏት Mekdes Yadeta የወረዳ 1 ዋና ስራ አስፈጻሚ እና Birtukan Bahiru የወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈጻሚ... የወረዳ አንዷ ንግስት ዛሬ በከተማ ደረጃ በተከበረው የ #አሸንዳ በዓል ላይ እንዲህ ፏ ብላ ህብረ ብሔራዊ አቋሟን፣ አስተሳሰብና አተያይዋን በተግባር ስታስመሰክር ነው የዋለችው፡፡
#መቅዲ_ብረቷ #Go_Ahead
102 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:13:37
97 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:46:17 ከ 500 በላይ ለሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረውና በኦቪድ ኮንስትራክሽን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሲገነባ የነበረው B+G+9 የመኖሪያ ቤት ግንባታ የስትራክቸር ስራ መጠናቀቁን ተከትሎ ለፕሮጀክቱ ሠራተኞቹ የእራት ግብዣ ሊካሄድላቸው የተዘጋጀው ፕሮግራም ሊጀመር እንግዶች ቦታ ቦታቸውን እየያዙ ይገኛሉ፡፡
https://t.me/ProsperityFirst
111 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, edited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:46:16
106 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:29:20 ቤትህ ሲያከብርህ፣ ሲሸልምህ በጣሙን ደስ ከማለቱም ከፍ ብሎ እስከ ልብህ፣ እስከ ውስጥህ ይሰማኸል
https://t.me/ProsperityFirst
የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደርን ከልብ #አመሠግናለሁ
መላውን የክፍለ ከተማችንን የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት በይበልጥ ደግሟ የሊጋችንን ጠርናፊ #ፍፄ Fitsum Girefe ከልብ #አመሠግናለሁ
95 viewsእስጢፋኖስ Estifanos, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 11:33:00 በቴክኖሎጂ የዘመነው፣ ሌብነትን በሚገባ የቀነሰው፣ የተገልጋዮችን እንግልት በተግባር ያስቀረው፣ የተገልጋዮችን እርካታ ያረጋገጠው የየካ ክፍለ ከተማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፡፡
https://t.me/ProsperityFirst
በየካ ክፍለ ከተማ እያየናቸው ካሉ ጽ/ቤቶች አንዱ የሆነው የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የካ ቅርንጫፍ ሙሉ ለሙሉ ስራውን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረጉ ምክንያቱ የመጡና መሬት የነኩ ለውጦችን በተግባር ለመመልከት ችለናል፡፡

በዚህ የጉብኝት ፕሮግራም ላይ የተገኙትና ማብራሪያ የሰጡን የቅርንጫፍ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ኃላፊ አቶ ደረጄ አሰፋ "በዚህ ሰዓት የተገልጋዮችን እሮሮን አስቀርተን፣ የተገልጋዮችን እርካታ በማረጋገጥ ላይ እንገኛለን፡፡ ሁሉም ስራዎቻችን ከወረቀት ንክኪ የጸዱ እንደመሆናቸው መጠን በርካታ የሚባክኑ ሰአቶችን ቆጥበናል፣ በቀንም የምናስተናግደውን የተገልጋይ ቁጥር መጨመር ችለናል፡፡ በክፍለ ከተማችን 128 ሺህ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ እና 54 የተሽከርካሪዎች ፋይሎች ያሉን ሲሆን እነዚህን ፋይሎች በሙሉ በቴክኖሎጂ አስተሳስረን ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን" ሲሉ ገለጻ አድርገዋል፡፡
84 viewsRational View, 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ