Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቋል ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ለሁለት ቀናት  | Prime Media

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቋል

ፕራይም ሚዲያ(አዲስ አበባ)_ለሁለት ቀናት  በኢ ሲ ኤ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ከደቂቃዎች በፊት ፍፃሜውን አግኝቷል።

የፕሬዝዳንትነት እና የሥራ-አስፈፃሚው ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ በጉባኤው በታዛቢነት የተገኙት የፊፋ እና የካፍ ተወካዮች ምርጫው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስረድተዋል።

ዳግም በፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት መንበር የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ጂራ በቆይታቸው መልካም ሥራ እንደሚሰሩ ቃል ገብተው በክብር እንግድነት በተገኙት የባሕል እና ስፖርት ሚንስቴር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የመዝጊያ ንግግር ተጠናቋል።

ደረጀ አዱኛ