2022-02-08 19:46:47
#ረዥሙ_መንገድ
“ረዥም ርቀት ሳትጓዝ አሁን ላይ ባሉ ነገሮች ውስጥ ደስታህን መፈለግ ትችላለህ - ራስህንም ከደስታህ አታሽሽ”
#ማርከስ_አውሬሊየስ
ብዙ ሰዎችን ምን እያደረጉ እንደ ሆነ ጠይቃቸው፤ “
__ ለመሆን እ
የመከርኩ ነው” ነው ይሉሃል። ወይም የሆነ የስራ እድገትን ሊያገኙ እንደ ሆነ አልያም አዲስ ቢዝነስ ሊጀምሩ፣ ሚልየነር ሊሆኑ፣ ታዋቂ ለመሆን እና ወዘተ እንዳሰቡ ይነግሩሃል። እናም ራስህን እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቀው፤ ‘ስለምን ይህን ታደርጋለህ?’ ወይም ‘መጨረሻ ላይ ከዚህ ነገር ምን ማግኘት ትፈልጋለህ?’ አብዛኞቹ ፍላጎቶችህ ሲጠቃለሉም ነጻነትን ወይም ደስታን የማግኘት አልያም በሌሎች መከበር ይሆናሉ።
ስቶይክ እነዚህን ፍላጎቶችህን ተመልክቶ ምን ያህል ቀላል እንደሆኑ እና በቀጥታ ምንም ሳትለፋ ልታገኛቸው የምትችላቸው እንደሆኑ ይነግርሃል። ማሳደድም ሆነ መድከም አይጠበቅብህም። አድራጎትህም ልክ አንድን እቃ ሄደህ ከማንሳት ይልቅ አመታትን ፈጅተህ እቃውን የሚያነሳ ማሽን እንደመፈልሰፍ ነው። መነጽርህን ፍለጋ ብዙ ቦታ ካገላበጥክ በኋላ መነጽርህን ጭንቅላትህ ላይ እንደማግኘት ነው።
ነጻነት? ቀላል ነው። በምርጫዎችህ ውስጥ አለ።
ደስታ? ቀላል ነው። በምርጫዎችህ ውስጥ አለ።
ክብር? እርሱም ቀላል ነው፤ በምርጫዎችህም ይወሰናል።
እናም ይህ ሁሉ ከፊትህ አለ። ረዥሙንም መንገድ መጓዝ አይጠበቅብህም።
#የለት_ፍልስፍና መጽሐፍ
ስለ ስኬት እናውራ
https://t.me/positivevibee
704 views16:46